Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow ዲያስፖራዎች ፀረ-ኢትዮጵያ እንቅስቃሴዎችን እንዲ
ዲያስፖራዎች ፀረ-ኢትዮጵያ እንቅስቃሴዎችን እንዲ Print E-mail
Sunday, 06 January 2008
በዲያስፖራ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በኢትዮጵያ ልማትና ዴሞክራሲ ግንባታ ላይ የተቃጡ ..እንደ ኤች አር 2003.. ያሉ ድርጊቶችን ሊቃወሙ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት በዲያስፖራ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የብሔር ብሔረሰቦችን ቀን በተለያዩ አገራት ሲያከብሩ በተለይ በካናዳ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ..ኤች አር 2003.. ሕግ J•  ”ÇÃ¨× የተቻላቸውን ለማድረግ ቃል መግባታቸውን ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ጠቅሷል፡፡

በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የብሔር ብሔረሰቦችን ቀን ሲያከብሩ የተገኙት በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ጌታቸው ሀሙሳ ኢትዮጵያውያንና በመላው ዓለም ያሉ የአገሪቱ ወዳጆች በኢትዮጵያ ላይ የሚቃጡ ፀረ-ሰላም ድርጊቶችንና እየተከናወነ ያለውን የዴሞክራሲ ግንባታ የሚያደናቅፉ ሁነቶችን እንዲቃወሙ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

አምባሳደሩ አክለውም እንደ ኤች አር 2003 ያሉትን በኢትዮጵያ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ህጎችን መቃወም እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

በካናዳና አካባቢዋ የሚኖሩ የበዓሉ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ኤች አር 2003 የተሰኘውን ረቂቅ ተቃውመው ተግባራዊ እንዳይሆን የተቻላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

በካናዳ የተከበረውን በዓል ያዘጋጀው ከተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች የተውጣጣ አባላት ያሉት ኮሚቴ መሆኑን ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አመልክቷል፡፡

በሌላ በኩል የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በጀርመን ፍራንክፈርት ሲከበር የብሔረሰቦች ራስን በራስ ማስተዳደር መቻልና በቋንቋቸው እንዲጠቀሙ መደረጉ በአገሪቱ ሰላም ለማስፈን እና የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ያለውን ጠቀሜታ በተመለከተ በጀርመን የኢትዮጵያ ዋና ቆንሲል ወርቁ ኤፍጌ ገለፃ አድርገዋል፡፡

በተመሳሳይ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በኩዌት ሲከበር በኩዌት የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጉዳይ አስፈፃሚ ተወካይ አዲስ ድልነሳ የብሔር ብሔረሰቦች ቀንን የሚያከብሩት ህገ መንግስቱ የፀደቀበትን ታሪካዊ ቀን ለማስታወስ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በዲያስፖራ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአብዛኛው በመረጃ እጥረት ውስጥ ያሉ፣ በአገራቸው ስለሚካሄደው እንቅስቃሴ ትክክለኛ ዕውቀት የሌላቸው መሆኑ በተደጋጋሚ ከመዘገቡ አንፃር በዲያስፖራ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የብሔር ብሔረሰቦች ቀንም ይሁን ሌሎች ክብረ-በዓሎችን ምክንያት በማድረግ መሰባሰባቸው የመረጃ ማሰራጫ መንገድ ተደርጎ ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል ነው፡፡ በዚህ ረገድ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሥር የተቋቋመው በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጉዳይን የሚመለከተው ክፍልም የተቋቋመበት ዓላማ አንዱ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡

ይህ ክፍል በዝርዝር ከተቀመጡ ዓላማዎችና ተግባራቱ አንፃር ብዙ ተንቀሳቅሷል ለማለት አያስደፍርም፡፡ አልያም የተሻለ ቢንቀሳቀስ በዲያስፖራ ያለውን ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊ የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግርን እውን ለማድረግ እንዲቻል ማስተባበር በተቻለ ነበር፡፡

በተደጋጋሚ እንደተገለፀው ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎችን አምጥቶ በአገራቸው የማሰራት ሁኔታ አገሪቱ ያለባት በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠነ የሰው ኃይል ችግር ማስወገድ ካለው ጠቀሜታ አንፃር ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ነው፡፡

በየአገራቱ ባሉ ኤምባሲዎች በኩል በዲያስፖራ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በሚመለከት አገራቸው ተመልሰው ሊሰሩ የሚፈልጉትን በመለየትና መረጃውን በአገር ውስጥ ጠቀሜታ የሚውልበትን መንገድ ማመቻቸትም በሚኒስቴሩ ሥር ሊከናወን የሚችል ተግባር ነው፡፡

ተገቢው መረጃ ከተሰጠና የቅስቀሳ ተግባር ከተከናወነ ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን በአገራቸው አስተዋጽኦ ለማበርከትም ሆነ መጥተው ያለውን ሁኔታ ለማየት ዝግጁ መሆናቸው የሐረር አንድ ሺህኛ ዓመት በተከበረበት ወቅት ከመጣው የዲያስፖራ ብዛት ማወቅ ይቻላል፡፡ በየኤምባሲው በኩል በተደጉ እንቅስቃሴዎች ብቻ ሳይሆን በየአገራቱ በተንቀሳቀሰ አንድ ቡድን አማካኝነት ውጤቱ ሊገኝ ችሏል፡፡ 

በአገር ውስጥ የዲያስፖራ ኤክስፐርትነት የሚፈልጉ ተቋማትን በተመለከተ የትኞቹ ሚኒስትሮች ምን ያህል ባለሙያ፣ በምን በምን ዘርፎች የሚለውን ለይተው በውጪ በሚገኙ ኤምባሲዎች በመስጠት /እስከ ዛሬ አልጀመሩ እንደሆነ/ ክፍተቱን ለመሙላት መስራት ይገባቸዋል፡፡ 

በጋዜጣው ሪፖርተር

 
< Prev