| የዓመት በዓል ገበያ |
|
|
| Sunday, 06 January 2008 | |
|
በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት መካከል አንዱ የገና በዓል ነው፡፡
እንደ ልምድ በዓላትን በፌሽታና በሆታ የማክበር ልምድ አለን፡፡ ለበአሉ የምናወጣው ወጪ ይለያያል፡፡ ቀላል የማይባል ወጪ እናወጣለን፡፡ ሌላው ቀርቶ በዓልን ተበድሮና ተለቅቶ የማክበር አጉል ልምዳችንም እንዳለ ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ አውደዓመት ገበያውን ለየት ያደርገዋል፡፡ ነጋዴዎች ተመሳሳይ በዓላትን ተከትለው የሚያደርጉት የዋጋ ጭማሪ ሸማቾችን ሲያማርር ቆይቷል፡፡ በዓል ስለሆነ ወይም ለበዓሉ ሲባል ሸማቹ ሳይወድ በግድ ይገዛል በሚል እሣቤ በተለያዩ እቃዎች ዋጋ ላይ ድርጊት መከላከል አልቻልንም፡፡ ጭማሪ ይደረጋል፡፡ ሰሞኑንም ወይም በኢትዮጵያ ሚሌኒየም የመጀመሪያው ገና ዋዜማ ያስተዋልነውም ይህንኑ ሸማቾችን የሚያማርር ድርጊት ነው፡፡ ወደ ገበያ የወጣ ሸማች በተለይ ለበዓሉ አስፈላጊ ናቸው በተባሉ ምርቶች ወይም እቃዎች ላይ ዋጋ ተጨምሮ ያያል፡፡ ከበዓሉ መዳረሻ የተወሰኑ ሳምንታት በፊት ከ48 እስከ 50 ብር የነበረ ሦስት ሊትር የያዘ የታሸገ ዘይት ከ55 ብር በላይ ሆኗል፡፡ የታሸጉ ቅቤዎችም ዋጋ የሁለትና የአምሥት ብር ጭማሪ አድርጓል፡፡ ሌሎችም ምርቶች እንዲሁ የዋጋ ለውጥ እየታየባቸው ነው፡፡ ለምን ይህ ሆነ ሲባል የሚሰጠው መልስ ..በዓል ነው.. የሚል ነው፡፡ ከአንድ ወር በፊት የተገዛና በመጋዘን ያለ ምርት ለበዓሉ ዋጋው ተጨምሮ ይሸጣል፡፡ እንደ ምሳሌ በቀድሞ ዋጋ ከአንድ የታሸገ ዘይት ይገኝ የነበረው ትርፍ ሦስት ብር ቢሆን በዓል ሲደርስ ትርፉ ሰባትና አስር ይሆናል፡፡ ከዚያም በላይ፡፡ ዓይነት ተገቢ ያልሆነ አሠራር የሚከተሉ ነጋዴዎች አሉ፡፡ ሥነ ምግባር ጥያቄ የሚያስነሳባቸው አይደሉም፡፡ ሸማቹ በዓል ስለሆነ ለምን ብሎ አይከራከርም፡፡ ምርጫም የለውም፡፡ ቢከራከርም የሚሰጠው መልስ ከገዛህ ግዛ ካልሆነ ተወው የሚል ነው፡፡ ስለዚህ በአውደ ዓመት ዋዜማዎች የሚደረጉ አግባብነት የሌላቸውን ጭማሪዎች መቆጣጠር ባለመቻሉ ሸማቹ ሁሌም ተጎጂ ነው፡፡ ሌላው በሰሞኑ ገበያ መታዘብ የቻልኩት እንደ እንቁላል ዓይነት ምርቶችን እንደልብ አለማግኘት ነው፡፡ ከተገኘም ዋጋቸው ጨምሯል፡፡ አንድ እንቁላል አንድ ብር ከ25 ሣንቲም ይሸጣል፡፡ ቀደም ብሎ ከዘጠና ሣንቲም እስከ አንድ ብር ይሸጥ ነበር፡፡ እንደ ልብ ያልተገኘበትም ዋናው ምክንያት ሰው ሠራሽ ጥረት ለመፍጠር ይመስላል፡፡ ዋጋ ለመጨመር መሆኑንም አያጠራጥርም፡፡ በዓሉን ምክንያት በማድረግ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል ብለው ማስታወቂያ የሚያስነግሩና የሚለጥፉ ባለመደብሮች አሉ፡፡ እንደ ምሳሌ የጫማና የአልባሳት መደብሮችን ማንሳት ይቻላል፡፡ እነዚህ ባለመደብሮች የሚሸጡት ምርት ላይ ይህን ያህል ይሸጥ የነበረው1በይህን ያህል ቀንሷል ብለው ይለጥፋሉ፡፡ የአንዳንዶች ማስታወቂያ ውሸት ነው፡፡ ሸማቹን ለማታለል የሚደረግ ስሌት ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ተግባር ሁሉም ባለመደብሮች ይጠቀሙበታል ማለት አይደለም፡፡ እውነተኛ ቅናሽ የሚያደርጉ መኖራቸውንም መካድ አይቻልም፡፡ አውደ ዓመትን ተከትሎ ለመክበር የሚደረግ ሸፍጥ የጥሩ ነጋዴ መገለጫ ሊሆን አይችልም፡፡ ውጤታማ ነጋዴም አያሰኝም፡፡ በተነፃፃሪው ደግሞ በአውደ ዓመት ዋዜማ የሚፈጠርን ያልተገባ ግብይትን ለመቆጣጠር ወይም በስግብግብ ነጋዴዎች መዳፍ ውስጥ ላለመግባት ሸማቾችም ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ሸማቾች ለአውደ ዓመት የሚሆኑ ቁሳቁሶችን በዓሉ ከመድረሱ ቀናት በፊት የመሸመት ልምድን ማዳበር ባለመቻላቸው ለችግሩ መባባስ ምክንያት ይሆናሉ፡፡ በናታን ዳዊት |
| < Prev |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |