| በሶማሊያ ግጭት ተቀሰቀሰ |
|
|
| Wednesday, 27 February 2008 | |
|
የሶማሊያ አክራሪ የእስልምና ቡድን ከአገሪቱ መንግስት ጋር በአገሪቱ ደቡባዊ ክፍል ሰሞኑን ግጭት መፍጠራቸውን ቢቢሲ ከሥፍራው ዘገበ፡፡
አማጽያኑ ከመንግሥት ጋር ባደረጉት ግጭት ከዘጠኝ በላይ ወታደሮችን መግደላቸውን ሲገልፁ መንግሥት በበኩሉ የአማጽያኑን ጥቃት መመከቱን አስታውቋል፡፡ በዲንሶር ከተማ በተካሄደው በዚሁ ግጭት ከተማዋን በውል የሚያስተዳድር አካል እንደሌለ ዘገባው አመልክቷል፡፡ የአማጽያኑ ቡድን ቃል አቀባይ ሙክታር አሊ ሮቦ "ወታደሮቻችን የመንግስት ወታደሮችን ከከተማዋ አስወጥተዋል" ሲሉ ማሸነፋቸውን አሳውቀዋል፡፡ ግጭቱን አስመልክቶ የሶማሊያ መንግሥት ባለስልጣናት አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ ማዳጋስካር በአውሎ ንፋስ ተመታች በማዳጋስካር ደሴት ሰሞኑን በተነሳው የአውሎ ንፋስ አደጋ ከአንድ መቶ አርባ አምስት ሺ በላይ ሰዎች ሲፈናቀሉ አርባ አራት ሰዎች መሞታቸውን የአሶሲየትድ ፕሬስ ዘገባ አመለከተ፡፡ ባለፈው እሁድ የተነሳው የአውሎ ንፋስ አደጋ በርካታ የአገሪቱ መንደሮችን ማውደሙ ተገልጿል፡፡ ከአውሎ ንፋሱ አደጋ ጋር በተያያዘ በደሴቱ ላይ የኮሌራ ወረርሽኝ መከሰቱ ተጠቁሟል፡፡ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጀነራል ማርኬል ራጂቮ "ሁኔታው አሳሳቢ ነው፡፡ በርካታ መንደሮች ወድመዋል፤ ሰዎች መጠለያ አልባ ሆነዋል" ሲሉ ገልፀዋል፡፡ ሚኒስትሩ የአለም አቀፉ ማኅበረሰብ እርዳታ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ብሌር ለሩዋንዳ የኢኮኖሚ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገለፁ የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቶኒ ብሌር ሩዋንዳ የግል ኢንቨስትመንት በአገሪቱ እንዲስፋፋ የምታደርገውን ጥረት እንደሚደግፉ ማስታወቃቸውን ቢቢሲ ዘገበ፡፡ በዘገባው መሠረት ብሌር ሰሞኑን በሩዋንዳ ባደረጉት ጉብኝት በአገሪቱ በመካሄድ ላይ ያለውን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ማድነቃቸው ታውቋል፡፡ በዚህም የግል ባለሃብቶች በአገሪቱ ኢንቨስትመንት ውስጥ እንዲሳተፉ በምታደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳታፊ እንደሚሆኑ ገልፀዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ1994 በሩዋንዳ በተካሄደው የዘር ማጥፋት ግጭት ወዲህ የውጭ ኢንቨስትሮች በአገሪቱ ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ውስጥ የነበራቸው ተሳትፎ ቀንሷል፡፡ ይህንን ተጽዕኖ ለማጥፋት የሚካሄደውን እንቅስቃሴ ብሌር የሚደግፉ መሆኑንና በአለም ደረጃ ታዋቂ የሆኑ ኢንቨስተሮችን በማነጋገር በአገሪቱ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ ለፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ቃል ገብተዋል፡፡ የጋዛ ነዋሪዎች በእስራኤል ላይ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ በሺዎች የሚቆጠሩ የጋዛ ነዋሪዎች እስራኤል የጋዛን መተላለፊያ በመዝጋቷ የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄዳቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ከስፍራው ያሰራጨው ዘገባ አመለከተ፡፡ በተቃውሞ ሰልፉ ከሀምሳ ሺ በላይ የጋዛ ነዋሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ከራፋ ከተማ እስከ ቤተ ሀኖን ድረስ በተደረገው ሰልፍ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡ የሰልፉ ተሳታፊዎች እጅ ለእጅ በመያያዝ አርባ ኪሎ ሜትር "የሰው ሰንሰለት" በመስራት የተቃውሞ ትዕይንት አካሂደዋል፡፡ የእስራኤል መንግሥት የተቃውሞ ሰልፉ ወደ ግጭት ካመራ ሀማስ ተጠያቂ እንደሚሆን አሳስቧል፡፡ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታዚፕ ሊቪኒ እንዲሁም የመከላከያ ሚኒስትር ኢሁድ ባራክ በጋራ በሰጡት መግለጫ ተቃውሞ ሰልፍ በጋዛ ውስጥ ማድረግ እንደሚቻልና ወደ እስራኤል ድንበር ለመሻገር በሚደረግ ሙከራ ለሚደረሰው ጥፋት ሀማስ ተጠያቂ እንደሆነ አሳውቀዋል፡፡ የጋዛን መተላለፊያ መዝጋት ለእስራኤል ህልውና ሲባል አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |