Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Monday
Sep 08th
Home arrow Sections arrow ዶ/ር አሸብር ለፓርላማ ይወዳደራሉ
ዶ/ር አሸብር ለፓርላማ ይወዳደራሉ Print E-mail
Wednesday, 20 February 2008
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት የነበሩት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ለተወካዮች ምክር ቤት አባልነት የግል ተወዳዳሪ ሆነው እንደሚቀርቡ ተገለፀ፡፡
ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ በወረዳ አስራ ስምንት (ሪቼ አከባባቢ) የምርጫ ክልል በግል ለመወዳደር የሚስችላቸውን መስፈርት አሟልተው የእጩነት መታወቂያ እየተጠባበቁ መሆኑን ከምርጫ ክልሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ዶ/ር አሸብር በምርጫ ሕጉ መሠረት የግል ተወዳዳሪዎች ሊያሟሏቸው የሚገቡትን መስፈርቶች አሟልተዋል፡፡ ከአንድ ሺህ በላይ የአካባቢው ነዋሪዎች በአካባቢው ነዋሪ ስለመሆናቸው የፊርማ ማረጋገጫ በማሰባሰብ ለምርጫ ጣቢያው አስገብተዋል፡፡

በምርጫ ሕጉ መሰረት ከአንድ ሺህ በላይ ፊርማ ያሰባሰቡት ዶ/ር አሸብር በአሁኑ ደረጃ ተጠቋሚ እጩ መሆናቸው ተገል"ል፡፡

ዶ/ር አሸብር ላለፉት ሁለት ዓመታት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ ቆይተው በቅርቡ ከኃላፊነታቸው ቢነሱም ሕጋዊ ፕሬዚዳንት እንደሆኑ በመጥቀስ ለፊፋ ያቀረቡት ክስ ውሳኔ እንዳልተሰጠው ይታወቃል፡፡

በተሾመ ንቁ
 
< Prev   Next >