| ቢ ኤም አይ ከለንደን ወደ ኢትዮጵያ... |
|
|
| Sunday, 24 February 2008 | |
|
ቢ ኤም አይ ከለንደን ወደ ኢትዮጵያ በረራ ሊጀምር ነው
ቢ.ኤም.አይ የተባለ የእንግሊዝ አየር መንገድ በሳምንት አምስት ቀን ከለንደን ሔስሮው ተርሚናል አንድ ወደ ኢትዮጵያ በረራ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ፡፡ በሳምንት ሰኞ፣ ማክሰኞ፣ ሐሙስ፣ አርብና እሁድ በረራ እንደሚጀምር የተናገሩት የቢ.ኤም.አይ ግሩፕ ዲቪዥን ሥራ አስኪያጅ ኮሊን ካርተር፣ ..በአዲሱ የበረራ መስመራችን አዲስ አበባን ጨምሮ በአፍሪካ፣ መካከለኛው ምስራቅና ማዕከላዊ ኤዥያ በ17 አገሮች በረራ እንጀምራለን.. ብለዋል፡፡ ቢ.ኤም.አይ አዲስ በሚጀምረው የበረራ መስመር በኢትዮጵያ ገበያ ውስጥ ተወዳዳሮ በመሆን ለውጥ ለማምጣት ቆርጦ መነሳቱን ኮሊን ካርተር ተናግረዋል፡፡ አየር መንገዱ አዲስ ከሚጀምረው በረራ ጎን ለጎን አዲስ የጨመረው ነገር፣ የምግብና መጠጥ መስተንግዶ ማሻሻሉን፣ ደንበኞቹን ለማስደሰት በበረራ ወቅት እስከ 22 የሚደርሱ ፊልሞችን ማዘጋጀቱን ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡ በለንደን ሔስሮው በትልቅነቱ ሁለተኛ የሆነው ቢ.ኤም.አይ አውሮፕላን ጣቢያ፣ በአለም ላይ ከሚገኙት ሥራ ከሚበዛባቸው (ቢዚየስት) ጥሩ የበረራ ኔትዎርክ የሚያደርግ መሆኑን ኮሊን ተናግረዋል፡፡ በዓለም ላይ ባለው ጥሩና መልካም ግንኙነት በሳምንት 1..800 በረራዎችን እንደሚያደርግ፣ ደንበኞቹን ባለው ከፍተኛና ሰፊ የግንኙነት መረብ አማካኝነት ከሌሎች ዓለማት ጋር ለማገናኘት እንደሚችል፣ ታዋቂና ተሸላሚ ወደሆነው ኢንዱስትሪ (ዲያመንድ ክለብ) ውስጥ የመግባት እድል እንደሚፈጥርላቸው፣ በዚህም ከፍተኛ በረራ ሲያደርጉ ቅናሽ እንደሚያደርግ፣ ሆቴልና መኪና በማቅረብ ከፍተኛ አገልግሎት እንደሚሰጥ ኮሊን ካርተር አብራርተዋል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ኤርትራውያን ዕርዳታ የሚውል የ400ሺ ዩሮ እርዳታ ተሰጠ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚኖሩ ኤርትራውያን ስደተኞች እርዳታ የሚውል 400ሺ ዩሮ የጣሊያን መንግሥት ለተባበሩት መንግሥታት የከፍተኛ ስደተኞች ኮሚሽን (ዩ ኤን.ኤች.ሲ.አር) በእርዳታ መስጠቱን አስታወቀ፡፡ ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር በትግራይ ክልል በሺመልባ የሚኖሩትን ኤርትራውያንን እየተንከባከበና እየረዳ መሆኑን፣ በያዘው የዓለም አቀፍ ጥበቃና እንክብካቤ ዓላማ መሠረት፣ ለመኖር የሚያስችላቸውን ደረጃውን የጠበቀ የምግብ፣ ውሃ፣ ንጽህና፣ መጠለያ፣ ሕክምናና የአመጋገብ ትምህርትና ለኅብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡ የቱሪስት መስህቦችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የማስተዋወቅ ሥራ እየተሰራ ነው በኢትዮጵያ የሚገኙ የቱሪስት መስህቦችን በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ቋንቋዎች የማስተዋወቅ ሥራዎች እያከናወነ መሆኑን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አሰታወቀ፡፡ በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢው ለሚካሄዱ 25 የሆቴል ግንባታዎች የፈቃድ የምስክር ወረቀት መስጠቱንም አመልክቷል፡፡ ሚሌኒየሙ የኢትዮጵያ የቱሪዝም ሃብት በይበልጥ ለማስተዋወቅ መልካም አጋጣሚ መፍጠሩን፣ በአሁኑ ሰዓት በጃፓን፣ በእንግሊዝ፣ በኔዘርላንድስ፣ በስፔንና በእስራኤል ቅርሶቹን የማስተዋወቅ ሥራ እየተሰራ መሆኑን፣ እ.ኤ.አ እስከ 2008 ማብቂያ ከ440ሺ በላይ ቱሪስቶች ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙ የሚጠበቅ መሆኑንና ከነሐሴ 1999 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ከ150ሺ የሚበልጡ ቱሪስቶች መጎብኘታቸውን ገልጿል፡፡ (ኢዜአ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |