Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Aug 08th
Home arrow Sections arrow በፍቅረኛሞች ቀን ዋዜማ ከኢትዮጵያ...
በፍቅረኛሞች ቀን ዋዜማ ከኢትዮጵያ... Print E-mail
Sunday, 17 February 2008
በፍቅረኛሞች ቀን ዋዜማ ከኢትዮጵያ የተላከው አበባ በ20 በመቶ ጨምሯል

የፍቅረኞችን ቀን (ቫላንታይን ዴይ) ምክንያት በማድረግ ከኢትዮጵያ ለአለም አቀፍ ገበያ የቀረበው አበባ በ20 በመቶ፣ ዋጋው ከ10 እስከ 15 በመቶ መጨመሩ ተገለፀ፡፡ ከፍቅረኞች ቀን በፊት በነበረው አንድ ሳምንት በቀን 6 አውሮፕላን ወይም ከ1.5 እስከ 2 ሚሊዮን የተለያዩ አበቦች ለአለም አቀፍ ገበያ ቀርበዋል፡፡
የኢትዮጵያ አበባ አምራቾችና ላኪዎች ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ፀጋዬ አበበ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት፣ ደማቅ ቀይ አበቦች ለፍቅረኞች ቀን ማድመቂያ ተፈላጊ በመሆናቸው ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ አበባ ላኪዎች ለአለም አቀፍ ገበያ ያቀረቡትን አበባ ቁጥር አሳድጎታል፡፡

ባለፈው ሳምንት በነበረው ገበያ አብዛኛው አበባ ወደ ሆላንድ፣ ጀርመን፣ ጃፓን መላኩንም ገልፀዋል፡፡

በተጠናቀቀው የፈረንጆች ዓመት አበባ ወደ ውጭ ገበያ በማቅረብ ከ25 ሚሊዮን ዶላር የተገኘ ሲሆን፣ ገቢው ከ2006 ጋር ሲነፃፀር በ5 እጥፍ እንደሚበልጥ ተመልክቷል፡፡

በአሁኑ ሰዓት የአበባ ኢንዱስትሪ ለጠቅላላ አገራዊ ምርት ያለውን የአንድ በመቶ ድርሻና በወጪ ንግድ ያለውን የ10 በመቶ ድርሻ በማሳደግና በቀጣዩ አምስት አመታት በቡና የተያዘውን ደረጃ ለማስያዝ መታቀዱን አቶ ፀጋዬ አስታውቀዋል፡፡

አቶ ፀጋዬ እንዳሉት፣ በወር በ40 የተለያዩ አገሮች እስከ 8 ሚሊዮን አበቦች ለገበያ ይቀርባሉ፡፡ በተያዘው የበጀት ዓመት ከአበባ ወጪ ንግድ 166 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለማግኘት ሲጠበቅ፤ በ2006 ዓ.ም የዓመት የወጪ ንግድ ገቢው 700 ሚሊዮን ዶላር ለማድረስ መታቀዱ ተጠቁሟል፡፡

መንግሥት ለአገር ውስጥና ለውጪ ባለሐብቶች የአምስት አመት የታክስ እፎይታ፣ የካፒታል እቃዎችን ከቀረጥ ነፃ የማስገባትና 70 በመቶ የሚሆነውን የማምረቻ ገንዘብ በብድር የማግኘት እድል መስጠቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥ እንዲያመጣ እንዳደረገው አቶ ፀጋዬ ተናግረዋል፡፡

እንደ ኢትዮጵያ አበባ አምራቾችና ላኪዎች ማህበር መረጃ አበባ ኢንዱስትሪው ለ50ሺህ ኢትዮጵያውያን የሥራ እድል ሲፈጥር ከእነዚህ ውስጥ 80 በመቶው ሴቶች ናቸው፡፡

በቤዛዊት ሥዩም
 
< Prev   Next >