Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow ክቡር ሚኒስትር
ክቡር ሚኒስትር Print E-mail
Sunday, 06 January 2008
- ሃሎ ክቡር ሚኒስትር፡፡
- አለህ እንዴ አንተ ሰውዬ ና፡፡ ሰሞኑን የለህም?
- አዎን ክቡር ሚኒስትር ከአዲስ አበባ ለሳምንት ያህል ወጣ ብዬ ነበር፡፡ አሁንም የገና በዓል ስለደረሰና ያልታሰበ አጣዳፊ ነገር ስላጋጠመኝ እንጅ ለአንድ ሳምንት ያህል ላለመምጣት ፈልጌ ነበር፡፡
- ምን አጣዳፊ ነገር አጋጠመህ?
- በስልክ አይወራም፤ ክቡር ሚኒስትር፡፡ አሁን ልምጣና ላናግርዎት አጣዳፊና አደገኛ ነው፡፡
- ዛሬ አይመቸኝም አትምጣ፡፡

- እዛው ከፍለ ሃገር እያለሁ ለአውደ ዓመት በግም ጤፍም ይዤ መጥቼ ነበር፡፡ ቤት ሄጄ ላስቀምጠው? እኔማ ልምጣና ለወዳጃችን ለሾፌሩ ልስጠው ብዬ ነበር፡፡
- እሺ ና..
ረጤፍና በጉ በሾፌሩ በኩል ቤት ተወሰደ፡፡ ሰውየው እየተጣደፈ ክቡር ሚኒስትሩ ቢሮ ገባሪ
- እንዳው ይቅበሩኝ ክቡር ሚኒስትር፣ እንደተለመደው ይርዱኝ፡፡
- ምን ሆነህ ነው?
- እኔ የምመራው አጠቃላይ የኢትዮጵያ የበላይ ድርጅት እንደሆነ ያውቃሉ፣ ክቡር ሚኒስትር፡፡
- አዎ አውቃለሁ፡፡ እንዴ እዛ እንድትቀመጥ የደገፍኩህ እኔ ራሴ አይደለሁም ወይ፡፡
- ትክክል፤ ክቡር ሚኒስትር አሁን ይርዱኝ፡፡
- ምንድነው ነው የምረዳህ? ምን አጋጠመህ?
- ይኸውልዎ ክቡር ሚኒስትር፣ እኔን ሊያወርዱኝ ጠላቶች እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡
- አንተን ሊያወርዱ?
- አዎን ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ሞተናላ.. አታስብ፡፡ በጭራሽ አትጨነቅ፡፡ ወሬ ነው፡፡
- ይኸውልዎ፤ ክቡር ሚኒስትር፡፡ በየክልሉ ያሉት ማህበራት ለስብሰባና አጠቃላይ ጉባኤ ይጠራልን ብለው ወደ አዲስ አበባ ሰሞኑን ይመጣሉ፡፡
- ከየት ከየት ነው የሚመጡት?
- ከሁሉም ክልሎች ክቡር ሚኒስትር፡፡ ይህ የበላይ ፌዴሬሽን ነው እንጂ በየክልሉ እኮ የክልል ፌዴሬሽኖች አሉ፡፡
- ማን ነው የጠራቸው?
- ክቡር ሚኒስትር እነሱማ ተጠርተው ነው፣ የክልሎች አቅም ለመገንባት ነው የሚሉት፡፡
- በል እስቲ ረጋ በል እና አቅም ግንባታ ሚኒስትር ጠርቷቸው እንደሆን ጠያይቀህ ንገረኝ፡፡
- እሺ ክቡር ሚኒስትር፡፡ አጣርቼ ከሰዓት ልደውል፣ ወይም ልምጣ ኧረ እመጣለሁ ብመጣ ይሻላል፡፡
- እሺ ና፡፡
ረከሰዓት በኋላ ሰውየው እንደገና ክቡር ሚኒስትር ቢሮ መጣሪ
- ክቡር ሚኒስትር መንግሥት ጠርቷቸው አይደለም፡፡ የኔን ቦታ ለመያዝ የፈለጉ ሰዎች ናቸው፡፡ ይጥሩዋቸው እና አንድ ነገር ያድርጉልኝ፡፡
- ምን ላድርግ?
