Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 06th
Home arrow Sections arrow የሰነዶች ማረጋገጫ ጽ/ቤት በ6 ወራት...
የሰነዶች ማረጋገጫ ጽ/ቤት በ6 ወራት... Print E-mail
Sunday, 17 February 2008
የሰነዶች ማረጋገጫ ጽ/ቤት በ6 ወራት 16.9 ሚሊዮን ብር ሰበሰበ

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት በ2000 በጀት ዓመት በመጀመሪያው ስድስት ወር ከሰጠው አገልግሎት ከ16.9 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡
የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ይርጋ ታደሠ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት በስድስት ወር ውስጥ ጽ/ቤቱ አገኛለሁ ብሎ ያቀደው ገቢ 15.4 ሚሊዮን ብር እንደነበርና የተገኘው ግን 16.9 ሚሊዮን ብር በመሆኑ የእቅዱን 109.83 በመቶ አከናውኗል ብለዋል፡፡

በስድስት ወራት ውስጥ 100 ሺህ ጉዳዮችን ለመቀበል አቅዶ 101 ሺህ 798 ጉዳዮችን ማስተናገዱና ለእነዚህም ጉዳዮች የቀረቡ 138 ሺህ 889 ባለጉዳዮች መሆናቸውም ተጠቅሷል፡፡

በዘንድሮ የስድስት ወራት የእቅድ አፈፃፀም ካለፉት ሦስት ዓመታት ተመሳሳይ ወቅቶች ጋር ሲነፃፀር በጽ/ቤቱ የሚስተናገዱ ባለጉዳዮች መጨመራቸውን ያመለክታል፡፡

በ1997 ዓ.ም የመጀመሪያ ስድስት ወራት የተስተናገዱት ጉዳዮች ብዛት 70”022 እንደነበር ያስታወሱት አቶ ይርጋ ይህ ቁጥር በአሁኑ ወቅት ወደ 101”889 ማሳደግ መቻሉንም አመልክተዋል፡፡

በአራቱ ተከታታይ ዓመታት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የገቢ ሁኔታን በተመለከተም በ1997 ዓ.ም 14.03 ሚሊዮን ብር በ1989 ዓ.ም 17.04 ሚሊዮን ብር በ1999 ዓ.ም ደግሞ 19.6 ሚሊዮን ብር መገኘቱ ታውቋል፡፡

ይህም የገቢ መረጃ በ1999 የበጀት ዓመት የተገኘው ገቢ ከሌሎች ዓመታት ከተገኘው ገቢ ጋር ብልጫ አለው፡፡

ጽ/ቤቱ የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ፕሮግራሞችን እንደቁልፍ ተግባር በመውሰድ አገልግሎቱን ፈጣንና ዘመናዊ ለማድረግ ተከታታይ ማሻሻያዎች እየወሰደ እንደሚገኝ አቶ ይርጋ ገልፀዋል፡፡ በየጊዜው አገልግሎቱን በማሻሻል ተገልጋዩ የበለጠ የሚረካበትና ሕጋዊነትን ተከትሎ ጤናማ የንግድና የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ለማድረግ የሚችልበት ሁኔታ በማመቻቸት ላይ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

በጽ/ቤቱ የ6 ወራት የሥራ ክንውን በሚያመለክተው ሪፖርቱ ላይ እንደተጠቀሰው ደግሞ በአሰራሮቹ ላይ ያጋጠሙ ችግሮች እንዳሉ ጠቁሟል፡፡

ዋና ዋና ችግሮች ናቸው ብሎ ካስቀመጣቸው ውስጥ በርካታ የተጭበረበሩ መታወቂያዎችና ሌሎች ሰነዶች ይዘው የሚቀርቡ ባለጉዳዮች ማጋጠማቸው፣ ከጽሕፈት ቤቱ ጋር ግንኙነት ያላቸው እንደመሬት ልማትና አስተዳደር ባለስልጣን፣ የትራንስፖርት ባለስልጣንና የመሳሰሉት ቀናት የምንገናኝበት መድረክ ባለመኖሩ ሰነድ ለማረጋገጥ መጉላላትና መመላለስ ታይቷል፡፡

ይህ መስሪያ ቤት ቀደም ሲል የውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት ይባል የነበረ ሲሆን አዋጅ ቁጥር 334/1995ን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 467/1997 መሠረት የሠነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት ተብሎ መጠራት የጀመረ ሲሆን በአዲሱ መጠሪያው ከሐምሌ 1 ቀን 1998 ዓ.ም ጀምሮ ተጠሪነቱ ለፍትህ ሚኒስቴር ሆኖ በፌዴራል ደረጃ ሥራ መጀመሩ ይታወቃል፡፡ በአሁኑ ወቅትም በአዲስ አበባ በዋና መስሪያ ቤት እና በአራት ቅርንጫፎች እንዲሁም በድሬዳዋ አንድ ቅርንጫፍ በመክፈት በሕግ የተሰጡትን ተግባራትና ኃላፊነቶች እየተወጣ መሆኑን የገለፁት አቶ ይርጋ ጽ/ቤቱ በቀጣይ ለመሥራት ካቀዳቸው ተግባራት ውስጥ በጣም በተጨናነቀና በተጣበበ ቦታ ላይ የሚገኙ ጽ/ቤቶችን በተለይም ልደታ ለሚገኘው የቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሚሆን ቢሮ በመከራየት ተገቢውን አገልግሎት መስጠት ይገኝበታል፡፡

በዳዊት ታዬ
 
< Prev   Next >