| የ70 ሚሊዮን ዓመት... |
|
|
| Wednesday, 20 February 2008 | |
|
የ70 ሚሊዮን ዓመት የእንቁራሪት ቅሪተ አካል ተገኘ
በማዳጋስካር ከ7ዐ ሚሊዮን ዓመት በፊት በምድር እንደኖረ የተነገረለት ግዙፍ እንቁራሪት ቅሪተ አካል ሲገኝ ግኝቱ ማዳካስካር፣ ህንድና ደቡብ አሜሪካ እስከ ዳይኖሰር ዘመን ድረስ የተገናኙ አህጉሮች ነበሩ የሚለውን መላ ምት አጠናክሯል ይላል የፊዚኦርግ ድረ ገፅ ዘገባ፡፡ "ሲኦል የመጣው እንቁራሪት" ተብሎ የተጠራው ግዙፍ እንቁራሪት የተገኘው በለንደን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ እና በኒውዮርክ ስቶኒ ብሩክ ዩኒቨርሲቲ አጥኚዎች ነው፡፡ የተገኘው ቅሪተ አካል ባለቤት የሆነው እንቁራሪት በቅርፁ በአሁኑ ወቅት የሚገኘውን ፣ሆርንድ ቶድ፣ እየተባለ የሚጠራ ጉርጥ የሚመስል ሲሆን ሙሉ ሰውነት፣ ትልቅ ጭንቅላትና ሰፊ አፍ አለው፡፡ ርዝመቱ 4ዐ ሴንቲ ሜትር ሲሆን ክብደቱ አራት ኪሎ ይሆናል ተብሏል፡፡ ይኸውም በአሁኑ ወቅት አሉ ከሚባሉ ትላልቅ የእንቁራሪት ዝርያዎች ሁለት እጥፍ የሚሆን ነው፡፡ ቅሪተ አካሉ የማላጋሲ ታሪክ መፅሐፍ ውስጥ የተካተተ ሲሆን የተመዘገበውም ከሥጋ-በል ዳይኖሰሮች፣ እፅዋት በል አዞዎችና ትላልቅ እባቦች ተርታ በአጠቃላይም አሁን በማዳጋስካር ከሚገኙ እንስሳት ሁሉ የተለየ በሚለው ዝርዝር ተቀምጧል፡፡ ሞባይል በብዛት መጠቀም ለካንሰር ሊያጋልጥ ይችላል የሞባይል ስልኮችን አብዝቶ መጠቀም በካንሰር የመጠቃት አጋጣሚን ሊያሰፋው ይችላል ሲል የአሜሪካ ጆርናል ኦፍ ኢፒዲሞሎጂን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ሞባይል አብዝቶ መጠቀም በተለይ በምራቅ አመንጪ እጢዎች ላይ ካንሰር ሊያስከትል እንደሚችል የጠቆመው ጥናቱ የሞባይል ስልክ ጥሪን በተደጋጋሚ በአንድ ጐን ብቻ (በአንድ ጆሮ በኩል) መቀበል ደግሞ በምራቅ አመንጪ እጢዎች ላይ ካንሰር የማስከተል አቅሙ 50 በመቶ ከፍ ያለ እንደሚሆን ገልጿል፡፡ ከዚህ ቀደም የሞባይል አጠቃቀምና ጉዳቶቹን በተመለከተ የተለያዩ ጥናቶች ቢደረጉም በካንሰር የመጠቃትን እድል ይጨምራል የሚል ግኝት አልነበረም፡፡ በእስራኤል የቴል አቪቭ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ግን ከዚህ ቀደም የተደረጉ ጥናቶች የሞባይል ስልክ ከጭንቅላት ካንሰር ጋር ያለው ግንኙነት ላይ ያተኮረና በሞባይል ረዥም ጊዜ ተጠቃሚዎች ላይ ያተኮረ አልነበረም ብለዋል፡፡ ተመራማሪዎቹ ምርመራቸውን ያካሄዱት የሞባይል ስልኮችን ለረዥም ጊዜ የተጠቀሙ 5ዐዐ እስራኤላዊያን ላይ ነበር ጤናማ የሞባይል ስልክ አጠቃቀም ከነበራቸው 1..300 ሰዎች ጋርም ጥናታቸውን በንፅፅር መረጃ አስደግፈዋል፡፡ በውጤቱም መሠረት የሞባይል ስልክ አብዝተው የተጠቀሙት 500 እስራኤላውያን የምራቅ አመንጪ እጢ ካንሰር ምልክት ታይቶባቸዋል፡፡ የምራቅ አመንጪ እጢ ካንሰር በአብዛኛው የሚከሰት የካንሰር ዓይነት ባይሆንም ጥናቱ ይፋ ያደረገው ከረዥም ጊዜ የሞባይል ስልክ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ሊመጣ እንደሚችል ነው፡፡ ጥናቱ እንዳመለከተው ከተማ ከሚኖሩት ይልቅ በገጠራማው አካባቢ የሚኖሩ የሞባይል ተጠቃሚዎች ለችግሩ ያላቸው ተጋላጭነት የሰፋ ነው፡፡ ምክንያቱም በገጠራማ አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች የሞባይል ስልክ ጥሪን በጠራ መልኩ ለመቀበል ስልኮቻቸው ከፍተኛ ጨረርን ስለሚጠቀሙ ነው፡፡ ባለፈው ዓመት የእንግሊዝ ..ሞባይል ቴሌኮሙዩኒኬሽን ኤንድ ሄልዝ ሪሰርች ኘሮግራም.. ሞባይል አጠቃቀምን አስመልክቶ የተጠኑ ጥናቶችና ውጤቶች ትክክለኛ ማረጋገጫ ባይገኝላቸውም ሞባይል በረዥም ጊዜ ሊያስከትል በሚችለው ጉዳትና በህፃናት ላይ የሚያስከትለው ተፅእኖ ዙሪያ ጥናት ማካሄድ እንደሚያስፈልግ ጠቁሞ ነበር፡፡ ሮቦቶች በእንስሳት ላይ የሚደረጉ ምርምሮችን ይቀንሳሉ የአሜሪካ ሳይንቲስቶች አደገኛ ኬሚካሎችን በላቦራቶሪ በሰሩዋቸው ሴሎች ውስጥ መፈተሽ እየጀመሩ ነው፡፡ ጅምሩ ከዚህ ቀደም ህይወት ባላቸው እንስሳት ላይ ይደረጉ የነበሩ የምርምር ሙከራዎችን ይቀንሳል ተብሏል፡፡ የምርምር ውጤቶችን ለማረጋገጥ በሮቦቶች የመጠቀም ወጪን፣ ጊዜንና ከፀረ አረም ጀምሮ ለቤት ውስጥ ጥቅም የሚውሉ ኬሚካሎችን ለመፈተሽ ይውሉ የነበሩ የእንስሳት ቁጥርን ይቀንሳል፡፡ ሮቦቶች ከተፈጥሮ እንስሳት በተለየ መልኩ በቀን ውስጥ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኬሚካሎችን ለመፈተሽና የመርዛማነት መጠናቸውን ለመለየት አቅም አላቸው፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |