| የመንደር የእንስሳት ሐኪሞች |
|
| Sunday, 06 January 2008 | |
|
በአዲስ አበባ ከተማ የእንስሳት ሕክምናን አገልግሎት ከግል ገቢና ጥቅም ጋር ብቻ በማቆራኘት ሕጋዊ ሰውነት የሌላቸው ግለሰቦች በአገርም ሆነ በሙያ ደረጃ ሕገወጥ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ በአዲስ አበባ በግል የእንስሳት ሐኪሞች ማኅበር አባላት አስታወቁ፡፡
አባላቱ ለሪፖርተር ጋዜጣ ታህሳስ 21 ቀን 2000 ዓ.ም እንዳመለከቱት ሕጋዊ c¨<’ƒ ¾K?L†¨< እነዚሁ ግለሰቦች በኅብረተሰቡ መሃል በመስረግ የተሳሳተና ከእውነት የራቀ ፕሮፖጋንዳ በመንዛት ትክክለኛ ያልሆነና ኢሳይንሳዊ የሆነ የሕክምና አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡ የሕገ ወጦቹም ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጨመር ላይ ይገኛል፡፡ ይህም የእንስሳት በሽታዎች እንዲስፋፉና እንዲጠናከሩ አድርጓል፡፡ ጉዳዩ በሚመለከታቸው ባለሙያዎችና ሐኪሞች ላይም እንቅፋት ፈጥረዋል፡፡ ለኅብረተሰቡም ስጋት ሆነዋል፡፡ ስለሆነም ማንኛውም የእንስሳት ሕክምና የአገልግሎት ተጠቃሚ የኅብረተሰብ ክፍል ለቤት እንስሳት ሕክምና አገልግሎት እንዲደረግለት ሲፈልግ የአገልግሎት ሰጪውን ማንነት የመጠየቅ፣ የዜግነት መብቱ መሆኑን ሊረዳው ይገባል፡፡ ማንኛውም የሕክምና አገልግሎት ሰጪ ግለሰብ ከግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር የተሰጠውን ፈቃድ በተጠየቀበት ሰዓት ለተገልጋዩ ፈቃዱን ማሳየት ይጠበቅበታል፡፡ ከባለሙያዎቹ እንደተላኩ በማስመሰል ለማሳመን የሚሯሯጡና የሚያታልሉ ግለሰቦችን ኅብረተሰቡ እንዳይቀበላቸው፣ እንዲያውም በአቅራቢያው ለሚገኝ ሕጋዊ አካል እንዲያሳውቅ፣ እንዲሁም የቤት እንስሳትን ከጥቃት እንዲከላከሉዋቸውና እንዲጠብቋቸው አባላቱ አሳስበዋል፡፡ የተጠቀሱት ነጥቦች ሁሉ በመንግሥት የሕክምና አገልግሎት ማዕከል የሚሰጠውን የእንስሳት ሕክምና አገልግሎት እንደማያካትት፣ ነገር ግን ባለሙያዎቹ ከመንግሥት ሕክምና ማዕከል ስለመምጣታቸው የሚያረጋግጥ መለያ ለተጠቃሚው ኅብረተሰብ ማሳየት እንደሚገባቸውና ኅብረተሰቡም መጠየቅ እንዳለበት አባላቱ አስረድተዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል ዶክተር ዳንኤል ግርማ የማኅበሩ ፕሬዚዳንት እንዳስገነዘቡት በየመንደሩ የሚዘዋወሩትና ምንም አይነት የሙያ ፈቃድ የሌላቸው ግለሰቦች የሚሰሩት ክትባት ከመስጠት እስከ ማከም የሚደርስ ነው፡፡ ይህንንም የሚያከናውኑት ..አደገኛ የውሻ በሽታ ገብቷልና ውሾቻችሁን አስከትቡ.. የሚል የሀሰት ወሬ በመንዛት ነው፡፡ ኅብረተሰቡም እውነት መስሎት ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለልጆቹና በአጠቃላይ ለቤተሰቦቹ ስለሚያስብ አገልግሎቱን ይጠቀምበታል፡፡ በዚህም ዘላቂያዊ መፍትሄ ያገኘ ይመስለዋል እንጂ በተሰጠው አገልግሎት ላይ እንስሳቱ ምን አይነት መርፌ እንደተወጉ የሚያውቀው ነገር የለም፡፡ አንድ እንስሳ የመዥገር ንክሻ ስለተገኘበት ብቻ መድሃኒት ይሰጣሉ፡፡ እንስሳው በመዥገር ስለተነከሰ ታሟል ለማለት አይቻልም፡፡ ነገር ግን የሕገወጦች በዚህ ይጠቀሙበታል፡፡ አደገኛ በሽታ ሲገባ በፌዴራል ግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር አማካይነት በመገናኛ ብዙሃን እንደሚገለጽ፣ በጋዜጣም እንደሚወጣ፣ መወሰድ የሚገባቸውንም እርምጃዎች ሁሉ በደረጃ እንደሚነገርና በአግባቡ እንደሚፈጽም ዶክተር ዳንኤል አስታውቀዋል፡፡ በድመቶችና በቡችሎች ላይ የቆዳ፣ በመዥገር የሚተላለፍ፣ የውስጥ ጥገኛ በተለይ በቡችሎች በዕድሜ ልዩነት የሚከሰት ቫይረስ ብዙ ጊዜ ይታያሉ፡፡ የውሻ በሽታን ለመከላከል ሲባል በመርዝ የማስወገዱን ተግባር አላምንበትም ያሉት ዶክተር ዳንኤል፣ ከዚህ ይልቅ የመራባት ሃይላቸውን በመቀነስና ክትባት በመስጠት በሽታውን ማስወገድ ባይቻል መቀነስ እንደሚቻል አስረድተዋል፡፡ ዶክተር ሸንቁጥ ተሾመ የማህበሩ አባል በበኩላቸው ..እኛ ሽጋዊ ሆነን በሕጋዊ መንገድ እየሰራን ሌሎቹ ደግሞ በሕገወጥ መንገድ ሥራችንና ሙያችንን እያጠፉ ነው.. ብለዋል፡፡ ይህንንም ችግር ለኢትዮጵያ የእንስሳት ሐኪሞች ማኅበርና ለአዲስ አበባ ግብርና ልማት መምሪያ በደብዳቤ ማሳወቃቸውን አስረድተዋል፡፡ በሕገወጥ መንገድ የሚንቀሳቀሱትም የእንስሳት ሐኪሞች ሊሆኑም ላይሆኑም ይችላሉ፡፡ ግን ሕጋዊ አይደሉም፡፡ ሕጋዊ እስካልሆኑ ድረስ ደግሞ ይህ አይነቱን ሥራ የማከናወን መብት የላቸውም፡፡ እንደዚህ አይነት ሕገወጦች የሚያክሟቸው ውሾች ብዙ ጊዜ በሽተኛ ይሆናሉ፡፡ ..ከተብን.. ይላሉ፡፡ ነገር ግን የከተቧቸው ውሾች አካላቸው መግል ይይዛል፡፡ በውሾቻቸው ላይ ይህ አይነቱ ችግር የደረሰባቸው ሰዎችም ሕክምናውን ተገድደው እንዳደረጉት ይናገራሉ፡፡ ሕገወጦቹ ቤት ለቤት እየሄዱ ..የእብድ ውሻ በሽታ ገብቷል፡፡ ስለሆነም ውሾቻችሁን አስከትቡ፡፡ ይህንን ካልፈፀማችሁ በሕግ ትቀጣላችሁ.. በማለት አንደሚያስፈራሯቸው፣ ዶክተር ሸንቁ..ጥ ተናግረዋል፡፡ ካከሙ በኋላ አንኳን ስለ ሕጋዊነታቸውና የመርፌው ቁጥር ምን እንደሆነ አይጠይቋቸውም፡፡ የከተበውም ማንነቱን የሚገልጽና ማህተም ያለው አድራሻ አይሰጥም፡፡ ..ተከትቧል.. የሚል ወረቀት ብቻ ይሰጧቸዋል፡፡ አጋጣሚ ሆኖ የውሻ በሽታ ቢከሰት ሰዎቹ ውሾቻችን ቀደም ብሎ ተከትበዋል ብለው ይቀመጣሉ፡፡ በዚህም ሳቢያ እያንዳንዱ ቤተሰብ በሙሉ በበሽታው ሊበከል ይችላል፡፡ ስለሆነም ለውሻ በሽታ መስፋፋት መንስኤ ከሆኑት መካከል አንደኛው የሕገወጥ ሐኪሞች እንቅስቃሴ ነው፡፡ ከዶክተር ሸንቁጥ ለመረዳት እንደተቻለው የውሾችን ቁጥር ወይም መራባት መቀነስ የሚቻለው ባለቤት የሌላቸውን ውሾች ይዞ እንዳይወልዱ በማድረግና ክትባት በመስጠት ነው፡፡ በሲራ አካባቢ ያሉ ውሾች ብዙዎቹ ዕድሜያቸው ከአንድ ዓመት በላይ የሚሆኑ ናቸው፡፡ እነሱ በሚወገዱበት ጊዜ ከአንድ ዓመት በፊት የተወለዱት ለመውለድ ይደርሳሉ፡፡ ውሾች በወጣትነት ዕድሜያቸው እስከ 12 ድረስ ሊወልዱ ይችላሉ፡፡ ትላልቅ ውሾች በሚገደሉበት ጊዜ ቡችላ ሆነው በማደግ ላይ ያሉት በቂ ምግብ ይኖራቸዋል፡፡ ስለዚህ ሁልጊዜ ለውጥ የለም፡፡ ይገደላሉ የሚወለደው ቁጥር ግን እየጨመረ ይሄዳል፡፡ መንግሥት መድሃኒት የሚያስመጣው ብዙ ጊዜ በዕርዳታ ወይም ከታክስ ነፃ በሆነ መንገድ ሊሆን ይችላል፡፡ ዋጋውም በጣም አነስተኛ ነው፡፡ ስለሆነም ባለቤት የሌላቸውን ውሾች የማኮላሸት/ የማምከንና የመከተብ ሥራ ሊያካሂድ ይችላል፡፡ የግል እንስሳት ሐኪሞች ማህበር አስፈላጊው እገዛ በማድረግ ሊተባበር እንደሚችል ዶክተር ሸንቁጥ ገልፀዋል፡፡ ዶክተር አብርሃም አየለ የማህበሩ አባል በበኩላቸው እንዳብራሩት ትልቁ ነገር ሕዝቡ ስለ ሕገወጦች እንቅስቃሴ ጉዳይ ጠንቅቆ እንዲያውቅ ማድረግ ነው፡፡ ሕዝቡ በትክክል ስለ ችግሩ ከተረዳ ሕገወጦችን በቀላሉ መንገድ ሊታገላቸውና ሊከላከላቸው የሚቻልበት መንገድ ይኖራል፡፡ ዶክተር ጣፋ ሁንዴ የአዲስ አበባ ከተማ ግብርና መምሪያ የእንስሳት ጤና ቡድን መሪ ስለዚሁ ጉዳይ ተጠይቀው በሰጡት መልስ፣ ..የሙያ ፈቃድ የሌላቸው ሰዎች ይህ አይነቱን ሕገወጥ ተግባር በመፈፀም ላይ መሆናቸውን በወሬ ደረጃ ይሰማል፡፡ ቡድኑም በዚህ ዙሪያ ያደረገው ክትትል የለም፡፡ በዚህ በኩል ኅብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግና መርፌ ወጊዎች ሕጋዊ ለመሆናቸው የሚገልጽ መታወቂያ ማየት ይጠበቅበታል.. ብለዋል፡፡ በታደሰ ገብረማርያም |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |