Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow በተጭበረበረ ሰነድ ከንግድ ባንክ...
በተጭበረበረ ሰነድ ከንግድ ባንክ... Print E-mail
Wednesday, 20 February 2008
በተጭበረበረ ሰነድ ከንግድ ባንክ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ 600ሺህ ብር ተወሰደ

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ በተጭበረበረ ሰነድ ከአንድ ግለሰብ ሂሳብ ብር 600,000 (ስድስት መቶ ሺህ ብር) ተወሰደ፡፡ በተጭበረበረ ሰነድ ገንዘቡን እንዲከፈል ያደረገው ሠራተኛም ታሰረ፡፡
ግለሰቡ 600ሺህ ብሩ እንዲከፈለው የጠየቀው ሕጋዊ ማስረጃዎችና ሰነዶች ናቸው ያላቸውን በማቅረብ ሲሆን በጥያቄው መሠረት ማስተናገድ ይቻል እንደሆነ ጉዳዩ ለባንኩ የሕግ መምሪያ ቀርቦ የሚመለከታቸው የባንኩ የሕግ ባለሙያዎች በተጠየቀው መሠረት ይከፈል ዘንድ የውሳኔ ሃሳባቸውን ለባንኩ ሰጥተዋል፡፡

ገንዘቡ ከተከፈለ በኋላ ባንኩ የተጭበረበረ መሆኑን ያወቀው የገንዘቡ ባለቤት መጥተው ሂሳባቸውን ሲጠይቁ ነው፡፡ ባንኩም ገንዘቡን ወጪ አድርጎ እንዲከፈለው ያደረገው ሰው ባቀረበው ሰነድ መሰረት በተገቢው ሁኔታ መከፈሉን ቢገልጽም ከዋናው/እውነተኛው ባለገንዘብ በቀረበው ተቃውሞ ጉዳዩ ሲጣራ ባንኩ መጭበርበሩን ለመረዳት ችሏል፡፡

በተጭበረበረ ሰነድ ገንዘቡን የወሰደው ግለሰብም በቁጥጥር ሥር መዋሉን ለመረዳት ተችሏል፡፡    

በጋዜጣው ሪፖርተር
 
< Prev   Next >