Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow ለውጭ ገበያ የሚቀርበው ቡና ሊጨምር ነው
ለውጭ ገበያ የሚቀርበው ቡና ሊጨምር ነው Print E-mail
Sunday, 24 February 2008
ከወጪ ንግድ የተገኘው ገቢ ከዕቅድ በታች ነው

በተያዘው የበጀት ዓመት ማጠናቀቂያ 220..000 ሜትሪክ ቶን ቡና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ መታቀዱ ተገለፀ፡፡ ወደ ወጪ የሚላከውን ቡና መጠን በአንድ ሦስተኛ በማሳደግ ታቅዷል፡፡ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት ከወጪ ንግድ የተገኘው ገቢ ከታቀደው በታች መሆኑ ተገልጿል፡፡
በግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር የወጪ ንግድ ማስፋፊያ ባለሙያ አቶ ጥላሁን ሰለሞን ለሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ እንደገለፁት፣ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የቡናን ምርት በ15 በመቶ ለማሳደግ ታስቧል፡፡ በዚሁ መሠረት በአነስተኛ አቅም የሚያመርቱ አርሶ አደሮችን አቅም በሥልጠና፣ ድጋፍና ምክር ለማሳደግ እየተሠራ ነው፡፡

በዘርፉ የሚሰማሩ ባለሃብቶችን ለማገዝ ኢንቨስት በሚያደርጉት ገንዘብ መጠን ወደ ውጪ ሲልኩ ከወጪ ንግድ ታክስ ነፃ የመሆን እና ከ5 እስከ ሰባት ዓመት የሚደርስ ነፃ የሊዝ ክፍያ ማበረታቻ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

ባለፈው ዓመት 176..000 ቶን ቡና ወደ አሜሪካና አውሮፓ አገሮች የተላከ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከ1ዐዐ በላይ የቡና ላኪዎችና ማህበራት በቡና መላክ ሥራ ላይ መሠማራታቸውም በግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በተያያዘ መልኩ በግማሽ የበጀት ዓመት ከወጪ ንግድ 622.3 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ቢታቀድም የተገኘው 552.7 ሚሊዮን ዶላር መሆኑንና ገቢው ከዕቅዱ 11.2 በመቶ መቀነሱን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ለማግኘት ከታቀደው 296.1 ሚሊዮን ዶላር የተገኘው 270.8 ሚሊዮን ዶላር ነው፡፡ በበጀት ዓመቱ የታቀደን 1.7 ቢሊዮን ዶላር የወጪ ንግድ ገቢ ለማሳካት በሁለተኛው ግማሽ ዓመት ከእቅዱ በላይ መስራት አስፈላጊ ነው፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በተያዘው የበጀት ዓመት ያለውን የወጪ ንግድ ገቢ አስመልክቶ የሰጠው መረጃ እንደሚያመለክተው ከጨርቃ ጨርቅ ንግድ ለማግኘት ከታቀደው 16.5 ሚሊዮን ዶላር የተገኘው 7.5 ሚሊዮን ዶላር ነው፡፡ ከእቅዱ በታች ለተገኘው ገቢ ወደ ሥራ ይገባሉ የተባሉት የአልባሳት ፋብሪካዎች ሥራ ባለመጀመራቸውና በአገር ውስጥ ገበያ ላይ ትኩረት በማድረጋቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡

በአግሮ ኘሮሰሲንግ ዘርፍ ከታቀደው በላይ 16.7 ሚሊዮን ዶላርና ከቆዳና ቆዳ ውጤቶች 50.4 ሚሊዮን ዶላር የተገኘ ሲሆን ከአበባ 43.8 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱንም አመልክቷል፡፡
 
< Prev   Next >