Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Aug 08th
Home arrow Sections arrow መፍትሄ ይፈለግልን
መፍትሄ ይፈለግልን Print E-mail
Sunday, 24 February 2008
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ፋኩልቲ በማታው ክፍለ ጊዜ ለመጀመሪያ ጊዜ የዲግሪ መርሃ ግብር በ1997 ዓ.ም ትምህርታቸውን ጀምረው በፋኩልቲው በ1999 ዓ.ም ለመመረቅ የበቁት ኤዱኬሽናል ማቲማቲክስ ተማሪዎች ብቻ ነበሩ፡፡
ዩኒቨርሲቲው መውሰድ ያለባቸውን ኮርስ ማጠናቀቃቸውን አውቆ እንዲመረቁ ቢያደርግም ጊዜያዊ ዲግሪያቸውንና ስቱደንት ኮፒ እንዳይወስዱ እገዳ ካደረገባቸው ስድስተኛ ወራቸውን ይዘዋል፡፡ የሚጠበቅባቸውን ማንኛውንም ክፍያም ሆነ መውሰድ ያለባቸውን ኮርስ በሙሉ የወሰዱትና የከፈሉት ዩኒቨርሲቲው ባወጣው መመሪያ መሰረት ነው፡፡ የእነዚህ ተማሪዎች የሶስት ዓመታት የጥረታቸው ውጤት በዩኒቨርሲቲው የተሳሳተ አሰራር በእንጥልጥል ላይ የሚገኝ በመሆኑ ሌሎቻችንን በስጋት እንድንማር አድርጎናል፡፡ እንደሚታወቀው ማንኛውም ተማሪ በየዲፓርትመንቱ መውሰድ ያለበትን ኮርስ የሚወስነው ዩኒቨርሲቲው ባወጣው ዝርዝር መመሪያ መሠረት ነው፡፡ ይህ ሆኖ እያለ ዩኒቨርሲቲው አስተምሮ በህጋዊ መንገድ ካስመረቃቸው ተማሪዎች ዳግመኛ ምን እንደሚፈልግ ግልጽ አይደለም፡፡

(ከዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ)
 
< Prev   Next >