| ፍትህ ወይስ ብልሃት |
|
|
| Sunday, 24 February 2008 | |
|
ለዘንድሮው ምርጫ ዕጩዎችም መራጮችም ተመዝግበዋል ቢባልም፣ ቁጥሩም ሆነ ስሜቱ ቀዝቅሶ ይታያል፡፡ በተለይ በዋና ጉዳዮች ላይ ውይይት፣ ክርክርና ፉክክር የሌለበት ሂደት ሆኗል፡፡ ያለፈውን ምርጫ ተከትሎ ከደረሰው ቀውስ አንፃር ይህ ሁኔታ ብዙም ላያስደንቅ ይችላል፡፡ ግን ሰዉ ፈርቶ በመሸማቀቅ፣ ምን በወጣኝ ልጋለጥ ብሎ፣ ለምንስ ለእስርና ጉዳት ልዳረግ በሚል ትቶት ከሆነ ያሳዝናል፡፡ ወደ ኋላ መመለስ ነውና!
በሌላ በኩል በግልጽ ከመጋፈጥ ይልቅ ሙያ በልብ አድርጌ ለማምንበት አቋምና ይህንኑ ለሚያራምዱ እጩዎች ድምፄን እሰጣለሁ በማለት ድጋፉን በስውሩ ምርጫ ለመግለጽ አድብቶ ከሆነ ብልህነት ነው፡፡ ዴሞክራሲ በረዥም ጊዜ ጥረትና ልምድ የሚገነባ እንደመሆኑ በችኮላ ቢኬድ በጥራትና በብቃት አይተገበርም፡፡ ካለፈው ምርጫ ተምሮና በፈተናውም ሳይደናገጡ፣ አዲስ በሚደርስ ውዥንብርና ተጽዕኖዎችም ሳይደክሙ፣ ለአገርና ለህዝብ የሚጠቅሙ ወገኖችን በጥንቃቄ ለይቶ መምረጥ የዜግነት ግዴታና የዴሞክራሲ መብትም መገለጫ ነው፡፡ ስለሆነም በፍርሃት ሳይሆን በብልሃት፣ ተጠቃሚው ወገን በሚወተውተው ሳይሆን ሃቁን በመተንተን አስተውለን ለዘለቄታ እድገታችን የሚበጀንን መምረጥ ይገባል፡ (ይበይን ተግባሩ፣ ከቦሌ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |