Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow ከድርጅቶቹ ከታክስ በፊት...
ከድርጅቶቹ ከታክስ በፊት... Print E-mail
Wednesday, 20 February 2008
ከድርጅቶቹ ከታክስ በፊት 508 ሚሊዮን ብር ትርፍ ተገኘ

የኘራይቬታይዜሽንና የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ በግማሽ በጀት ዓመቱ ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከታክስ በፊት 508 ሚሊዮን ብር ትርፍ መገኘቱን አስታወቀ፡፡
የተገኘው ትርፍ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ185 ሚሊዮን ብር ብልጫ እንዳለው፣ በውጪ ንግድ ከተሰማሩ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች 291 ሚሊዮን ብር መገኘቱን፣ ምርቶቻቸውን ለውጪ ገበያ የሚያቀርቡ የልማት ድርጅቶችን አፈፃፀም ለማሳደግ ከኢንዱስትሪ ልማት ፈንድ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ አቅማቸውን ለማጠናከር የተለያዩ እርምጃዎች በመውሰድ ላይ መሆናቸውን፣ ለተገኘው ትርፍ ቆዳና ጫማ፣ የእርሻና አግሮ ኢንዱስትሪ፣ የሆቴልና ቱሪዝም፣ የሲሚንቶና ኮንስትራክሽን ዘርፎች ተጠቃሾች መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡

(ኢዜአ)

ብሔረሰቦች ግጭቶችን ለማስወገድ ተስማሙ

በደቡብ ኦሞ ዞን የሚገኙ 17 ብሔረሰቦች አልፎ አልፎ በአካባቢያቸው የሚከሰቱ ግጭቶችን በማስወገድ በጋራ ልማታቸውን ለማፋጠን ተስማሙ፡፡

በጂንካ ከተማ በዞኑ ከሚገኙ 17 ብሔረሰቦች የተውጣጡ ከአንድ ሺ በላይ ሰዎች ተካፋይ የሆኑበት የሠላምና የዕርቅ ውይይት፣ ፓክት ኢትዮጵያ የተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ከደቡብ ኦሞ አስተዳደር ጋር በመተባበር ማወያየቱንና ለግጭቶቹ መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ጐጂ ባህሎችን ለማስወገድና የግንዛቤ ለውጥ ለማምጣት በመንግሥት የተጀመረው ትምህርትን የማስፋፋትና የሴቶችን ተሳትፎ የማሳደግ ጥረት አጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡

(ዋኢማ)

የ100 የመካከለኛ አውቶብሶች ርክክብ ተካሄደ

የአዲስ አበባ ከተማን የትራንስፖርት ችግር ለማቃለል እንዲቻል ከ166 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ውጪ ከቻይና ከተገዙት 5ዐዐ መካከለኛ አውቶብሶች መካከል ወደ አገር ወስጥ የገቡት 1ዐዐዎቹ በፌደራል ትራንስፖርት ባለሥልጣንና በባለሀብቶች መካከል የርክክብ ሥነ ስርዓት ተካሄደ፡፡

ከቀረፅ ነፃ የገቡትን መካከለኛ አውቶብሶች መንግሥት ያወጣውን መስፈርት በማሟላት አሸናፊ ለሆኑ ባለሀብቶች፣ ድርጅቶችና ኩባንያዎች የማስተላለፍ ሥራ መከናወኑን፣ አውቶብሶቹ በቅርብ ቀን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ ተጠቁሟል፡፡

(አዲስ ዘመን የካቲት 9 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም.)

ሐውልቱን መልሶ ለማቆም የመሠረት ግንባታው ተጠናቃቀ

ከኢጣሊያ ሮም ከ68 ዓመት በኋላ የተመለሰውን የአክሱም ሐውልት መልሶ ማቆም የሚያስችለው የመሠረት ግንባታ መጠናቀቁን በትግራይ ክልል ባህል ቱሪዝም ኮሚሽን የአክሱም ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ገለፀ፡፡

የሐውልቱን ማቆሚያ ኮንክሪት መሰረት ግንባታ ያናቀቀው በኢጣሊያ መንግሥት ሥራውን እንዲያከናውን የተደረገው ላታንዚ የተባለ የኮንስትራክሽን ኩባንያ መሆኑን፣ ሁለት ክሬኖችና ሌሎች መሳሪያዎች አክሱም ገብተው የተከላው ሥራ እየተፋጠነ መሆኑን፣ ቁመቱ 23 ሜትር ክብደቱ 17ዐ ቶን የሆነው የአክሱም ሐውልት የማቆም ሥራ በመጪው ነሐሴ 2ዐዐዐ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልፆ በአካባቢው ከ400 የሚበልጡ የቆሙና መሬት ላይ የወደቁ ሀውልቶችና ቅርሶች እንደሚገኙም ቀናግሯል፡፡

(ኢዜአ)
 
< Prev   Next >