Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Saturday
Jul 05th
Home arrow Sections arrow የኬንያ ተቃዋሚ ፓርቲ የተቃውሞ...
የኬንያ ተቃዋሚ ፓርቲ የተቃውሞ... Print E-mail
Sunday, 24 February 2008
የኬንያ ተቃዋሚ ፓርቲ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚጠራ አስታወቀ

የኬንያ ተቃዋሚ ፓርቲ ያቀረበው የስልጣን ክፍፍል አማራጭ በአገሪቱ መንግሥት ተቀባይነት የማያገኝ ከሆነ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪ እንደሚጠራ ማስታወቁን አሶሺየትድ ፕሬስ ዘገበ፡፡

የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ራይላ ኦዲንጋ ሰሞኑን እንዳስታወቁት መንግሥት የአገሪቱ ህገመንግስትን በማሻሻል የጠቅላይ ሚኒስትር የስልጣን መንበር የማይፈጠር ከሆነ የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪ ይተላለፋል፡፡

ፕሬዚዳንት ምዋይ ኪባኪ በበኩላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር የስልጣን መንበር ምስረታን ሀሳብ “የማይጠቅም” ሲሉ አጣጥለውታል፡፡ ፕሬዚዳንቱ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች በአገሪቱ የፖለቲካ ስልጣን የሚሰጣቸው መሆኑን ነገር ግን የጠቅላይ ሚኒስትር የስልጣን መዋቅር እንደማይፈጠር ገልፀዋል፡፡

የዳርፉር ስደተኞች ወደ ቻድ መግባት እንዳልቻሉ ተገለፀ

በሺዎች የሚቆጠሩ የዳርፉር ስደተኞች የቻድን ድንበር አቋርጠው ማለፍ አለመቻላቸውን ቢቢሲ የአይን እማኞችን በመጥቀስ ዘገበ፡፡

በአካባቢው የተሰማሩ የእርዳታ ድርጅት ሠራተኞች የሱዳን መንግሥት ስደተኞቹ ወደ ቻድ እንዲያልፉ ማገቱን ገልፀዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቃል አቀባይ አርላ ክሊንተን በአካባቢው ከስምንት ሺ በላይ ተፈናቃዮች እንደሚገኙና ወደ ቻድ እንዳይሄዱ መከልከላቸውን ገልፀዋል፡፡ አርላ ክሊንተን ተፈናቃዮቹ ከሱዳን መንግስት በሚሰነዘረው ጥቃት ጉዳት እንደደረሰባቸውም አስታውቀዋል፡፡

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩሉ በአካባቢው ተፈናቃዮች ስለመኖራቸው እንደማያውቅ ገልፆ በአካባቢው አማጽያንን ብቻ በመለየት ጥቃት መሰንዘሩን አስታውቋል፡፡

የተመድ ዋና ፀሐፊ ባንኪ ሙን የሱዳን መንግሥት በአካባቢው የሰነዘረው መጠነ ሰፊ ጥቃት ሳቢያ ሰላማዊ ሰዎች ሰለባ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ በዚህም የሱዳን መንግሥት እርምጃውን እንዲገታ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የእርዳታ ድርጅት ሠራተኞችና የአይን እማኞች የሱዳን መንግሥት የአየር ኃይል በቅርቡ በአካባቢው በሰነዘረው ጥቃት በትንሹ አንድ መቶ ሰዎች መሞታቸውንና ከአስራ ሁለት ሺ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን ገልፀዋል፡፡

ቡሽ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በላይቤሪያ አጠናቀቁ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ በአምስት የአፍሪካ አገራት ያደረጉትን ጉብኝት በላይቤሪያ አጠናቀቁ፡፡

ፕሬዚዳንቱ በላይቤሪያ ጉብኝታቸው ወቅት አሜሪካ በአፍሪካ ውስጥ የወታደራዊ ጣቢያ ለማቋቋም ጥረት እያደረገች አለመሆኑን ገልፀዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ቡሽ የጉብኝታቸው አላማ ወታደራዊ ጣቢያ ለማቋቋም አለመሆኑን ገልፀዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ የአፍሪካ አገራትን ወታደራዊ አቅም ለማጠናከር አጋዥ የሆነውን አፍሪኮምን ከማቋቋም ያለፈ የአሜሪካ የጦር ኃይል ጣቢያ በአፍሪካ እንደማይቋቋም መግለፃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ፕሬዚዳንቱ በጉብኝታቸው ቤኒን፣ ታንዛኒያ፣ ሩዋንዳ፣ ጋናና ላይቤሪያን መጎብኘታቸው ተገልጿል፡፡

የቱርክ ወታደሮች ሰሜን ኢራቅ ገቡ

የቱርክ ወታደሮች ሰሜናዊ ኢራቅ በመግባት በአካባቢው የሚገኙ የኩርድ አማጽያን ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገባ አመለከተ፡፡

በሺዎች የሚቆጠሩ የቱርክ ወታደሮች በሰሜን ኢራቅ በመሰማራት ከፍተኛ ጥቃት ማድረሳቸው ተዘግቧል፡፡ በዘገባው መሰረት ባለፈው ሐሙስ የኢራቅን ድንበር የተሻገሩት የቱርክ ወታደሮች በሰሜናዊ ኢራቅ የሚገኝ የኩርዶችን ይዞታ ተቆጣጥረዋል፡፡

በዘመቻው ከአስር ሺ በላይ የቱርክ ወታደሮች ተሳትፈዋል፡፡ የአሜሪካ መንግሥት በበኩሉ ቱርክ አሸባሪዎችን የመዋጋት ኃላፊነት አለባት ሲል ድጋፉን ገልጿል፡፡
 
< Prev   Next >