| የኪራይ ቤቶች ህንጻ ተደርምሶ... |
|
|
| Wednesday, 20 February 2008 | |
|
የኪራይ ቤቶች ህንጻ ተደርምሶ በሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ
ንብረትነቱ የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት የሆነውና "ለአድማስ ዘመናዊ ሴንተር አክስዮን ማህበር" በሊዝ የተሰጠው ህንፃ ተደርምሶ በንብረትና በሕይወት ላይ ጉዳት አደረሰ፡፡ ችግሩ የተከሰተው በኪራይ ቤቶች ቸልተኝነት ምክንያት መሆኑን የአድማስ ዘመናዊ አክስዮን ማህበር ገል ል፡፡ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ቀበሌ 19 የሚገኘውንና ንብረትነቱ የኪቤአድ የሆነው ህንፃ ተደርምሶ ሁለት ሰዎችን ሲገድል ስምንት መኪኖችንና ሌሎች ንብረቶችን ከጥቅም ውጭ አድርጓል፡፡ የአድማስ ዘመናዊ አክስዮን ማህበር የቦርድ አባል አቶ ተክለመድህን በቀለ ለሪፖርተር እንደገለጹት ህንፃው በ1992 ዓ.ም በሊዝ ቢሸጥም ባለአክስዮኖቹ ህንጻውን አፍርሰው ግንባታ እንዲጀምሩ አልተፈቀደላቸውም፡፡ የባለአክስዮኖቹ የህንፃ ግንባታ በተቃደው ጊዜ ባለመከናወኑ ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ የግንባታው ወጪ ከ35 ወደ 45 ሚሊዮን ብር ማደጉን አክለው ገልፀዋል፡፡ ባለአክሲዮኖቹ ሲነግዱበት የቆዩበትን ቦታ በሊዝ ገዝተው የሚፈለግባቸውን የሊዝ ገንዘብና ተጨማሪ የቤት ግምት ማሟያ ክፍያ ገቢ አድርገው ከመስከረም 30/1998 ዓ.ም በፊት የገበያ ማዕከሉ የዲዛይኑ ስራው ቢያልቅም ባልታወቀ ምክንያት ህንፃውን በማፍረስ ግንባታ መጀመር አለመቻላቸውን ተናግረዋል፡፡ ከባለአክስዮኖቹ ተደጋጋሚ ጥያቄ የቀረበለት የአዲስ አበባ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት በ1998 ዓ.ም ኪቤአድ በፃፈው ደብዳቤ ለንግድ አገልግሎት ግንባታ እንዲውል በሊዝ በተሰጠው ቦታ ላይ አልሚዎች ወደ ሥራ ለመግባት ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁ መሆኑን ጠቅሶ በኪራይ ቤቶች በኩል የካሳ መጠን ተረጋግጦ የልማት ሥራው በፍጥነት እንዲጀመር ጠይቆ ነበር፡፡ አቶ ተክለ መድህን እንደሚሉት ኪቤአድ ከክፍለ ከተማው ለተላከው ደብዳቤ የሰጠው ምላሽ የለም፡፡ በዚህም ምክንያት ረጅም እድሜ ያስቆጠረው ህንፃ ፈርሶ በንብረትና በሕይወት ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡ የአድማስ ዘመናዊ አክስዮን ማህበር መጋቢት 17 ቀን 1999 ዓ.ም ለአዲስ አበባ አስተዳደር የመሬት አስተዳደር ባለሥልጣን በፃፈው ደብዳቤ ሠላሳ አራቱ ባለአክስዮኖች 40 በመቶ የሚሆነውን ገንዘብ አሰባስበው ወደ ግንባታ ለመግባት ቢዘጋጁም ህንጻው ባለመፍረሱ ወደ ስራው አለመግባታቸውን አስታውቋል፡፡ የችሮታው ጊዜም የተቃጠለ በመሆኑ ጊዜው ታስቦ እንዲስተካከልለትና ለህንፃው የሚከፈለው ኪራይም ያልተቋረጠ በመሆኑ እንዲቆምለት ጠይቋል፡፡ አክስዮን ማህበሩ በፃፈው በዚህ ደብዳቤ ባለአክስዮኖቹ ውል ፈጽመው ካርታ የተረከቡት ነሐሴ 29/1997 ዓ.ም መሆኑን አመልክቷል፡፡ ጉዳዩን አስመልክተን ያነጋገርናቸው የኪቤአድ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ካሳሁን የፈረሰውን ህንፃ ጉዳይ ፖሊስ እየተከታተለው መሆኑን ገልፀው ህንፃው በሊዝ ተሸጧል ስለሚባለው ጉዳይ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ በኃይሌ ሙሉ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |