Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow ሴቶች ከወንዶች የበለጠ የማስታወስ ችሎታ...
ሴቶች ከወንዶች የበለጠ የማስታወስ ችሎታ... Print E-mail
Sunday, 24 February 2008
ሴቶች ከወንዶች የበለጠ የማስታወስ ችሎታ እንዳላቸው ተረጋገጠ

ሴቶች ከወንዶች የበለጠ የማስታወስ ችሎታ እንዳላቸው በሳይንስ ተረጋገጠ፡፡ የስነ ልቦና ባለሙያዎችን ጥናት ጠቅሶ “ሳይንስ ዴይሊ” እንደገለፀው የሰዎች ፆታ መለያየት የእለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸውን በማስታወስ በኩል የተለያየ ችሎታ እንዲኖራቸው ምክንያት ሆኗል፡፡
የጥናቱ ውጤት ሴቶች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸውን ከወንዶች ይልቅ ረዘም ላለ ጊዜ ማስታወስ እንደሚችሉ ይጠቁማል፡፡

ጥናቱ የተደረገባቸው ሴቶች ቃላትን፣ ቁሳቁሶችን፣ ስዕሎችንና የዕለት ተዕለት ድርጊቶችን ከወንዶች በተሻለ ያስታወሱ ሲሆን ወንዶች ደግሞ በቃላት የማይገለፁ መረጃዎችን ወይም ተምሳሌታዊ ነገሮችን በማስታወስ የተሻሉ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ በተጨማሪም ሴቶች አንዴ ያዩዋቸውን ሰዎች ፊት የማስታወስ ችሎታቸው ከፍ ያለ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ ለዚሁም ምክንያቱ ከወንዶች ይልቅ ሴቶችን ትኩረስ ሰጥተው ስለሚመለከቱ ሊሆን እንደሚችል ጥናቱን ጠቅሶ ዴይሊ ሳይንስ ረግቧል፡፡

ጥናቱን ያካሄዱት የሥነ ልቦና ባለሙያዎች በዘር ከሚተላለፍ የችሎታ መለያየቶች በተጨማሪ በሴቶችና በወንዶች መካከል ስላለው የማስታወስ ችሎታ ልዩነት ምክንያቱ ምን እንደሆነ አለመታወቁን ተናግረዋል፡፡

 
< Prev   Next >