| የአፍሪካ የሴቶች ኘሮቶኮል... |
|
|
| Sunday, 17 February 2008 | |
|
የአፍሪካ የሴቶች ኘሮቶኮል እንዲፀድቅ ጥሪ ተደረገ የአፍሪካ ሴቶችን ሁለንተናዊ መብት ለማረጋገጥ ያግዛል የተባለው የህብረቱ የሴቶች መብት ኘሮቶኮል እንዲፀድቅ ለማድረግ ዘመቻ በመደረግ ላይ መሆኑ ተጠቆመ፡፡ የህብረቱ አባል ሀገራት በሙሉ ኘሮቶኮሉን በማፅደቅ አስገዳጅ ህግ እንዲሆን የበኩላቸው እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል፡፡ “ሶሊዳሪቲ ፎር አፍሪካን ውሜንስ ራይትስ” የተሰኘው ተቋም ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ “የአፍሪካ ህብረት የሴቶች መብቶች ኘሮቶኮልን ለማፅደቅ ዘመቻ” በሚል ባካሄደው ስብሰባ ላይ የድርጅቱ ሊቀመንበር ሚስ ፋይዛ መሐመድ እንዳሉት ኘሮቶኮሉ በአፍሪካ ደረጃ አስገዳጅ ህግ መሆኑ የሴቶችን ሁለንተናዊ መብት ለማረጋገጥ ይረዳል፡፡ መብቶቹም የሥነ ተዋልዶ ጤና መብትን ማረጋገጥ፣ የሴት ልጅ ግርዛትን ማስቀረት፣ በሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃትን ማስቀረት፣ እኩል ክፍያ ማግኘት፣ የሴቶችን ምስል የሚያበላሹ ማስታወቂያዎችን ማስቀረት የመሳሰሉት ናቸው፡ ኘሮቶኮሉ ሊፀድቅ መንግሥት ለኘሮቶኮሉ አንቀፆች መተግበር በጀት እንዲመብ ከማስገደድ አንስቶ የሴቶች ጉዳይ ቢሮዎች፣ ፍትህ ቢሮዎችና ፖሊስ ለኘሮቶኮሉ መረጋገጥ እንዲሠሩ ያደርጋል፡፡ አፍሪካ ህብረት አባል ሀገራቱ ኘሮቶኮሉን እንዲፈርሙ የማስገደድ ግዴታ ቢኖርበትም እስካሁን የፈረሙት ከ53 ሀገራት 2ዐ ያህሉ ብቻ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ኘሮቶኮሉን ብትፈርም አላፀደቀችም፡፡ ኘሮቶኮሉ የሀገሪቱ ህግ አካል እንደሆነ በፓርላማ ፀድቆ መውጣት ይኖርበታል፡፡ ድርጅቱ በ2ዐዐ9 የሚካሄደውን የኀብረቱን የሴቶች ስብሰባ ጨምሮ በተገኘው አጋጣሚ አገራቱ ኘሮቶኮሉን እንዲፈርሙ ለማድረግ ዘመቻ ያካሂዳል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |