Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 07th
Home arrow Sections arrow ቡሽ በአፍሪካ ለወባ መከላከል ዘመቻ...
ቡሽ በአፍሪካ ለወባ መከላከል ዘመቻ... Print E-mail
Wednesday, 20 February 2008
ቡሽ በአፍሪካ ለወባ መከላከል ዘመቻ እገዛ እንደሚያደርጉ ገለፁ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ በሰብ ሰሃራ አፍሪካ ለሚደረገው የወባ መከላከል ዘመቻ አገራቸው አምስት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን የወባ ትንኝ መከላከያ አጎበር እርዳታ እንደምታደርግ መግለፃቸውን የአሶሽየትድ ፕሬስ ዘገባ አመለከተ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ይህን የገለፁት በአምስት የአፍሪካ አገራት የሚያደርጉትን ጉብኝት በአሩሻ ታንዛኒያ እያካሄዱ ባሉበት ወቅት ነው፡፡ ቡሽ በታንዛኒያ ለሚገኙ ከአንድ እስከ አምስት አመት የዕድሜ ክልል ለሚገኙ ህፃናት በነፃ የወባ መከላከያ አጎበር እንደሚያቀርቡም አክለው ገልፀዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ቡሽ “በወባ ምክንያት የሚደርሰውን የሰው ልጆች ህይወት ጥፋትና የኢኮኖሚ ውደቀት የአሜሪካ ህዝቦች አይቀበሉትም” ብለዋል፡፡ የአሜሪካ ህዝብ የሰውን ህይወት የማዳን የሞራል ግዴታ አለበት ሲሉ ፕሬዚዳንቱ ገልፀው አሜሪካ በአፍሪካ የሚደረገውን የፀረ ወባ ዘመቻ አጋዥ መሆኗን አስታውቀዋል፡፡

ወባ በአፍሪካ ለህፃናት ሞት ዋነኛ መነሾ መሆኑንና በየሰላሳ ሰከንድ አንድ ህፃን በወባ ምክንያት ህይወቱን እንደሚያጣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገልጿል፡፡ የአለም አቀፉ የጤና ድርጅት በበኩሉ በአፍሪካ ከአምስት የህፃናት ሞት አንዱ በወባ ምክንያት መሆኑን ገልጿል፡፡

ራይስ ኬንያ ገቡ

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኮንዶሊዛ ራይስ የኬንያን የምርጫ ውዝግብ ለመፍታት ያለፈው ሰኞ ኬንያ መግባታቸውን ቢቢሲ ዘገበ፡፡

ኮንዶሊዛ ራይስ ፕሬዚዳንት ሙዋይ ኪባኪና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ራይለ ኦዲንጋ ስልጣን ለመጋራት ከስምምነት ላይ እንዲደርሱ የሚያደርጉ መሆኑ ተገምቷል፡፡ ኮንዶሊዛ በኬንያ መንግስትና በተቃዋሚዎች መካከል ድርድር እንዲካሄድ በመሸምገል ላይ የሚገኙትን ኮፊ አናንን የሚያነጋግሩ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የራይስን ጉብኝት አስመልክቶ የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሴስ ዌታንጉላ “ወዳጆቻችን የሚያደርጉት እገዛ የሚደነቅ ነው፤ ነገር ግን የሀይል ጫና ለማድረግ ሙከራ እንዳያደርጉ” ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ ሚኒስትሩ “ምንም እንኳን የጎብኝዎቻችን ጥረት እኛን ለመርዳት ቢሆንም፤ የኬንያ ችግር መፍትሄው ኬንያውያን ጋር ነው ያለው” በማለት ገልፀዋል፡፡

በኬንያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት ምክንያት የተነሳው ውዝግብ ፖለቲካዊ እንዲሁም የጎሳ ግጭት ማስነሳቱ ይታወሳል፡፡ በዚህም በትንሹ አንድ ሺ ሰዎች ሲሞቱ ከስድስት መቶ ሺ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ታውቋል፡፡

በፓኪስታን ምርጫ ተካሄደ

በፓኪስታን ያለፈው ሰኞ በመላው አገሪቱ የፓርላሜንታዊ ምርጫ መካሄዱን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገባ አመለከተ፡፡

በዘገባው መሠረት የምርጫው ሂደት በቤናዚር ቡቶ ሞት ምክንያት ቀዝቀዝ ያለ እንደነበር ተገልጿል፡፡ የአገሪቱ የፖሊስ ኃይል የምርጫው ስነ-ስርዓት እንዳይሰናከል ከፍተኛ ቁጥጥር ማድረጋቸው ተዘግቧል፡፡

የቅድመ ትንበያ ዘገባዎች የፓኪስታን ምርጫ ካልተጭበረበረ የቤናዚር ቡቶ የፓኪስታን ህዝብ ፓርቲ በአንደኝነት እንደሚያሸንፍና የነዋዝ ሸሪፍ ፓርቲ ሁለተኛ እንዲሁም የፕሬዚዳንት ሙሻራፍ የፓኪስታን ሙስሊም ሊግ ኪው ፓርቲ ሦስተኛ እንደሚሆን ተገምቷል፡፡

የፈረንሳይ ፖሊስ ከ33 በላይ ነውጠኞችን በቁጥጥር ስር አዋለ

የፈረንሳይ ፖሊስ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት የተካሄደውን ነውጥ የመሩትን ለመያዝ በጀመረው ዘመቻ ከ33 በላይ ነውጠኞችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአገሪቱ ዜና አገልግሎት ዘገበ፡፡

የአገሪቱ ፖሊስ የነውጡ ተካፋዮች እንዲሁም በመሪነት ነውጡን የመሩ ግለሰቦችን እየያዘ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በዚህም ፖሊስ የነውጡ ተካፋዮችን ለጠቆመ በሺዎች የሚቆጠር ዩሮ፣ ክፍያ እንዳዘጋጀ አስታውቋል፡፡ ፕሬዚዳንት ሳርኮዚ “የርብሻው ተካፋዮችን በቁጥጥር ስራ ማዋል ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ ነው” ሲሉ አስታውቀዋል፡፡ በረብሻው ወቅት አንድ መቶ አስራ ዘጠኝ ፖሊሶች መቁሰላቸው ይታወሳል፡፡
 
< Prev   Next >