- ክቡር ሚኒስትር፣ እንዳይመጡ ያድርጉልኝ፡፡
- እሺ እደውልላቸዋለሁ፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ ደወሉ ብለህ ግን እንዳታወራ፡፡
- ኧረ በጭራሽ በኔ ይተውት፡፡
- በል ይመጣሉ የሚባሉትን ሰዎች ስልክ ቁጥር ስጠኝ፡፡
ረሰጣቸውሪ
- እስቲ ባናከብረውም እንደ ፈረንጆቹ ..ሃፒ ኒው ይር.. ልበል ብዬ ነው፡፡
- ኧረ ክቡር ሚኒስትር፣ ደህና ነዎት፡፡ እርስዎኮ ቁም ነገረኛ ነዎት፡፡
- የገና ዝግጅት እንዴት ይዞሃል ጃል?
- እንዳንዘጋጅማ አዲስ አበባ በአስቸኳይ እንድትመጡ ተብለን የለ፡፡
- ለምን?
- ለፌዴሬሽኑ ስብሰባ ነዋ፡፡ መሪው ጥሩ አይደሉም፡፡ ክልሎች ሊያወርዷቸው ይፈልጋሉ፡፡
- እንዳትሳሳቱ፡፡
- እንዴት እንዳትሳሳቱ? አልገባኝም፤ ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ማን ነው የጠራችሁ?
- ከዛው ከአዲስ አበባ ነዋ፡፡
- ይህ ሰውየ ለአገር ብዙ የሰራና የሚቆረቆር ነው፡፡
- ኧረ አይመስለኝም፤ ክቡር ሚኒስትር፡፡
- እንዴት አይመስልህም፡፡ ከራሱ ገንዘብ እያመጣ ነው ፌዴረሽኑን የሚደጉመው፡፡
- አይምሰልዎ ክቡር ሚኒስትር፤ እንዳያታልልዎ ብዙ ማስረጃ በእጃችን አለ፡፡
- መንግሥት እስኪጠራችሁ ብትጠብቁ ጥሩ ይመስለኛል፡፡
- አትምጣ እያሉኝ ነው?
- መንግሥት እስኪጠራህ ቆይ ነው የምልህ፡፡
- መንግሥት ነው የጠራኝ፡፡
- ማን የሚሉት መንግሥት?
- የአቅም ግንባታ፡፡
- ብቻ ግለሰቦች እንዳያታልሉህ፤ ብዬ ልመክርህ ፈልጌ ነው፡፡ ለራስህ ያዘው ለማንም አታውራ፡፡
- እሺ ክቡር ሚኒስትር፤ አላወራም፡፡ እመጣለሁ ያልኩትም የመንግሥት መሥሪያ ቤት ፀሐፊ ስለደወለችልኝ ነው እንጂ ራሴ ፈልጌ አይደለም፡፡
- አሁን ግን ገብቶሃል አይደል?
- ኧረ በደንብ ገብቶኛል፡፡ በዓመት በዓል ዋዜማ ወዲህ ወዲያ ማለትም ያስጠላል፡፡
- እሺ ቻው፡፡
- ደህና ይሁኑ ክቡር ሚኒስትር፡፡
ረክቡር ሚኒስትሩ ወዳጃቸው ሰውዬ ጋር ደወሉና ጠሩትሪ
- አንተ፣ አንድ የጠረጠርኩት ነገር አለ፡፡
- ምን ክቡር ሚኒስትር?
- መንግሥት ነው የጠራቸው፡፡ አንድ አምስቱን አነጋገርኳቸው፡፡ መንግሥት ነው የጠራን ብለዋል፡፡
- እኔምኮ እንደገና ሳጣራ መንግሥት እንደጠራቸው አወቅኩ፡፡
- ታዲያ ለምን ደውለህ አልነገርከኝም፡፡
- ልደውልልዎ ስል እርስዎ ቀደሙኝ፡፡   
- አየህ አየህ አሁን ችግሩ እነሱ ከጠሯቸውና እኛ ቅሩ ካልናቸው በእኛ ላይ ያልሆነ ግምት ያሳድራል፡፡
- አይ ክቡር ሚኒስትር፣ እንደውም ያስመሰግነናል እንጅ አያስወቅሰንም፡፡
- እንዴት?
- በአሁኑ ጊዜ የኢንተርኔት ዘመን ነው፡፡  ሃሳብና ቅሬታ ጥያቄ ካላቸው ኢሜይል ያድርጉ የአገርና የህዝብ ባጀት ለምን ይገላሉ፡፡ ከአውሮፕላን ከሆቴል ወጪ ማዳን ግዴታችን ነው መሰለኝ፡፡
- እውነትክን ነውኮ... ቆይ አላስፈላጊ ገንዘብ አታባክኑ ብዬ እደውልላቸዋለሁ፡፡
- ትክክል ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ስልክ ቁጥሮቻቸውን እንደገና ስጠኝ፡፡
- ይኸውኮ፡፡ በነገራችን ላይ ሁለቱ እንኳ ቢመጡም የእኛ ደጋፊዎች ናቸው፡፡ ሌሎቹ ግን በጭራሽ መምጣት የለባቸውም፡፡
- በል በል የጨረስነውን አትደጋግም፡፡
- በቃ፤ እኔ ልሂድ፡፡ ለአውደ ዓመቱ ልዘገጃጅ፡፡ እርስዎ እንደሆነ ሰው ካላስታወሰዎት ስለአውድ ዓመት ብዙ አይጨነቁም፡፡
- ዘንድሮማ በጣም ተጨንቄያለሁ፡፡
- ለምን ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ባለቤቴ መኪና ካልገዛህ ብላኝ ነዋ፡፡
- ውይ ክቡር ሚኒስትር፤ ይህማ ያስደስታል እንጂ ምን ያስጨንቃል፡፡ ባለቤትዎ ደግሞ መኪና ያምርባቸዋል፡፡ ሁል ጊዜ ይህን ሊፍት ባክ ሲነዱ ሳያቸው እናደዳለሁ፡፡ እስከአሁን ዝም ያልኩት፣ እኔ ያልመረጥኩት ቀለም ነው ብለው ቅር እንዳይላቸው ብዬ ነው፡፡
- እሷ ስለቀለም ብዙ ደንታ የላትም ኧረ፡፡
- አለቀ ነገሩ፤ ክቡር ሚኒስትር፡፡
- በኔ በኩል ያለውም ያልቅልሃል፡፡
- የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደዚህ ተደጋግፎ ቢሰራ ኖሮ ይህች አገር የትና የት በደረሰች ነበር፡፡
- ትክክል፡፡ በል ቻው ልደዋውል፡፡
- ቀለሙ ቢጫ ቢሆን አይጠሉትም አይደል፡፡
- እንደውም የሰላምና የፍቅር ምልክት ነው፡፡
- ቻው ክቡር ሚኒስትር፡፡
 ረክቡር ሚኒስትሩ ሊደውሉ ሲሉ ስልክ ተደወለላቸውና አነሱሪ
- ሃሎ ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ሃሎ ማን ልበል? ይቅርታ እሺ ይቅርታ፣ ምን ልታዘዝ ጌታዬ፡፡
- ከናንተ ቢሮ ወደክልል ደውሎ ተሰብሳቢዎችን አትምጡ ያለ አለ ወይ?
- ኧረ የለም፡፡
- ደውለው አትምጡ አሉን ብለው ነገሩና፡፡
- ማን ነው እንደዛ ብሎ የነገራቸው፡፡
- እነሱማ ክቡር ሚኒስትሩ ደውለው እንደዛ አሉን ነው የሚሉት፡፡
- እኔ አትምጡ አላልኩም፡፡ በተቻለ መጠን አላስፈላጊ የትራንስፖርትና የሆቴል ወጪ እንዳይኖር አድርጉ ነው ያልኩት፡፡
- ምን ማለት ነው ይሄ?
- በአጭር ጊዜ የሚጠናቀቅበትን መንገድ ፈልጉ ማለቴ ነው፡፡
- ብቻ ኋላ ራሳቸው ሚኒስትሩ ሲመጡ ራሳቸው ይደውላሉ፡፡ ለጊዜው ግን በራስ ላይ ገመድ ማስገባት እንዳይሆን ማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡ ቻው፡፡
- ቻ-ቻ-ቻቻ-ውውው
ረክቡር ሚኒስትሩ ደንግጠው ሹክክ ብለው ወንበራቸው ላይ ተቀመጡ፡፡ በእጅጉ ደንግጠዋል፡፡ እንደገና ስልክ ተደወለሪ
- ክቡር ሚኒስትር እንኳን ደስ አለን፡፡
- ምን ተገኘ?
- ልክ ከቢሮ እንደወጣሁ ቀጥታ ሄድኩ፡፡ ቢጫው ተገኘ፣ ቆንጆ ቀለም ነው፡፡ ባለቤትዎ እንደሚወዱት እርግጠኛ ነኝ፡፡ ሊብሬና ሌላ ጨርሰው እንዲሰጡኝ አዝዤያለሁ፡፡ በገናው ዋዜማ ነው ..ሰርፕራይዝ.. የምናደርጋቸው፡፡
- እ?
- ሃሎ ክቡር ሚኒስትር፣ ስልኩ ተቋረጠ እንዴ?
- ሃሎ ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ይቅርታ ሰው መጥቶብኝ ነው ኋላ እደውልልሃለሁ፡፡ ላደረከው አመሰግናለሁ፡፡
- ኧረ ገና ትልቅ ፌስታ ነው የምናከብረው፡፡
- ማታ እደውላለሁ፡፡
 ረክቡር ሚኒስትሩ ደብዳቤ ደርሷቸዋል፡፡ እጅግ ፈርተዋል፡፡ አዝነዋል፣ ተናደዋል፡፡ ማታ ከባለቤታቸው ጋር ቁጭ ብለው ዜና ያዳምጣሉ፡፡ ዜናው እንዳለቀ ስልክ ከሰውየው ተደወለላቸውሪ
- ክቡር ሚኒስትር እንዴት ነው ነገሩ፡፡ የፌዴሬሽኑ አመራር አባላት ተባረዋል የሚል ዜና ሰሙት?
- አዎን ሰምቸዋለሁ፡፡ በየቦታው አትምጡ ያልናቸው ሰዎች ሁሉም መጥተው ስብሰባ አድርገው ነበር አሉ፡፡
- እነሱ ናቸው እኔን እንድባረር የወሰኑት፡፡
- ምን አንተ ብቻ፡፡
- ሌላማ ምን ሆነ?
- እኔም ደብዳቤ ደርሶኛል፡፡
- ምን የሚል ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ከቦታየ አነሱኝ፡፡ ሌላ ደብዳቤ እስኪደርስህ ድረስ ቤት ቆይ አሉኝ፡፡ ባነሰ ቋንቋ እረፍት ውሰድ ይላል ደብዳቤው፡፡
- ያው መመለሻ የለም ማለት ነውኮ፤ ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ኧረ ሌላ ጣጣ አይምጣ እንጅ ለራሴ ግድ የለም፡፡ አንተም እኔም ከሰርን ተጠቃሚ የሆነችው እሷ ብቻ ናት፡፡
- እሷ ማን ክቡር ሚኒስትር?
- ምን ክቡር ሚኒስትር ትለኛለህ? እሷ ስል ባለቤቴ ማለቴ ነው፡፡ ስለቢጫው ነው የምነግርህ ያለሁት፡፡
- እ ክቡር ሚኒስትር፣ እሱምኮ ችግር አጋጠመው፡፡
- ምን የሚሉት ችግር?
- መኪናው ቀድሞ ለሌላ የተሸጠ ስለሆነ ሌላ መኪና እስኪመጣ ትጠብቃለህ አሉኝ፡፡
- ሁሉም ከስሯል በለኛ..

 

 
< Prev