Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 28th
Home arrow Sections arrow አዲሱ የፖስታ አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ...
አዲሱ የፖስታ አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ... Print E-mail
Wednesday, 20 February 2008
አዲሱ የፖስታ አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ የሠራተኛ ሽግሽግ ጀመሩ

በቅርቡ የፖስታ አገልግሎት ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ሆነው የተሾሙት አቶ ግደይ ገብረዮሐንስ በድርጅቱ ውስጥ የሠራተኛ ሽግሽግ መጀመራቸውን ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ አመለከተ፡፡

በሥራ አስኪያጁ የሠራተኛ ሽግሽግ መሠረት በድርጅቱ የእቅድና ዝግጅት ግምገማ ክፍል ኃላፊ የነበሩት አቶ ሰይድ ከድር ከኃላፊነታቸው ተነስተው በኤክስፐርት ደረጃ እንዲሰሩ ሆኗል፡፡ የድርጅቱ የድጋፍ ሰጪ የሥራ አስፈፃሚ የነበሩት አቶ በዛብህ አስፋው በአቶ ታደለ አስፋው መተካታቸው ታውቋል፡፡

የኢ.ኤም.ኤስ ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ግዛቸው ወርቁ በወይዘሪት ይፍቱሥራ መኮንን ሲተኩ፣ የደብዳቤ አሰራር የሥራ ሂደት ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ፋንታበል አበበ በአቶ በዛብህ አስፋው ተለውጠዋል፡፡

በድርጅቱ የማርኬቲንግና ቢዝነስ ዲቨሎፕመንት ማኔጀር የነበሩት አቶ ቢያዝንልኝ አስረስ ከኃላፊነታቸው ተነስተው በወይዘሪት ይፍቱሥራ መኮንን ቦታ ወደ ፋይናንሺያል ቢዝነስ የሥራ ሂደት መደብ ተመድበው እንዲሰሩ መደረጉ ተጠቁሟል፡፡

በሽግሽጉ ከኃላፊነታቸው የተነሱት አቶ ግዛቸው ወርቁና አቶ ፋንታበል አበበ በምንም ሥራ አልተመደቡም፡፡

አንዳንድ የድርጅቱ ሠራተኞች ሽግሽጉን አስመልክተው ቀደም ሲል የነበሩት ሥራ አስኪያጅ የሠሩትን ስህተት እንዳይደገም አሳስበዋል፡፡ ሠራተኞቹ አይይዘው አዲሱ ሥራ አስኪያጅ የጀመሩት ሽግሽግ አግባብ ቢሆንም በወሳኝ ክፍሎች ላይ የተደረገው ምደባ እንደገና እንዲታይ ጠይቀዋል፡፡

በአሰግድ ተፈራ
 
< Prev   Next >