| የአትላንቲስ መጠቃ ለሌላ ጊዜ ተላለፈ |
|
|
| Sunday, 06 January 2008 | |
|
ናሳ ከአውሮፓ ኰሎበስ ላብራቶሪ ሊያመጥቃት የነበረችው መንኮራኩር አትላንቲስ ጉዞ ለሌላ ጊዜ ተላልፏል፡፡
ጉዞው በነዳጅ ሥርዓት ውስጥ በተፈጠረ ችግር ምክንያት ከጥር ወደ የካቲት ተዛውሯል፡፡ የስፔስ ስቴሽን ኘሮግራም ማናጀር ማይክ ሲፈርዲኒ እንደገለፁት መንኩራኩሯ እንደ ጁሌስ ቬርኔ /የአውሮፓ አውቶሜትድ ትራንስፈር መሳሪያ/ ሆና ማየት ስለምንፈልግ ወደ የካቲት አስተላልፈነዋል ብለዋል፡፡ ናሳ በአሜሪካና በአውሮፓ የጠፈር ጥናት ቡድን አትላንቲስን በተሣካ ሁኔታ ለማምጠቅ ዕቅድ ያለው ሲሆን በነዳጅ አካሏ በደረሰ የአሠራር መዛባት ሁለት ጊዜ የመምጠቂያ ኘሮግራም ሠርዟል፡፡ ..ይህ ለእኛ ትልቅ ፈተና ነው.. ያሉት የአምጣቂ ቡድኑ መሪ ሊኦፓልድ አይ ሃርትሶ የአትላንቲስ መዘግየት ቀናት ብቻ ሣይሆን ሣምንታትም ሊጠይቅ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |