Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow ከወርቅ ጋር በተያያዘ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ...
ከወርቅ ጋር በተያያዘ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ... Print E-mail
Wednesday, 27 February 2008
ከወርቅ ጋር በተያያዘ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ ቺፍ ጂኦሎጂስት ታሰሩ

በኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ቺፍ ጆኦሎጂስት አቶ አመንቲ አብርሃም ከወርቅ ጋር በተያያዘ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አደረጋቸው፡፡
የአይን እማኞች ለሪፖርተር እንደገለፁት በጂኦሎጂካል ሰርቬይ በምክትል ኃላፊነት ደረጃ የሚሰሩት አቶ አመንቲ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ባለፈው ረቡዕ ቢሯቸው በሥራ ላይ እያሉ ነው፡፡

የፌደራል ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከወርቅ ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ በጥምረት ከፌደራል ፖሊስና ከዋናው ኦዲተር ጋር እየሰራ ባለው ሥራ ቀደም ሲል ከጂኦሎጂካል ላብራቶሪ ሶስት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉ አይዘነጋም፡፡

በዚሁ መሠረት ከጂኦሎጂካል ላብራቶሪ ኃላፊው፣ ምክትላቸውና አንድ ኬሚስት በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል፡፡

የፌደራል ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ለምርመራ ሥራው ይረዳው ዘንድ ከላብራቶሪ በተለያዩ ወቅት ሙያዊ አስተያየት በመጠየቅ መረጃ ሲያሰባስብ እንደነበርም ከዜናው ምንጮች ለመረዳት ተችሏል፡፡

ከወርቅ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪዎች ከብሄራዊ ባንክ፣ ከፖሊስ፣ ነጋዴዎችና አበሮቻቸው በተለያዩ ጊዜያት በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የሚታወቅ ሲሆን ፖሊስ ከወንጀሉ ጋር በተያያዘ ተፈላጊ ያላቸውን ለህዝብ ይፋ በማድረግ ድጋፍ መጠየቁም አይዘነጋም፡፡

በአሰግድ ተፈራ
 
< Prev   Next >