| ከመጠን ያለፈ ውፍረት... |
|
|
| Sunday, 17 February 2008 | |
|
ከመጠን ያለፈ ውፍረት የሴቶች ችግር ሆኖ ይቀጥላል በአሜሪካ ሴቶች ላይ የተደረገን ጥናት ጠቅሶ ኒውስ ዊክ እንዳስነበበው ከሀገሪቱ አዋቂ ሴቶች ሁለት ሦስተኛው ከመጠን ያለፈ ውፍረት ችግር ሲኖርባቸው ለመቀነስ የሚያደርጉት ጥረትም ውጤት አልባ ነው፡፡ እንደዘገባው ሴቶች ከመጠን ባለፈ ውፍረታቸው ፈፅሞ ደስተኛ ባይሆኑም ለመቀነስ የሚያደርጉት ጥረት አናሳ ነው፡፡ ስለሆነም ከመጠን ያለፈ ውፍረት የሴቶች ችግር ሆኖ ይቀጥላል፡፡ በተጨማሪም በአጭር ጊዜ ክብደት የመቀነስ ግብ አስቀምጠው የሚንቀሳቀሱትም ቢሆኑ ከጥረታቸው በኋላ ክብደታቸው ሲመዘን አሁንም ከክብደት በላይ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በዘገባው እንደተመለከተው ከመጠን ያለፈ ክብደት ያላቸው (ወፋፍራም) ጓደኞች የመሚይዙ ሴቶች ክብደት ለመቀነስ ያላቸው ፍላጐት አናሳ ነው፡፡ ተመሳሳይ ክብደትን እንደመደበኛ ጉዳይ የማየታቸው ነገር ያመዘነ ነው፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |