Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 28th
Home arrow Sections arrow ልማት ባንክ ብሄራዊ ባንክን ኮነነ
ልማት ባንክ ብሄራዊ ባንክን ኮነነ Print E-mail
Wednesday, 27 February 2008
Imageከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ እዳ አልሰበሰበም

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አጠቃላይ ካበደረው ብድር ውስጥ ከ1.5 ቢሊዮን ብር ያልተከፈለ ወቅቱ ያለፈበት ገንዘብ እንዳልተመለሰለት አስታወቀ፡፡ ልማት ባንክ ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ ከስሯል በሚል የተሰራጨው ዜና ከእውነት የራቀ መሆኑን ባንኩን በመኮነን ገለፀ፡፡ “ብሄራዊ ባንክን” ኦዲተር አይደለህም” ብሎታል፡፡
የልማት ባንክ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዳርጌ በርኬሳ ይህንን የገለፁት ከሁለት ሳምንት በፊት ባንኩን በተመለከተ የተዘገበውን ሲያስተባብሉ ነው፡፡ ኃላፊው በመግለጫቸው የብሄራዊ ባንክ ባለሙያዎች በሰጡት አስተያየት ማዘናቸውን ገልፀዋል፡፡

ባንኩ በአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ፕላኑ መሰረት ባለፈው ዓመት 2.5 ቢሊዮን ብር ለማበደር እቅድ ቢይዝም ከእቅድ በላይ 3 ቢሊዮን ብር ማበደሩን አቶ ዳርጌ አስታውቀዋል፡፡

የተከፈለ 1.9 ቢሊዮን፣ አጠቃላይ ካፒታል 3 ቢሊዮን ያለው ልማት ባንክ ባለው ካፒታል መጠን እስከ 12 ቢሊዮን ብር ተበድሮ ማበደር እንደሚችል የጠቆሙት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው “የብሄራዊ ባንክ ባለሙያ ተብዮዎች እንደሚሉት ሳይሆን ልማት ባንክ አትርፏል” ሲሉ በባንኩ ላይ የተሰነዘረውን አስተያየት አጣጥለውታል፡፡ “ከዚህም በላይ” ይላሉ ኃላፊው “ከዚህም በላይ ብሄራዊ ባንክ በአዋጅ ከተሰጠው ስልጣን ውጪ የኦዲተር ኦዲተር የሚሆንበት አሠራር ስለባንካችን ከምናውቀው በላይ ሊነገረን መሞከሩ አስገራሚ ነው” ብለዋል፡፡

ልማት ባንክ እንደ ንግድ ባንክ ለትርፍ ብቻ አይሰራም፡፡ በዚህ የስራ ባህሪው የተጠራቀሙ ያልተከፈሉ ወለዶች አሉ፡፡ ከአጠቃላይ ባንኩ ካበደረው 30 ከመቶ ያልተከፈለ (ያልተመለሰ) ውዝፍ ብር አለ፡፡ ውዝፍ አለ ማለት ግን እስከመጨረሻው አይከፈልም ማለት አይደለም ያሉት ኃላፊው ያልተከፈለውን ውዝፍ ብር በማስያዣነት በተያዘው ንብረት ይተካል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እዳ ያለባቸውን ድርጅቶች ፕሮጀክታቸውን በማከም ከችግራቸው እንዲወጡ ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል ብለዋል፡፡

ብድር ሲሰጥ ፕሮጀክቱ እዳውን በተቀመጠለት መንገድ መክፈል እንዲችል ስምምነት አለ፡፡ ፕሮጀክቱን አስታመነው ከእዳ መውጣት ካልቻለ ይሸጣል፡፡ በአዲስ አበባ ለብድር በማስያዣነት ከተያዘ ንብረቶች ከሚፈለገው እዳ በላይ የሚሸጥበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ በትንንሽ ከተሞች ተበድረው የተወሰደው ገንዘብና በእዳ የተያዘው ንብረት ሲሸጥ ዝቅ የሚልበት ሁኔታ አለ፡፡ ይህ ማለት ግን ባንኩ ይከስራል ማለት አይደለም በማለት የብሄራዊ ባንክን አስተያየት በመቃወም አቶ ዳርጌ ተናግረዋል፡፡

“በርካታ ተበድረው ያልከፈሉ ድርጅቶች አሉ፡፡ ባንኩ እንደስሙ ልማትን ቅድሚያ አጀንዳው ማድረጉ ሊዘነጋ አይገባም፡፡ ፕሮጀክቶች ችግር ባጋጠማቸው ቁጥር ተነስተን እንሽጥ የማንለው ለዚህ ነው፡፡ ለምሳሌ የመንግሥትን የልማት አቅጣጫ ተከትለው፣ ለባንኩ ወለድ የሚያስገኙ፣ ለአገሪቱ የሥራ እድል የሚፈጥሩና ፕሮጀክቶችን እንንከባከባለን” ያሉት አቶ ዳርጌ ብሔራዊ ባንክ ባለሙያዎች የሰጡት አስተያየት የልማት ባንክን ዋንኛ አጀንዳ ያላገናዘብ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡  

በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ለውጥ፣ በተለያዩ የዋጋ ጥረቶች፣ በተለያዩ የውስጥና  የውጭ ችግሮች በውላቸው መሰረት መክፈል ያልቻሉ ድርጅቶች ምንጊዜም መክፈል አይችሉም ማለት አይደለም፡፡ በሂደት ሁኔታዎች ተመቻችቶላቸው እዳቸውን የከፈሉና እየከፈሉ ያሉ ድርጅቶች የመኖራቸውን ያህል ከገቡበት ችግ መውጣት ያቃታቸውም እንዳሉ ኃላፊው አልሸሸጉም፡፡

ለምሳሌ መሰቦ ሲሚንቶ 622 ሚሊዮን ብር ብድር ነበረበት፡፡ ከአራትና አምስት ዓመት በፊት የገበያ ችግር እንደነበረበትና ብድሩን የመክፈል ችግር እንዳጋጠመው ያስታወሱት አቶ ዳርጌ በብሄራዊ ባንክ እንዲህ ያለውን አጋጣሚ “ሊከፈል የማይችል ብድር (Loss loan) ነው” መጠባበቂያ ገንዘብ ይያዝለት ይላል፡፡ በዚህም ምክንያት መጠባበቂያ ገንዘብ ማግኘት ሲገባው ልማት ባንክ ይህንን አላደረገም በሚል ብሄራዊ ባንክ ይተቻል፡፡ ልማት ባንክ ግን ከዚህ በተቃራኒ ፋብሪካው የገበያ ችግሩን ሲቀርፍ እዳውን ይከፍላል የሚል እምነት ስለነበረውና ከዓላማው አንፃር ማስታመምን  እንደ መረጠ አቶ ዳርጌ ገልፀዋል፡፡ በዚሁ መሰረት መሶበ ሲሚንቶ ከ1999 ዓ.ም የበጀት ዓመት መክፈያ ጊዜው በፊት 46 ሚሊዮን ብር ለመክፈል መቻሉንም አመልክተዋል፡፡

የአገዋንና አውሮፓ አገሮች የሰጡትን የገበያ እድል ለመጠቀም 18 የአልባሳት ፋብሪካዎች ብድር ቢወስዱም ተወዳዳሪ ሆነው ብድር በመመለስ ሂደት ላይ ያሉት ከ5 እንደማይበልጡ ተናግረው በዚህም ተመሳሳይ ሂደት ሊኖር እንደሚችል ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡

ብሄራዊ ባንክ ባልተመለሱ (የተበላሹ ብድሮች) ምትክ መጠባበቂያ 715 ሚሊዮን ብር መያዝ እንደነበረብን አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡ እኛም ተግባራዊ እያደረግን ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ግን ባንኩ በተለያዩ የብድር ስህተቶች እንደከሰረ አድርጎ መግለፁ ፍጹም ተቀባይነት እንደሌለው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡

ሌሎችም በተመሳሳይ ሁኔታ ችግር የገጠማቸው ድርጅቶች በውሉ መሰረት መክፈል ባለመቻላቸው መጠባበቂያ ገንዘብ መያዙ አግባብ ቢሆንም ልማት ባንክ ማትረፉንና መክሰሩን ብሄራዊ ባንክ ሊነግረው እንደማይገባ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አፅንኦት ሰጥተው ገልፀዋል፡፡

“የአንድ ድርጅት ትርፍና ኪሳራ የሚገለፀው በራሱ በድርጅቱና ነፃ በሆኑ በኦዲተር ብቻ ነው” የሚሉት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ብሄራዊ ባንክ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ልማት ባንክ በተሰጠው ፈቃድ መሰረት መስራቱን፣ ፖሊሲውን ተግባራዊ ማድረጉን ከመቆጣጠር ውጪ ሌላ ተግባር ማከናወን እንደማይችል አስረድተዋል፡፡

“ብሄራዊ ባንክ ተቆጣጣሪ (ሪጉላቶር) እንጂ ኦዲተር አይደለም” ባለድርሻ በመሆኑ ኦዲት መደረግ አይችልም በማለት አቶ ዳርጌ ብሄራዊ ባንክ ካለው የስራ ድርሻ ውጪ አስተያየት መስጠቱ ለወደፊቱ መደገም እንደሌለበት አመልክተዋል፡፡
 
ልማት ባንክ ላለፉት ሦስት ዓመታት 28፣ 32 እና 41 ሚሊዮን ብር ማትረፉን ያመለከቱት ኃላፊው ኪሳራ ማለት የገቢና የወጪ ልዩነት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ አያይዘውም በዚህ መሰረታዊ የሂሳብ አሰራር መርህ መሰረት ልማት ባንክ ማትረፉን ማኔጅመንቱ አረጋግጦ ለኤክስተርናል ኦዲት ለውጪ ሂሳብ መርማሪዎች (ኤክስተርናል ኦዲተሮች፣ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን በመደባቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ባንኩ ማትረፉ መረጋገጡን አስረድተዋል፡፡  

በአሰግድ ተፈራ
 
< Prev   Next >