Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ...
የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ... Print E-mail
Wednesday, 27 February 2008
የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ውዝግብ ቀጥሏል

በቅድስት ሥላሴ መንፈሣዊ ኮሌጅ ተማሪዎችና በኮሌጁ አስተዳዳሪዎች መካከል ከአራት ወር በፊት የተጀመረው ውዝግብ አሁንም ቀጥሏል፡፡ ያቀረብናቸው ጥያቄዎች አልተመለሱልንም የሚሉ ተማሪዎች በአስተዳደሩ በደል እየተፈፀመባቸው እንደሚገኙ ሲገልጹ የኮሌጁ አስተዳደር በበኩሉ የተማሪዎቹ ውንጀላ መሰረተ ቢስ መሆኑን ይናገራል፡፡
የአስተዳደር ብልሹነት፣ የአካዳሚክ ጉዳይ፣ የደመወዝና የምግብ ሁኔታን በሚመለከት ጥያቄ ማቅረባቸውን የሚገልጹት የመንፈሳዊ ኮሌጁ ተማሪዎች እስካሁን ድረስ ምላሽ አለማግኘታውን ተናግረዋል፡፡

የመንፈሳዊ ኮሌጅ የአራተኛ አመት ተማሪ የሆነው ዲያቆን ሰለሞን አሰፋ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፀው ተማሪዎቹ ያቀረቧቸውን ጥያቄዎች የሚያጣራው ገለልተኛ ኮሚቴ ስራውን ከጨረሰ አንድ ወር ከ15 ቀን ቢያልፈውም ምንም የተለወጠ ነገር የለም፡፡

ዲያቆን ሰለሞን እንደሚለው ወቅቱ ተማሪዎች የሁለተኛ ሴሚስተር ትምህርታቸውን የሚጀምሩበት ጊዜ ቢሆንም ትምህርት ለመጀመር የሚያስችል ሁኔታ በኮሌጁ ውስጥ አይታይም፡፡ በኮሌጁ ሕንፃ ውስጥ ለመጠጥ፣ ለገላ መታጠቢያና ለልብስ ማጠቢያ የሚሆን ውሃ ከጠፋ ከሁለት ሳምንት በላይ መሆኑን የጠቆመው ዲያቆን ሰለሞን የኮሌጁ ተማሪዎች ውሃ እንዳያገኙ የተደረገውም በኮሌጁ አስተዳዳሪዎች አማካኝነት መሆኑን ተናግሯል፡፡ በኮሌጁ ህንፃ ውሃ ባለመኖሩም ተማሪዎቹ ለተለያዩ የጤና ችግሮች መዳረጋቸውን አክሎ ገል..ል፡፡

በህንፃው ውስጥ የሚገኙት የተማሪዎቹ መፀዳጃ ቤቶች በውሃ እጦት ምክንያት ባለመጸዳታቸውም ተማሪዎቹ ወደ ዶርማቸው ለመግባት እንደተቸገሩ ተናግረዋል፡፡

ኮሌጁ ሆን ተብሎ ተማሪዎቹን ለማማረር የወንጌል አገልግሎት የሚሰጥበትን አዳራሽ ለሰርግ ሲያከራይ መቆየቱን የገለፀው ሌላው የኮሌጁ ተማሪ በያዝነው ዓመት ኮሌጁ የመመገቢያ ካፍቴሪያውን ለሰርግ በማከራየት ተማሪዎቹ ምግባቸውን ከአዳራሽ ውጪ እንዲመገቡ እንደሚደረግ አስታውቋል፡፡

በኮሌጁ ውስጥ የሚገኙ መፅሐፍትን እንደልብ አለማግኘትም ሌላው ችግር መሆኑ ተገል..ል፡፡ የኮሌጁ ተማሪዎች እንደሚሉት ከሆነ በአሁኑ ሰዓት በተማሪዎችና በኮሌጁ የአስተዳደር ሰራተኞች መካከል የነበረው ግንኙነት ተቋርጧል፡፡

ተፈጠረ የተባለውን ችግር አስመልክተን ያነጋገርናቸው የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ጠባቂ ሊቀ ጳጳስ አባ ጢሞቲወስ የተማሪዎቹ ውንጀላ ሙሉ በሙሉ ውሸት መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በግቢው ውስጥ የውሃ ችግር አለመኖሩን የገለጹት አባ ጢሞቲዎስ ተማሪዎቹ መማር ስለማይፈልጉ ብቻ የተለያዩ ውንጀላዎችን እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል፡፡ አባ ጢሞቲወስ ይህን ይበሉ እንጂ ተማሪዎቹን ለማነጋገር ወደ ተማሪዎቹ ግቢ በሄድንበት ወቅት ከተማሪዎቹ መኖሪያ ህንፃ የሚወጣው መጥፎ ሽታ የሚያስቀርብ ሆኖ አላገኘነውም፡፡

ኮሌጁ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ግብፃውያን፣ ህንዳውያንና አርመናውያን መምህራን ት/ቤቱን ሲመሩት መቆየታቸውን የገለጹት አቡነ ጢሞቲወስ በዚህ ዓመት ሲያስተምሩ የነበሩ ሁለት የህንድ ፕሮፌሰሮች በተማሪዎች ግፊት ምክንያት ስራቸውን እንዲለቁ መደረጉን አመልክተዋል፡፡ ከጥቅምት ወር ጀምረውም እስካሁን ድረስ ተማሪዎቹ ወደ ክፍል አለመግባታቸውን አክለው ገልፀዋል፡፡

..አንድ አዕምሮ ያለው ሰው ምግብ እየተመገበ ለምን ወደ ክፍል አይገባም? ለምን ወደ ጸሎት አይሄድም?.. ያሉት የኮሌጁ የበላይ ጠባቂ ምንም በደል ያልደረሰባቸው የኮሌጁ ተማሪዎች ኮሌጁን ለማዘጋት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም ..ዘጠና ዘጠኝ በመቶ የሚሆኑት የኮሎጄ ተማሪዎች ውሸታሞች ናቸው.. ሲሉ በተማሪዎቹ ላይ ያላቸውን ቅሬታ ገልፀዋል፡፡ ኮሌጁ የተማሪዎቹን ምግብ ቤት ለሰርግ ዝግጅት እየተጠቀመበት ነው በሚል ከተማሪዎቹ የቀረበወ መረጃም ውሸት መሆኑንና ኮሌጁ ምግብ ቤቱን ለሰርግ አከራይቶ እንደማያውቅ ገልጸዋል፡፡

ኮሌጁ ከተመሰረተበት ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ 12 ጊዜ በዲፕሎማ 7 ጊዜ በዲግሪ ተማሪዎች መመረቃቸውን የገለጹት አባ ጢሞቲዎስ ከተመረቁት ተማሪዎች ዘጠና ዘጠኝ በመቶ የሚሆኑት ዲግሪያቸውን ይዘው ወደ ውጭ እንደሚሄዱ አመልክተዋል፡፡

በኃይሌ ሙሉ
 
< Prev   Next >