Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Jul 04th
Home arrow Sections arrow በሙስና ወንጀል ሲፈለግ የነበረው...
በሙስና ወንጀል ሲፈለግ የነበረው... Print E-mail
Sunday, 24 February 2008
በሙስና ወንጀል ሲፈለግ የነበረው በቁጥጥር ስር ዋለ
 
ከዚህ በፊት በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ከመሬት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ በሙስና ድርጊት ተጠርጥረው ሲፈለጉ ከነበሩት ግለሰቦች መካከል ኑረዲን ያሲን ጎቢር የተባለው ግለሰብ ሐሙስ የካቲት 13/2000 ዓ.ም በቁጥጥር ስር መዋሉን የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ተጠርጣሪው በግንቦት ወር 1999 ዓ.ም እጁን ለኮሚሽኑ እንዲሰጥ በመገናኛ ብዙሀን ጥሪ ተላልፎለት የነበረ ቢሆንም በቁጥጥር ሥር እስከዋለበት ድርስ እራሱን ሸሽጐ እንደቆየ ኮሚሽኑ ገል"ል፡፡

በተመሳሳይ ድርጊት ሲፈለጉ የነበሩ እና በመገናኛ ብዙሀን ጥሪ ከተላለፈላቸው አራት የድርጊቱ ተጠርጣሪዎች መካከል እስካሁን ሦስቱ ተጠርጣሪዎች ከሁለት ወራት በፊት እጃቸውን ለኮሚሽኑ መስጠታቸው ይታወሳል፡፡ በቁጥጥር ስር ባልዋለው አንድ ተጠርጣሪ ላይ የሚደረገው ክትትልም አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን ኮሚሽኑ አመልክቷል፡፡

ግለሰቦቹ በኮልፌ ቀራኒዩ ክፍለ ከተማ በወጣው 53ኛ ዙር የሊዝ ጨረታ ፋሪ የተባለው አካባቢ 250 ካሬ ሜትር ቦታ አሸንፈው ካገኙ በኋላ ቦታው ለግሪን ኤሪያ የተያዘ ነው በሚል ሰበብ ሌላ ተለዋጭ ቦታ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡ በቤቴል አካባቢ በስፋቱም ሆነ በሊዝ ዋጋው ካለፈው የበለጠ ቦታ እንዲያገኙም ተደርጓል፡፡

በቤተል የተሰጣቸው ቦታ 1000 ካሬ ሜትር ሲሆን በካሬ ሜትር የሊዝ ዋጋውም 500 ብር ነው፡፡ የቀድሞው ቦታ ደግሞ 250 ካሬ ሜትር ሲሆን በካሬ ሜትር የሊዝ ዋጋውም 430 ብር እንደነበር ከተጠርጣሪዎቹ ጋር በተያያዘ ያለውን ወንጀል ኮሚሽኑ ገል"ል፡፡

በጋዜጣው ሪፖርተር
 
< Prev   Next >