Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለከፍተኛ...
በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለከፍተኛ... Print E-mail
Sunday, 17 February 2008
በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለከፍተኛ ትምህርት ትኩረት ይሰጣሉ
ታዳጊዎቹ በትምህርታቸው ውጤታማ አይደሉም

በአሜሪካ የሚገኙ ብዙሀን ኢትዮጵያውያን ለከፍተኛ ትምህርት ትልቅ ትኩረት የሚሰጡ ሲሆን የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ የሆኑ ታዳጊ ኢትዮጵያውያን ግን በትምህርታቸው ብዙም ውጤታማ እንዳልሆኑ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አገልግሎት የተሰኘውና በሳንሆዜ ካሊፎርኒያ የሚገኝ የዲያስፖራ ተቋም ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል፡፡
ወደ አሜሪካ የሚሄዱ ኢትዮጵያውያን ቢያንስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁና የከፍተኛ ትምህርት ለመቀጠል ፍላጎትና ከፍተኛ ትጋት እንዳላቸው የሚያሳየው ይህ ሪፖርት ካሊፎርኒያ ውስጥ ካሉ የተማሩ ጥቁር ስደተኞች ኢትዮጵያዊያኑ ከፍተኛውን ቁጥር እንደሚይዙ ያመለክታል፡፡ እንደ ሪፖርቱ በአካባቢው ከሚኖሩ ከሀምሳ ከመቶ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የባችለር ዲግሪና ከዚያም በላይ አላቸው፡፡ ነገር ግን እነዚህ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ሳሉ ባገኙትም ሆነ አሜሪካ በተማሩት ዲግሪአቸው አልያም በትምህርት ደረጃቸው ስራ ሊቀጠሩ እንደሚችሉ ወይም ትምህርታቸውን መቀጠል እንደሚችሉ አያውቁም በማለት ሪፖርቱ ያትታል፡፡  

በተቃራኒው አሜሪካ ውስጥ በመጀመሪያና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ኢትዮጵያውያን ሕፃናት በትምህርታቸው ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው በመጥቀስ የባህል፣ የቋንቋና የአኗኗር ዘዴ ለኢትዮጵያዊያን ሕፃናቱ የትምህርት ብቃት መቀነስ ዋነኛ ምክንያቶች መሆናቸው በሪፖርቱ ተገል”ል፡፡ በተጨማሪም የአቻ ግፊት (Peer pressure) ተፅዕኖ የሚበረታባቸው መሆኑ በትምህርታቸው ደካማ እንዲሆኑ አድርጓል ይላል ሪፖርቱ፡፡ የአቻ ግፊት ተፅዕኖዎቹ የዕፅ ተጠቃሚነት የመሳሰሉትን ችግሮች በታዳጊዎቹ ላይ ያስከትላሉ፡፡ የተለያዩ ባህሎችን ጎን ለጎን ማስኬድና ከተለያዩ ህብረተሰቡና ባህል ከወጡ ግለሰቦች ጋር ተጣጥሞ መኖር ለሕፃናቱ ፈታኝ መሆኑን ወላጆቻቸው ገልፀዋል፡፡ ብዙዎቹ ሕፃናቶች በትምህርታቸው ጥሩ ውጤት እንዲያስመዘግቡ የወላጆች ወይም የአዋቂዎች እገዛ እንደሚያስፈልጋቸውና ይህን ድጋፍ ለማግኘት ደግሞ ባሕልና የቋንቋ ተፅእኖ እንደሚያሳድሩ ብዙ ወላጆች ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ አገልግሎት በካሊፎርኒያ ዋነኛ አላማው ለነዚህ ሕፃናትና ወጣቶች የትርፍ ጊዜ ማጠናከሪያ ትምህርት ሲሆን የተማሪዎቹ ወላጆች በዚህ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያዊያን ወላጆችም ከፍተኛ እገዛ እያደረገ ይገኛል፡፡ አገልግሎቱ ለልጆቻቸው በሚያደርገው ድጋፍ ሕፃናቱና ወጣቶቹ ለትምህታቸው ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ  ከመቻላቸው ባሻገር ከአባባቢው የሚጫንባቸውን የተለያዩ ተጽዕኖዎች ለመቋቋም መቻላቸውን ወላጆቹ ጠቁመዋል፡፡

የአዋቂ ኢትዮጵያውያኑን የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት በሚመለከት ወደሚቀጥለውን የትምህርት ደረጃ ለመቀጠል የሚያስችል ሁኔታ መኖሩ፣ የከፍተኛ ትምህርታቸውን ላቋረጡ ደግሞ የተወሰነ ክሬዲት ተይዞላቸው የጀመሩትን የትምህርት ዘርፍ መቀጠል እንደሚችሉ በሪፖርቱ ተገል”ል፡፡

ሪፖርቱ እንደሚያመለክተው እነዚህ ኢትዮጵያዊያን በጀመሩት የትምህርት ዘርፍ መቀጠል ባይችሉ እንኳ ወደ ሌላ የትምህርት ዘርፍ መግባት የሚችሉበት እድል አለ፡፡ በአብዛኞቹ ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች ከውጭ አገር ለመጡ ተማሪዎች በነፃ እገዛ የሚያደርጉ አማካሪዎችን በመጠቀም የሚሠሩ ናቸው፡፡ እነዚህ አማካሪዎች ለተማሪዎቹ ቀደም ሲል በትምህርታቸው ያስመዘገቡትን ውጤት ማየት ይፈልጋሉ፡፡ ለዚህም ተማሪዎቹ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ሰርተፊኬት ወይም የዲግሪ ወረቀታቸውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ በኋላ እነዚህ አማካሪዎች ያቀረቡትን መረጃዎች በመገምገም ተማሪዎቹ ሊያገኙ የሚችሉትን እገዛ ያስታውቃሉ፡፡ ይህ ግምገማ ተማሪዎቹ አሜሪካ ውስጥ ባለው የትምህርት ሥርዓት ውስጥ በመግባት የሚማሩበትን ሁኔታ ያመቻቻል፡፡ ግምገማው የሚደረገው የተለያዩ አገሮች የትምህርት ሥርዓትን በማነፃፀር ሲሆን ከውጭ አገር የሄዱ ተማሪዎችን ቀጣይ የትምህርት ሁኔታ ብቻ ሳይሆን የመቀጠር እድላቸውንም ይወስናል፡፡

የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አገልግሎት በአሜሪካ ካሊፎርኒያ - ሳን ሆዜ ደግሞ ስደተኞቹ የሚያስፈልጋቸውን አጠቃላይ መረጃ በዌብሳይቱ በኩል ይሰጣል፡፡

በጋዜጣው ሪፖርተር
 
< Prev   Next >