Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow ቴሌ በ6 ወር 1.2 ቢሊዮን ብር...
ቴሌ በ6 ወር 1.2 ቢሊዮን ብር... Print E-mail
Sunday, 24 February 2008
ቴሌ በ6 ወር 1.2 ቢሊዮን ብር ለግንባታና ለማስፋፊያ አዋለ

ትርፉ ከዕቅዱ በታች ነው

የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን በ2000 ግማሽ የበጀት ዓመት ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ልዩ ልዩ የቴሌኮም መሠረተ ልማት አውታር ዝርጋታና ማስፋፊያ ሥራዎችን ማከናወኑን ገል ል፡፡ በተጨማሪም 783.5 ሚሊዮን ብር ለማትረፍ አቅዶ 728.4 ሚሊዮን ብር ማትረፉን አስታውቋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ የግማሽ የበጀት ዓመቱን የሥራ እንቅስቃሴ በሚያሳየው ሪፖርቱ እንደገለፀው በ6 ወራት ወጪ ካደረገው ከ1 ቢሊዮን በላይ ብር ውስጥ በራስ አቅም ለሚሠሩ ፕሮጀክቶች ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲሁም በጥምረት ገንዘብ ምደባ አካሄድ ለሚሠሩ ፕሮጀክቶች ደግሞ ከ1.1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉን ያመለክታል፡፡

በግማሽ የበጀት ዓመቱም የተጣራ ትርፍ 783.5 ሚሊዮን ብር ለማግኘት ታቅዶ እንደነበር የሚያመለክተው ሪፖርቱ 728.4 ሚሊዮን እንደሚደርስ የሚጠበቅና ይህም ከአምናው የበጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ56 በመቶ ወይም የ292 ሚሊዮን ብር እድገት አሳይቷል፡፡

በግማሽ ዓመቱ መጨረሻ የመደበኛ ቴሌፎን ደንበኞች በ3.2 በመቶ፣ የሞባይል ደንበኞች በ50 በመቶና የመልቲ ሚዲያ ደንበኞች በ9.07 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን የሚያመለክተው ሪፖርት በተጠቀሰው ጊዜ ብቻ በሁሉም አገልግሎቶች 661"800 ተጨማሪ ደንበኞች አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን የሚጠቁም ሲሆን ይህም በ2000 በጀት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት መጨረሻ ኮርፖሬሽኑ 920,063 የመደበኛ ቴሌፎን፣ 1,816,946 የሞባይል፣ 28,8000 የዲያል አፕ ኢንተርኔት እንዲሁም 1,130 የመልቲ ሚዲያ ደንበኞችን ለማፍራት እንዳስቻለው ያመለክታል፡፡

የኔትዎርክ አቅምን በተመለከተም የመደበኛ ቴሌፎን ኔትዎርክ 80 በመቶ፣ የሞባይል ኔትዎርክ ደግሞ 79 በመቶ፣ የኢንተርኔት 28 በመቶ ያህሉ ሥራ ላይ መዋሉን ጠቅሶ ወደፊትም ከፍተኛ የሆነ የኔትዎርክ ግንባታ አገልግሎቶች እንደሚከናወን አስታውቋል፡፡

የኮርፖሬሽኑን የፋይናንስ አቅም በተመለከተም በዚሁ ሪፖርት ላይ እንደተጠቀሰው ኮርፖሬሽኑ የፋይናንስ አቅሙን ለማሳደግ በግማሽ ዓመቱ ውስጥ 2.25 ቢሊዮን ብር ለማግኘት ታቅዶ ብር 1.95 ቢሊዮን ተገኝቷል፡፡ ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የብር 550 ሚሊዮን ወይም የ39 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በበጀት ዓመቱ ለመሥራት ካቀዳቸው ዋና ዋና ፕሮጀክቶች ውስጥ በግማሽ የበጀት ዓመቱ ከተከናወኑት ሥራዎች መካከል በብሮድባንድ ኢንተርኔት እና መልቲ ሚዲያ መካከል የነበረውን የማስተላለፍ አቅም ከ100 ሜጋ ባይት ወደ 1 ጊጋ ባይት ለማሳደግ የታቀደው እቅድ አብዛኛው መጠናቀቁንና ጥቂት የማስተካከያ ሥራ ብቻ እንደሚቀረው ያመለክታል፡፡

ለ180 ገጠር ከተሞች የመደበኛ ቴሌፎን ለመትከል ታቅዶ 8ኛ ማዞሪያዎች በመትከል የእቅዱን 114 በመቶ፣ የስልክ ኔት ፕሮጀክት ደግሞ የትምህርት መገናኛ ኤጀንሲ ባለፈው ዓመት በስኩልኔት እንዲገናኙ ከጠየቃቸው 186 ትምህርት ቤቶች ውስጥ ያልተገናኙ 11 ትምህርት ቤቶች በግማሽ ዓመቱ ውስጥ ተገናኝተው ሥራው ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን አስታውቋል፡፡

በጥምር የፋይናንስ ሁኔታ/በቬንደር ፋይናሲንግ በሚሠሩ ፕሮጀክቶች በዜድ.ቲ.ኢ በተባለው የቻይና ኩባንያ ሙሉ ተርንኪ ከሚሠሩ ፕሮጀክቶች ውስጥ ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ባለፈው ዓመት መጨረሻ የተጀመሩ ሥራዎች ውስጥ የ1.2 ሚሊዮን የሞባይል ሚሊኒየም ፕሮጀክት አንዱ እንደነበር አስታውሶ የዚህ ፕሮጀክት ሥራ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቋል ብሏል፡፡

የኦፕቲካል ፋይበር ትራንስሚሽን በባክቦን ኔትዎርክ የመጀመሪያ ክፍል ሥራ ክንውንም ከ2243 ኪ.ሜ ኦፕቲካል ፋይበር ኬብል ውስጥ 1467 ኪ.ሜ ኬብል ሀገር ውስጥ የገባ ሲሆን ዝርጋታው የቁፋሮ ሥራ እየተከናወነ ስለመሆኑንና ሌሎችንም ተግባራቱን በሪፖርቱ ውስጥ አካቷል፡፡

በዳዊት ታዬ
 
< Prev   Next >