| በእነአቶ ተስፋዬ ብሩ ላይ ክስ ተመሰረተ |
|
|
| Wednesday, 27 February 2008 | |
|
የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ሥራ አስፈፃሚ በነበሩት በአቶ ተስፋዬ ብሩና በሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ላይ በትናንትናው ዕለት ክስ መሰረተ፡፡
የኮሚሽኑ ዐቃቤ ሕግ በተለያዩ የክስ መዝገቦች ክስ የመሰረተ ሲሆን በትናንትናው ዕለት ባቀረባቸው የክስ መዝገቦች፣ በአንደኛው የክስ መዝገብ 14፣ በሁለተኛው ደግሞ 24 ተጠርጣሪዎችን ከሷል፡፡ የተሰጣቸውን የሥራ ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ያለ አግባብ ሥልጣንን ተጠቅመዋል በማለት ዐቃቤ ክስ የመሰረተባቸው ተጠርጣሪዎች፣ ስምንቱ በከፍተኛ የሥራ ኃላፊነት ላይ እንደነበሩ ዐቃቤ ሕግ በቀረበው የክስ ቻርድ ላይ ጠቅሷል፡፡ ተይዘው ያልቀረቡ ተጠርጣሪዎች እንዳሉ ዐቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው አቤቱታ መሰረት፣ ፎቶግራፋቸው በጋዜጣ እንዲወጣ ቢታዘዝም፣ ዐቃቤ ሕግ “አልደረሰልኝም” በማለቱ በድጋሜ በጋዜጣ እንዲወጣ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡ ለሁሉም ተከሳሾች የክስ ቻርድ ከምርመራ ማስረጃዎቹ ጋር ተሰጥቶ፣ የተከሰሱበትን ክስ መልስ ለማዳመጥና ማስረጃ እንዲያቀርቡ ለመጋቢት 8 እና 10 ቀን 2000 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት ችሎቱ ተመላሽ ሆኗል፡፡ በታምሩ ጽጌ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |