Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Friday
Nov 21st
Home arrow Sections arrow ለአዲስ አበባ በየቀኑ የሚቀርበው 230ሺህ ሜትር ኪዩ
ለአዲስ አበባ በየቀኑ የሚቀርበው 230ሺህ ሜትር ኪዩ E-mail
Sunday, 06 January 2008
ለአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ በየቀኑ 230ሺህ ሜትር ኪዩብ የመጠጥ ውሃ እንደሚቀርብ የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የውጭና የሕዝብ ግንኙነት አገልግሎት መምሪያ አስታወቀ፡፡

¨<H¨<U ¾T>Ñ–¨< ŸKÑÇÇ=“ ŸÑð`d ÓÉx‹' ከአቃቂ ከርሰ ምድርና ከተለያዩ ጉድጓዶች መሆኑን የመምሪያው ኃላፊ አቶ ጌትነት ገሠሠ አስረድተዋል፡፡

ሰማንያ ከመቶ ያህሉ ውሃ የሚቀርበው ከለገዳዲ የውሃ ማጠራቀሚያ መሆኑን አቶ ጌትነት አመልክተው የገፈርሳና የለገዳዲ ግድቦች ውሃ የመያዝ አቅማቸውን የማሳደጉ ሥራ በጥሩ ሁኔታ በመካሄድ ላይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ከእነዚህም መካከል የገፈርሳ ግድብን የማሳደግ ሥራ ከሁለት ወር በኋላ እንደሚጠናቀቅ አውስተዋል፡፡ ከለገዳዲ ግድብ ብቻ በየቀኑ የሚቀርበውን 24ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ ወደ 30 ሺህ ሜትር ኪዩብ ከፍ ለማድረግ የሚያስችል ሥራ በመከናወን ላይ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

ከዚህም ሌላ ከፍተኛ የውሃ እጥረት በሚታይባቸውና ሕዝብ በሚበዛባቸው በተለያዩ አካባቢዎች 29 የውሃ ጉድጓዶች በመቆፈር ላይ ሲሆን ሌሎች የ39 ውሃ ጉድጓዶች ቁፋሮ ሥራ ደግሞ ባለፈው ዓመት መጠናቀቁን አቶ ጌትነት ገልፀዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የውሃ እጥረት ሊከሰት የቻለው የሕዝብ ብዛት በመጨመሩ፣ ኢንቨስትመንት በመስፋፋቱና ከፍተኛ የኮንስትራክሽን ሥራዎች በመከናወናቸው የተነሳ አቅርቦትና ፍላጎት ባለመጣጣማቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

 
< Prev   Next >