| "የአባይ ተፋሰስ አገሮች ለጋራ ልማት... |
|
|
| Sunday, 24 February 2008 | |
|
"የአባይ ተፋሰስ አገሮች ለጋራ ልማት ታጥቀው መነሳት አለባቸው"
አቶ አስፋው ዲንጋሞ የውኃ ሐብት ሚኒስትር የአባይ ተፋሰስ አገሮች ለጋራ ልማት ታጥቀው መነሳት እንዳለባቸው የፌዴራል ውኃ ሐብት ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አስፋው ዲንጋም በሁለተኛው የዓባይ ቀን የካቲት 15 ቀን 2000 ዓ.ም በተከበረበት ቀን ባደረጉት ንግግር አሳሰቡ፡፡ ሚኒስትሩ የዓባይን ቀን ምክንያት በማድረግ ባደረጉት ንግግር፣ "የዘንድሮውን የዓባይን ቀን ከሌሎቹ የሚለየው፣ የኢትዮጵያ ሚሌኒየም በዓል በምታከብርበት ዕለት አብሮ መከበሩ ነው "በኢትዮጵያ የሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦች አገራቸውን ለማልማት እንደተነሱ ሁሉ፣ የዓባይ ተፋሰስ አገሮችም ለጋራ ልማት ታጥቀው መነሳት ይገባቸዋል" ብለዋል፡፡ አገራቱ ለሚያከናወኑት የጋራ ልማት መሳካት አሁን በድርድር ላይ የሚገኘው በዓባይ የውኃ አጠቃቀም ላይ የሚኖራቸውን ፍትሐዊ ድርሻ የሚወሰነው፣ የሕጋዊና መዋቅራዊ ማዕቀፍ በፍጥነት ሊረጋገጥ እንደሚገባ አቶ አስፋው አሳስበዋል፡፡ የዓባይ ሁለተኛ ዓመታዊ በዓል በተከበረበት ቀን ዋና ነጥብ ሆኖ የተነሳው በአስሩ የዓባይ ተፋሰስ አገሮች መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር፣ እንዲሁም የዓባይ ተፋሰስ አገራት የጋራ መድረክ፣ የናይል ቤዚን ኢኒሼቲቭ ከተመሠረተ ዘጠኝ ዓመታት ጀምሮ የነበረበትን ችግርና ጥነካሬዎቹን መገምገም መሆኑ ተገል"ል፡፡ ከ1991 (እ.ኤ.አ) ጀምሮ በነበሩት የሥራ ዘመናት ከፍተኛ የሆነ ለውጥ እንደታየ፣ የሽግግር ተቋማት ሥራቸውን በጥሩ ሁኔታ እያካሄዱ መሆኑን የገለፁት የናይል ቤዚን ኢኒሼቲቭ ሥራ አስፈፃሚ ሚስተር ኡዳሴ ንዳይዘዬ ናቸው፡፡ ይሁን እንጅ ሥራ አስፈፃሚው በአሰራር ላይ ችግሮች መኖራቸውን ሳይገልጹ አላለፉም፡፡ የገንዘብ እርዳታ፣ የጋራ ራዕይ ፕሮጄክቶቹንና ውጤቶቻቸውን ወደ ቋሚ ተቋማት የማሸጋገር ሂደት ዘገምተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ናይል ቤዚን ኢኒሼቲቭ እ.ኤ.አ የካቲት 22 ቀን 1999 በቡሩንዲ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጐ፣ ግብፅ፣ ኤርትሪያ፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሩዋንዳ፣ ሱዳን፣ ታንዛኒያና ኡጋንዳ ባደረጉት ስምምነት መመስረቱ ይታወሳል፡፡ ሁለተኛ የዓባይ ቀን የካቲት 14 ቀን 2000 ዓ.ም በተባበሩት መንግሥታት ስብሰባ አዳራሽ በተከበረበት ዕለት ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ ሚኒስትሮችና አምባሳደሮች የዓባይ ሚዲያ ኔት ወርክ አባላት ተገኝተዋል፡፡ በታምሩ ጽጌ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |