| በቀነኒሳ ሕይወት ዙሪያ የተሰራው... |
|
|
| Wednesday, 27 February 2008 | |
በቀነኒሳ ሕይወት ዙሪያ የተሰራው ፊልም ውዝግብ አስነሳ“ከሦስት ሚሊዮን ብር በላይ ከስሬያለሁ ግን እንዲታይ አልፈልግም” አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በቀነኒሳ ሕይወት ዙሪያ የተሰራው ፊልም ለሕዝብ እይታ እንዳይቀርብ መታገዱን የፊልሙ ፕሮዲውሰር አቶ አብይ ፈቅ ይበሉ ለሪፖርተር ጋዜጣ ገለፁ፡፡ አቶ አብይ እንደገለፁት “ለፍቅር እሮጣለሁ” “ላቄባስ keeps me ሖበቃቃሽቃሸ” በሚል ርዕስ የተጀመረው የፊልም ሥራ ቢጠናቀቅም ለሕዝብ እይታ እንዳይቀርብ አትሌት ቀነኒሳ አግዶታል፡፡ አትሌቱ ፊልሙ “ሕይወቴን ይነካል” በሚል ማገዱን አቶ አብይ ገልፀዋል፡፡ አቶ አብይ የፊልሙን ሥራ ለማከናወን ሁለት ዓመት ገደማ መፍጀቱን ጠቅሰው፤ “የልፋቴን ፍሬ ማየት አልቻልኩም” ብለዋል፡፡ በአትሌት ቀነኒሳ ፈቃድና ከአትሌቱ ጋር በተደረሰ የውል ስምምነት የፊልሙ ሥራ በ1998 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን በሚሊየን የሚቆጠር የፊልሙን ወጪ ሼህ መሀመድ አላሙዲ እና አቶ አብነት ገብረመስቀል በመሸፈን ሥራው መከናወኑ ታውቋል፡፡ በአቶ አብይ ገለፃ መሠረት የፊልሙ ሥራ ዓለም አቀፍ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ ተዘጋጅቷል፡፡ ለዚህም ሥራ ሼህ መሀመድ አላሙዲን በዓለም አቀፍ ደረጃ ፊልም ሥራ የታወቁ ባለሙያዎችን ከሊባኖስ በማስመጣት ተሰርቷል፡፡ የባለ ሙያዎቹን ወጪ ሸራተን አዲስ መሸፈኑ ተገል”ል፡፡ የፊልሙ ፕሮዲውሰር የፊልሙን ፕሮፖዛል እንዲሁም የፊልሙን ስክሪፕት ፊልሙ ይመለከታቸዋል በተባሉ አካላትና በባለሙያዎች መገምገሙን እንዲሁም አትሌቱም የተስማማበት አንደነበር አስታውሰዋል፡፡ በዚህም ፊልሙ እንዲሰራ ከስምምነት ላይ መደረሱን ገልፀዋል፡፡ የፊልሙ ሥራም በብቃት እንዲሁም ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ መዘጋጀቱን የፊልሙ አዘጋጅ ገልፀዋል፡፡ አቶ አብይ በመጨረሻም የፊልሙ ማጠቃለያ ሥራ በባለሙያዎች መገምገሙን አስታውሰው የፖስተር ህትመት መከናወኑን ጠቅሰዋል፡፡ አቶ አብይ ፊልሙ ተጠቃሎ ካለቀ በኋላ በአዲሱ ሚሌኒየም ለሕዝብ እይታ እንደሚቀርብ ከአትሌቱ ጋር ስምምነት ተደርሶ እንደነበር አመልክተዋል፡፡ በመጨረሻም አቶ አብይ “የፊልሙ ሥራ ከተጠናቀቀ በኋላ ሕይወቴን ይነካል የሚል ሰበብ በመፍጠር አትሌቱ እንዳይታይ አድርጓል” ሲሉ ቅሬታቸውን ገልፀዋል፡፡ አቶ አብይ የቀነኒሳ የቀድሞ እጮኛ (ፍቅረኛ) ታሪክ በፊልሙ መካተቱን አውስተው የፊልሙ ሥራ እንዲሁም የአሁኑ የአትሌቱ ሕይወት በየቅሉ ተለያይቶ ሊታይ ይገባል ብለዋል፡፡ የፊልሙ አዘጋጅ በቀነኒሳና በአሁኗ የትዳር ጓደኛው መካከል ነበረ ያሉትን ግንኙነት አስታውሰው፤ ፊልሙ በአትሌቱ የቀድሞ ፍቅረኛ ዙሪያ ማጠንጠኑ በመካከላቸው ያለውን ግንኙነት ሊያሻክር ይችላል የሚል ፍራቻ መፍጠሩን ጠቁመዋል፡፡ የፊልሙ አዘጋጅ “ከሁለት ዓመት በላይ የለፋሁበት መሆኑንና በውሉ መሠረት ከፊልሙ ሽያጭና ከስፖንሰሮች የሚገኝ ገቢ እንዲሁም ቀሪ ክፍያ ይቀረኛል” ሲሉ ውል መጣሱን አመልክተዋል፡፡ አዘጋጁ ከፊልሙ ሥራ ሊያገኙት የነበረው መልካም ዝናም እንደቀረባቸው ገልፀዋል፡፡ በማያያዝም አዘጋጁ የፊልሙ ሥራን በተመለከተ የውል ስምምነት ሲካሄድ በምስክርነት የተገኙት ዶ/ር በዛብህ ወልዴ፣ ሻምበል ቶሎሳ ቆቱ፣ አቶ ተቀደ ማሞን ጨምሮ በአትሌቱ ወንድም ታሪኩ በቀለና በሌሎች ሰዎች ጉዳይ በሽምግልና እንዲፈታ ያደረጉት ጥረት በአትሌቱ እምቢተኝነት መፍትሔ አለማግኘቱን አሳውቀዋል፡፡ አቶ አብይ “አትሌቱ ታዋቂነቱን ተጠቅሞ ጫና፣ ማስፈራራት፣ ዛቻ እያካሄደብኝ ነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ጉደዩን በማስመልከት አትሌት ቀነኒሳ በቀለን አነጋግረነው የሰጠንን ምላሽ በቃለ መጠይቅ እንዳናወጣ በመጠየቁ ሙሉ በሙሉ ከማተም ተቆጥበናል፡፡ በጥቅሉ በፊልሙ ከሶስት ሚሊዮን ብር በላይ መክሰሩንና ፊልሙ ሲጠናቀቅ ደረጃውን የጠበቀ ባለመሆኑ እንዳይታይ ማገዱን አትሌቱ ጠቁሟል፡፡ አያይዞም የፊልሙ ይዘት ከሟች ፍቅረኛውም ሆነ ከትዳር ሕይወታቸው ጋር ግንኙነት እንደሌለው አስታውቋል፡፡ አትሌት ቀነኒሳ በጉዳዩ ዙሪያ ዝርዝር አስተያየት ከሰጠ በኋላ “በሚዲያ እንዲወጣ አልፈልግም በማለት ጥያቄ ሲያቀርቡ ዝግጅት ክፍሉ ድረስ በምጣት ነው፡፡ በዚሁ እለት አትሌቱ ዝግጅት ክፍላችን ተገኝቶ ስለፊልሙ የሰጠው መረጃ እንዳይፃፍ በማስፈራራትና በዛቻ አሳስቧል፡፡ በተሾመ ንቁ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |