| ወፎች ከገጠር ወደ ከተማ እየተሰደዱ ነው |
|
|
| Sunday, 06 January 2008 | |
|
ቢቢሲ አንድን ጥናት መሠረት አድርጐ ሰሞኑን እንደዘገበው ግንደ ቆርቁሮች በእርሻ ማሣዎች ለውጥ ምክንያት ከገጠር ወደ ከተማ እየተሰደዱ ነው፡፡
በገጠር አካባቢ አዕዋፋትን የመመገብ ባህል መዳበርም ሌላው ወፎችን ወደ ከተማ እንዲፈልሱ ምክንያት ነው ብሏል ቢቢሲ በዘገባው፡፡ የእንግሊዝ ፣ትረስት ፎር አሪንቶሎጅ፣ ጥናት እንደሚያመለክተው 46 በመቶ ግንደቆርቁሮች በለንደን አፀዶች የሚገኙ ሲሆን በገጠራማው ክፍል ግን 27 በመቶ ብቻ ይገኛል፡፡ ይህንንም ..አስገራሚ.. ብሎታል አጥኚ ቡድኑ፡፡ ባለፉት አሥርት ዓመታት እንዲህ አልነበረም በተባለው የወፎቹ ፍልሰት አራት ዓይነት ዝርያ ያላቸው ግንደ ቆርቁሮች የበለጠውን ቦታ ይይዛሉ፡፡ ከለንደን በተጨማሪ በማንችስተር 61 በመቶ ይሸፍናሉ፡፡ የአጥኚ ቡድኑ መሪ ፓልሰታን ክሊፍ እንደገለፁት ..በጣም የሚያስገርመው የወፎች ስደት ከገጠር ወጥተው በከተማ መንገዶች ዳር ባሉ አፀዶች እንዲሰፍሩ እያደረገ ነው.. ብለዋል፡፡ እንግሊዝ በክረምት ከሦስት ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ጥንድ ወፎች እንደመኖሪያ እንደምታገለግል ዘገባው አክሎ ገልጿል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |