| በሰሜን ወሎ ከ1ሺ በላይ አሽከርካሪዎች ተቀጡ |
|
|
| Sunday, 17 February 2008 | |
|
በሰሜን ወሎ ዞን የትራፊክ ደንብ በመተላለፍ ከ1ሺ በላይ አሽከርካሪዎች ተቀጡ፡፡ የዞኑ ፖሊስም አሽከርካሪዎቹ ከ66 ሺ ብር በላይ መቀጣታቸውን አመልክቷል፡፡
ዘንድሮ የተቀጡት አሽከርካሪዎች ብዛት ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ሲነፃፀር የ165 ብልጫ አለው፡፡ የትራፊክ አደጋ በዞኑ እየጨመረ የመጣ ሲሆን ባለፉት ወራት በደረሰው የመኪና አደጋ 17 ሰዎች ሞተዋል፣ ከ1ዐዐ የሚበልጡ ቆስለዋል፡፡ የመምሪያው የትራፊክ ደህንነት ባለሙያ ምክትል ኢንስፔክተር ተስፋዬ ንጉሴ እንደገለፁት አደጋው የተከሰተው በአሽከርካሪ ብቃት ማነስ፣ ጥንቃቄ ጉድለት፣ ከተወሰነ ፍጥነት በላይ ማሽከርከርና የቴክኒክ ብቃት ማነስ ነው፡፡ (ኢዜአ) ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች ከግማሽ ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ተገኘ ባለፉት ስድስት ወራት ወደ ውጪ ከተላከ የግብርናና የፋብሪካ ምርቶች ሽያጭ 553.6 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ከፍተኛ ገቢ በማስገባት የላቀ አፈፃፀም ድርሻ ካላቸው ምርቶች ውስጥ ቡና ቀዳሚውን ደረጃ የያዘ ሲሆን በሽያጩም ከ144 ሚሊዮን ደላር በላይ ተገኝቷል፡፡ የቅባት እህሎች፣ ጫትና ጥራጥሬ በሽያጭ ደረጃቸው ከሁለት እስከ አራተኛ ደረጃ ይዟል፡፡ በዘንድሮው ግማሽ የበጀት ዓመት ከተያዘላቸው እቅድ በላይ ገቢ በማስገባት በውጪ ገበያ ሽያጭ ክንውናቸው ልቀው የተገኙት የግብርና ምርቶች ጥጥ፣ እጣንና የጥራጥሬ ምርቶች ናቸው፡፡ (አዲስ ዘመን፣ የካቲት 7 ቀን 2000 ዓ.ም.) ባለሥልጣኑ ከ50 ሚሊንዮ ብር በላይ ካሣ ከፈለ ከኮምቦልቻ ወልዲያ ለሚካሄደው የአስፋልት መንገድ ሥራ ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ የካሣ ክፍያ መፈፀሙን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቁ፡፡ የካሳ ክፍያው የተፈፀመው የመንገድ ሥራ ኘሮጀክቱ በሚገነባበት መሬት ላይ ለነበሩት የተለያዩ ንብረቶች፣ ለእርሻ መሬት፣ የዛፍና የቋሚ አትክልቶች፣ ለመኖሪያና ለንግድ ቤቶች ግምት መሆኑን፣ የመንገድ ሥራው የሚያልፍባቸው የኮምቦልቻ፣ ደሴ፣ ሐይቅ፣ ውጫሌ፣ ሁርጌሳና መርሳ ከተሞችም መከፈሉን ገልጿል፡፡ (ዋኢማ) ለንስር አሞራ የመጀመሪያ ቀዶ ህክምና ተደረገ አንዲት ወርቃማ ንስር አሞራ ከከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሀይል ተሸካሚ ምሰሶ ጋር ተላትማ በተፈጠረባት የኤሌክትሪክ አደጋ ዓይኗን ብታጣም ህክምና ከተደረገላት በኋላ በከፊል ማየት መቻሏን የግላስጐ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡ ኤሌክትራ በመባል የምትጠራው ንስር አሞራ ጉዳቱ የደረሰባት ከቁራዎች ጥቃት ለማምለጥ ስትሞክር መሆኑን፣ ቀዶ ህክምናው ከተደረገላት በኋላ ወደ መጠለያዋ መመለሷንና ወርቃማ ንሥር አሞራዎች ከከፍተኛ ርቀት ላይ ሆነው የሚያድኑትን ነገር አጥርተው በማየት ረገድ የታወቁ መሆናቸውን ዩኒቨርሲቲው አብራርቷል፡፡ ክለቡ ትራኮማ በሽታን ለማጥፋት ከ45 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት መድቦ በመንቀሳቀስ ላይ ነው “ላይንስ ክለብ ኢትዮጵያ” በአማራ ክልል በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ለዓይነ ስውርነት የሚዳርገውን የትራኮማ በሽታ ሙሉ በሙሉ ለማስወገድ ከ45 ሚሊዮን ብር በላይ መድቦ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑን አስታወቀ፡፡ ለክለቡ ልዩ ልዩ ድጋፍ የሚሰጥ ክልል ዓቀፍ ማህበርም ተመስርቷል፡፡ (ኢዜአ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |