Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 06th
Home arrow Sections arrow ለኢንሹራንስ ኩባንያዎች በኢንቨስትመንት...
ለኢንሹራንስ ኩባንያዎች በኢንቨስትመንት... Print E-mail
Wednesday, 20 February 2008
ለኢንሹራንስ ኩባንያዎች በኢንቨስትመንት መሰማራት አስቸጋሪ ሆኗል

በኢትዮጵያ የኢንሹራንስ አገልግሎት እ.ኤ.አ በ1905 በግብጽ ባንክ አማካኝነት ተቋቁሞ የተጀመረ ሲሆን በወቅቱ ይሰጥ የነበረው አገልግሎትም ለእሳትና ለባህር አደጋዎች መድን ነበር፡፡ እ.ኤ.አ እስከ 1950 ድረስም በኢትዮጵያ አገር በቀል  የኢንሹራንስ ኩባንያ አልነበረም፡፡
በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጥናት መሠረትም እ.ኤ.አ በ1954 አስራ ዘጠኝ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የነበሩ ሲሆን ከነዚህ አንዱ ብቻ አቀር በቀል ነበር፡፡ በ1960 አካባቢ ደግሞ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ቁጥር 53 ደርሶ ነበር፡፡ በወቅቱ እነዚህ ኩባንያዎች ከመደበኛ ሥራቸው ሌላ በተለያዩ ኢንቨስትመንት መስኮች በመሰማራት አቅማቸውን ለማሳደግ እድል ነበራቸው፡፡  

በ2000 ዓ.ም መጀመሪያ ይፋ የሆነ መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ ደግሞ በአሁኑ ጊዜ አስር የሚደርሱ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ውስጥ በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው፡፡

ዘጠኙ በግል የተያዙ ሲሆን አንደኛው ደግሞ በመንግስት ይዞታ ስር የሚገኝ ነው፡፡ በጥቅሉ የመንቀሳቀሻ ካፒታላቸውን 521.1 ሚሊዮን ብር ያደረጉት እነዚህ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች እስካለፈው አመት ድረስ 146 በሚሆኑ ቅርንጫፎች አገልግሎት እየሰጡ ነው፡፡

ከ521.1 ሚሊዮን ካፒታላቸው 204.5 ሚሊዮን የሚሆነው የመንግሥታዊ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ድርሻ ሲሆን ቀሪው የዘጠኙ የግል የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ነው፡፡

እንደ ኢንሹራንስ ባለሙያዎች ገለፃ ደግሞ ሕጉ በአሁኑ ወቅት እየተንቀሳቀሱ ያሉት የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በተለያዩ ኢንቨስትመንት ሥራዎች ተሰማርተው ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት የሚገድብ ነው ይላሉ፡፡ "የብሔራዊ ባንክ መመሪያ እያደገ ከመጣው ኢንሹራንስ ጋር ሊጣጣም የማይችል መመሪያ አለው" የሚሉት ያነጋገርናቸው የኢንሹራንስ ኩባንያ የሥራ ኃላፊዎች አትራፊ በሆኑ ኩባንያዎች ላይ ኢንቨስት በማድረግ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ገደብ ይጥላል፡፡

በአገራችን ኢንሹራንስ ኩባንያዎች አረቦን በመሰብሰብ የሚያገኙት ገቢ ትንሽ ነው፡፡ ስለዚህ የግድ አትራፊ በሚባሉ ኢንቨስተሮች ውስጥ በመሳተፍ ካፒታላቸውና አቅማቸውን ማሳደግ ይችሉ ነበር፡፡ "ነገር ግን የብሔራዊ ባንክ መመሪያ ፣ከእሴትህ 15 በመቶ ብቻ ለኢንቨስትመንት አውል፣ የሚል ስለሆነ በተቀመጠ ገንዘባችን ለመስራት እንኳን እድል አይሆንም ይላሉ፡፡"

"ብሔራዊ ባንክ በገደብ ካስቀመጠው መጠን በላይ ገንዘባችንን በአትራፊ ሥራዎች ላይ ማዋል አልቻልንም" የሚሉት እነዚሁ የሥራ ኃላፊዎች እንደገለፁት ይህም አትራፊ በሚባሉ ኢንቨስትመንቶች ላይ ተሳታፊ የመሆን እድልን በመንፈጉ ኩባንያዎቹን ያቋቋሙት ባለ አክስዮኖች ገንዘባቸው ያለ ሥራ እንዲቀመጥ ያደርገዋል፡፡ ይህ ገንዘብ ቢሆን ኖሮ አበድሮት ሊጠቀምበት ይችል ነበር፡፡

እ.ኤ.አ በ2004 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የኢንሹራንስ ገንዘብ ኢንቨስትመንትን አስመልክቶ ባወጣው በዚሁ መመሪያ ኢንሹራንሶቹ ከተቀማጭ ገንባቸው ከ65 በመቶ በማያንስ የግምጃ ቤት ሰነድ ጨረታ (ትሬዠሪ) ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ ያመለክታል፡፡

ሆኖም ከዚህ ከግምጃ ቤት ጨረታ ሊገኝ የሚችለው ትርፍ ሦስት ወይም አራት በመቶ ብቻ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለአንድ ኢንሹራንስ ኩባንያ አነስተኛ ነው፡፡ ስለዚህ የብሔራዊ ባንክ መመሪያ ኢንሹራንስ ኩባንያዎች አትራፊ በሆኑ ኢንቨስትመንት ዘርፎች እንዲሳተፉ እድል መስጠት እንዳለበት ጥሩ አስረጅ እንደሆነ ያመለክታሉ፡፡

እንደ ንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ የሥራ ኃላፊዎች ለምሳሌ በዚህ ዓመት ኢንሹራንስ ኩባንያው ያገኘውን ትርፍ ለባለ አክስዮኖች አከፋፍሏል፡፡ ባለአክስዮኖቹ ካፒታላቸውን ለማሳደግ ጠይቀው ነበር፡፡ ሆኖም ካፒታላቸውን ለማሳደግ የሚሸጠው አክስዮን ገንዘብ ያለ ሥራ ስለሚቀመጥ ሳንሸጥ ቀርተናል ብለዋል፡፡

በሌሎች የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ውስጥ ተመሳሳይ የሆነ ችግር ያላቸውን ገንዘብ ኢንሸስት ለማድረግ የሚፈቀደው መጠን አነስተኛ በመሆኑ በሌሎቸ ኢንቨስትመንት ለመሰማራት የነበራቸውን ፍላጎት አጥብቦታል፡፡  

"አክስዮን ሽጠን ገንዘቡን ብንይዝ ምንም ዋጋ የለውም፡፡ ይህ ገንዘብ በባንክ ቢሆን አበድሮ ወለድ ሊገኝበት ይችል ነበር፡፡ የተቀመጠውን የኢንሹራንስ ገንዘብ እንደተፈለገው በኢንቨስትመንት ላይ መዋል አልተቻለም" ይላሉ የኢንሹራንስ ባለሙያዎቹ፡፡  

ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ባላቸው ገንዘብ በሪል ስቴት ሆቴልና ቱሪዝም የመሳሰለው ኢንቨስትመንት ላይ መሳተፍ መቻል አለባቸው፡፡

የብሔራዊ ባንክ መመሪያውን ያወጣው ፣አረቦን ሰብስባችሁ ብሩን ኢንቨስትመንት ላይ የምታውሉት ከሆነ አደጋ ቢገጥም ደንበኛ መቸገር የለበትም፣ ከሚል እሳቤ ቢሆንም የኢንሹራንስ ኩባንያ የሥራ ኃላፊዎች ድርጅታቸውን የሚያስጠይቅ መሰል ሥራ ይሰራሉ ብሎ ማመን ያስቸግራል ባይ ናቸው፡፡

እንደ አስተያየት ሰጪዎቹ ሌላ የቁጥጥር ስልት በማመቻቸት የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ገንዘባቸውን እንዲጠቀሙበት ማድረግ ይቻላል፡፡ አትራፊ በሆኑ ኩባንያዎች ውስጥ ኢንቨስት ማድረጋቸው የተጠቀሰውን የብሔራዊ ባንክ ስጋት ሊቀንስ ይችላል የሚል እምነት ያላቸው እኚሁ የኢንሹራንስ ባለሙያዎች በዚህ ዙሪያ የሌሎች አገሮች ልምድ መታየት እንደሚኖርበት ያምናሉ፡፡

እንደ ባለሙያዎቹ ገለፃ በሌሎች አገሮች የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በአረቦን ከሚሰበሰቡት ገንዘብ በበለጠ በተለያዩ ኢንቨስትመንቶች ውስጥ ተሳትፈው የሚያገኙት ትርፍ ለደንበኞቻቸው የበለጠ አገልግሎት እንዲሰጡ ያበረታታቸዋል፡፡

በዳዊት ታዬ
 
< Prev   Next >