Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 28th
Home arrow Sections arrow ተስፋዬ ብሩ ታሰሩ
ተስፋዬ ብሩ ታሰሩ Print E-mail
Wednesday, 20 February 2008
Imageፀረ ሙስና ንብረታቸው እንዲታገድ ጠየቀ
ቴሌ ለ1.54 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ተዳርጓል


የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ብሩ ታሰሩ፡፡ የፌዴራሉ ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በአቶ ተስፋዬ ላይ የመሰረተው ክስ ኮርፖሬሽኑ ላይ የ1.54 ቢሊዮን ብር ኪሳራ አድርሰዋል በሚል ነው፡፡
አቶ ተስፋዬ በቁጥጥር ስር የዋሉት ከትናንት በስቲያ ሰኞ መሆኑን ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡

አቶ ተስፋዬና የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ ኃላፊዎች ኮርፖሬሽኑ ባካሄደው ኦዲት ጥፋተኛ ተብለው ከሥራ እንዲሰናበቱ ተወስኖባቸው ነበር፡፡

ኮርፖሬሽኑ አስተዳደራዊ እርምጃ ከወሰደባቸው በኋላ የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ትኩረት ሰጥቶ ምርመራ በማካሄድ አገኘኋቸው ባላቸው ግድፈት ያላቸው ግዢዎች፣ ስምምነቶችና ውሎች ላይ ተንተርሶ ክስ መስርቷል፡፡

የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የቀድሞ የኢትዮጵያ ቴሌ ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስኪያጅ የአቶ ተስፋዬ ብሩንና የሃያ ስድስት የኮርፖሬሽኑ የሥራ አመራር አባላት ንብረት እንዳይንቀሳቀስ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥያቄ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

የኮሚሽኑ ዋና ሥራ አስኪያጁ በስልጣን ዘመናቸው ኮርፖሬሽኑን ለ1.54 ቢሊዮን ብር ኪሳራ መዳረጋቸውን በመጥቀስ፣ "በግለሰቡ ስም የተያዙ ተሽከርካሪዎች፣ የመኖሪያ ቤቶችና የባንክ ሒሳብ እንዳይንቀሳቀሱ ይታገድልኝ" ሲል ታህሳስ 23/2000 ዓ.ም ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ታህሳስ 25/2000 ዓ.ም በዋለው ችሎት ኮሚሽኑ የተጠርጣሪ ግለሰቦችን ንብረት ለይቶ እንዲያቀርብ ጠይቆ ነበር፡፡

የኮርፖሬሽኑ የዳሬክተሮች ቦርድ በ1998 ዓ.ም ባደረገው ድንገተኛ ጉባኤ አቶ ተስፋዬንና ሁለት ምክትል ሥራ አስኪያጆችን ከስልጣን በማስወገድ አቶ አማረ አምሳሉን መሾሙ ይታወሳል፡፡ የኮርፖሬሽኑ የኦዲት ሪፖርት ከስልጣን የታገዱት የአመራር አባላት የፈጸሟቸው ውሎች፣ ስምምነቶችና ግዢዎች የተጭበረበሩ እንደነበሩ ይፋ ማድረጉ አይዘነጋም፡፡ የኦዲት ሪፖርት ውጤትን ተከትሎ የኮርፖሬሽኑ ኦዲት፣ የሥራ አመራር፣ የውልና የጨረታ ኮሚቴ አባላትን ከሥራ አባሯል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የኦዲት ሪፖርቱን ለፀረ ሙስና ኮሚሽን በማቅረብ አስፈላጊው የወንጀል ምርመራ እንዲደረግ ጠይቋል፡፡

ኮሚሽኑ ታህሳስ 2 ቀን 2000 ዓ.ም የቀድሞ የኮርፖሬሽኑ የሥራ አመራር አባላትና የኮሚቴ አባላት ዝቅተኛ ደረጃ ያላቸውና መወገድ የሚገባቸውን መሳሪያዎች ግዢ ማከናወናቸውን አስታውቋል፡፡ ኮሚሽኑ ትኩረት ሰጥቶ የመረመረው ከስዊድኑ ኤሪክሰን ኩባንያ ጋር የተደረገው የሞባይል ማስፋፊያ የቅድመ ክፍያ ስምምነት፣ ከአሜሪካው ሉሰንት ጋር የተደረገውን የሶላር ኃይል መሳሪያዎች አቅርቦት ስምምነት ላይ መሆኑን ለፍርድ ቤቱ ገል"ል፡፡ በዚህም አቶ ተስፋዬ 48.5 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ከኤሪክሰን ኩባንያ ጋር ለሁለተኛ ጊዜ የቅድመ ክፍያ የኔትዎርክ ማስፋፊያ ስምምነት መፈራረማቸውን ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ አቶ ተስፋዬና ሃያ ስድስት የአመራር አባላት ኩባንያውን ከጨረታው ሂደት ባለማገዱ በአሰራር ሂደቱ ውስጥ ጥርጣሬ እንዳለው አመልክቷል፡፡ በዚህም "ኤሪክሰን የፕሮጀክት እንዲሁም የአቅርቦት ጨረታውን ሉሰንት እንዲያሸንፍ በማድረግ፣ የሥራ አመራሩ ዝቅተኛ ደረጃ ያለው የእቃና የአገልግሎት አቅርቦት እንዲኖር በማድረግ ኮርፖሬሽኑ ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ ለሆነ ኪሳራ ዳርገውታል" በማለት ከሷል፡፡

የኮሚሽኑ የምርመራ መምሪያ የምርመራ ውጤቱን ለኮሚሽኑ አቃቤ ሕግ ያቀረበ ሲሆን አቃቤ ሕግ ምርመራውን አጣርቶ ክስ እስኪመሰርት ድረስ የተጠርጣሪዎቹ ንብረትና የባንክ ሂሳብ እንዲታገድ ጥያቄ ማቅረቡ ይታወሣል፡፡   

በአሰግድ ተፈራ
 
< Prev   Next >