Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Aug 08th
Home arrow Sections arrow የእንግሊዙ ኩባንያ በአየር ትራንስፖርትና...
የእንግሊዙ ኩባንያ በአየር ትራንስፖርትና... Print E-mail
Wednesday, 20 February 2008
የእንግሊዙ ኩባንያ በአየር ትራንስፖርትና በታሸገ ውሃ ኢንቨስትመንት ሊሠማራ ነው

በአፍሪካ ለአንድ መቶ ዓመታት በማዕድን ልማት ዘርፍ የካበተ ልምድ ያለው "ሎንርሆ" የተባለው የእንግሊዝ ኩባንያ በኢትዮጵያ በአነስተኛ አውሮኘላን እና በታሸገ ውሃ ኢንቨስትመንት ለመሠማራት ማቀዱን አስታወቀ፡፡
የአፍሪካ ቢዝነስ መፅሄት በዚህ ወር እትሙ እንደዘገበው ሎንርሆ ቀድሞ ከሚታወቅበት የማዕድን ልማት ዘርፍ በተጨማሪ በአፍሪካ በአነስተኛ ክፍያ የሚሠሩ አነስተኛ የመጓጓዣ አውሮኘላኖችን በማዘጋጀት በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

የሎንርሆ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሚስተር ዴቪድ ቤኒጋስ ከአፍሪካ ቢዝነስ መፅሄት ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ እንደገለፁት፣ ከቅርብ ዓመታት ጀምሮ ቻይና እና ህንድ በአፍሪካ ውስጥ ያላቸው ኢንቨስትመንት እየጨመረ መምጣቱ በአህጉራቱ ያሉ ነባር ካምፓኒዎች ሥራቸውን እንዲፈትሹ እና ወደ ተጨማሪ ኢንቨስትመንት እንዲገቡ የሚያደርግ በመሆኑ፣ ኩባንያቸው ኢትዮጵያን ጨምሮ በስድስት ሀገሮች በተለያዩ ኢንቨስትመንት ለመሠማራት ኘሮጀክቶች እያጠናቀቀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሥራ አስፈፃሚው ማብራሪያ እንደሚጠቁመው፣ መንገደኞች አነስተኛ ክፍያ እየፈፀሙ ሊጓጓዙበት የሚችሉበት "ፍላይ 540" የመንገደኞች አውሮኘላንን በመላው አፍሪካ ማስፋፋት ይፈልጋሉ፡፡


በአሁኑ ወቅት ንብረትነቱ የሎንርሆ ኩባንያ የሆነው "ፍላይ 540" አውሮኘላን በኬንያ አትራፊና ታዋቂ እየሆነ የመጣ ሲሆን ኩባንያው በተጨማሪ በአንጎላ 15 አውሮኘላን ማረፊያዎች አገልግሎቱን በመስጠት ተጨማሪ ኢንቨስትመንት በመፈፀም "ፍላይ 540" የመንገደኞች አውሮኘላንን ለማሠማራት በዝግጅት ላይ ነው፡፡

ሎንርሆ ኩባንያ ከማዕድን ልማት ዘርፍና ከአየር ትራንስፖርት በተጨማሪ በታሸጉ ንፁህ የመጠጥ ወሃ ኢንቨስትመንት የተሠማራ ሲሆን በቅርቡ በአንጎላ ከከፈተው የውሃ ማሸጊያ ኩባንያ በተጨማሪ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎች የአፍሪካ አገሮች በዘርፉ ለመሰማራት ዕቅድ ይዟል፡፡

የሩቅ ምስራቅ አገሮች ከአፍሪካ ጋር ያላቸው የንግድ ግንኙነት በአህጉሩ ለዓመታት በኢንቨስትመንት ሲንቀሳቀሱ ለቆዩት ኩባንያዎች አስደንጋጭ መሆኑን የሚናገሩት ዋና ስራ አስፈፃሚው "ተወደደም ተጠላ የሩቅ ምስራቅ ኩባንያዎችን በመፎካከር በአፍሪካ ለበርካታ ዓመታት የሠሩ ኩባንያዎች መንቀሳቀስ ጀምረዋል" ብለዋል፡፡

መፅሔቱ ቢዝነስ በአፍሪካ ውስጥ የ1ዐዐ ዓመታት ልምድ የነበረውን ሎሆርም ታሪክ እንዳቀረበው ከሆነ ኩባንያው ከዓመታት በፊት የነበረውን ስም ለመመለስና መልክዐ ምድር ወደ ማይወስነው ኢንቨስትመንት በመሠማራት የወጡ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት እየጨመረ በመጣበት የአፍሪካ አህጉር ተጨማሪ ልዩነት ፈጣሪ ኩባንያ ለመሆን በዝግጅት ላይ መሆኑን ገልጿል፡፡

ሎንርሆ ከእ.ኤ.አ በ1909 የተመሠረተው በለንደን እና በቀድሞዋ ሮዴሺያ በአሁኑ ዚምባቡዌ በማዕድን ልማት ነበር፡፡ ከዚያም ከዓመት ወደ ዓመት እየቀነሰ የመጣው የአፍሪካ ኢንቨስትመንቱን በማሻሻል በአዲስ መልክ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን መፅሄቱ ገልጿል፡፡

ኩባንያው በሞዛምቢክ የሚገኘው የካርዶሶ ሆቴል ከፍተኛ ባለአክሲዮን፣ በደቡብ አፍሪካ የልዩ ልዩ ኢንዱስትሪዎች ባለንብረት እና እስከ 4ዐ ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ካፒታል ያለው ኩባንያ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ 
 
< Prev   Next >