| ቤጅንግን የአየር ብክለት አስግቷታል |
|
|
| Sunday, 06 January 2008 | |
|
በአየር ብክለት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች የምትባለው ቤጅንግ ሰኞ እለት 246ኛው ..የሰማያዊ ሰማይ ቀን..ን ምዝገባ ያካሄደች ሲሆን ባለሥልጣናት ከተማዋ የብክለት ሰለባ ሆናለች ብለዋል፡፡
በ2008ቱ የቤጂንግ ኦሊምፒክ ላይ ተፅዕኖ ሊያደርስ ይችላል የተባለውን የከተማዋ ብክለት አስመልክቶ በቅርቡ የኦሊምፒክ የበላይ ኃላፊ ጃኮሰ ሮግ የኦሊምፒክ ኘሮግራሞች በአየር ሁኔታው የተነሳ ሊለዋወጡ ይችላሉ ብለዋል፡፡ የቻይና ባለሥልጣናት ይህንን ለመከላከል ቁጥጥር እያደረጉ ነው፡፡ የአካባቢና ጥበቃ ቢሮ ዳይሬክተር የሆኑት ዱ ቫኦዞንግ ለዥንዋ እንደገለፁት ..የሰማያዊ ሰማይ ቀንን ካወጅን አሥር ቀን አልፎናል፡፡ ይሁን እንጂ አሸዋ አዘል ነፍስ ያሰጋናል.. ብለዋል፡፡ በሳይንቲስቶች መመዘኛ መሠረት የሰማያዊ ሰማይ ቀንን ለማወጅ ሦስት የአየር ብክለት ደረጃዎች ተቀምጠዋል፡፡ የቢቢሲ ዘጋቢ ሬኖልድ ከቤጅንግ ይህንን የቤጅንግን እወጃ ጥሩ ነው ብሎታል፡፡ ቤጅንግ ለ2ዐዐ8 ሁለት መቶ ሃምሳ ስድስት የሰማያዊ ሰማይ ቀን ዕቅድ ነድፈዋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |