| ካንትሪ ትሬዲንግ የአኪራ ቴሌቪዥኖችን... |
|
|
| Wednesday, 27 February 2008 | |
|
ካንትሪ ትሬዲንግ የአኪራ ቴሌቪዥኖችን ሊገጣጥም ነው
አኪራ በመባል የሚታወቀውን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በወኪልነት ላለፉት አስር ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ ሲያከፋፍል የቆየው ካንትሪ ትሬዲንግ የአኪራ ቴሌቪዥን መገጣጠሚያ ፋብሪካ ሊገነባ መሆኑን አስታወቀ፡፡ የካንትሪ ትሬዲንግ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ቢኒያም ብርሃነ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት፣ በወር ከ3 እስከ 4 ሺህ ቴሌቪዥኖችን ለማምረት የሚያስችለውን መገጣጠሚያ ፋብሪካ ሥራ ለማስጀመር የሚያስችለው የመሳሪያዎች ግዥ ለማከናወን ከዓለም አቀፉ የአኪራ ኩባንያ ጋር ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ፋብሪካው ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ ለዚህ የሚሆን በጀት መያዙን ያመለከቱት አቶ ቢኒያም ለፋብሪካው የሚሆኑትን መሣሪያዎች የሚተከሉበት ህንፃ ግንባታ ሃና ማሪያም ተብሎ በሚጠራው ቦታ መገንባቱንም አስታውቀዋል፡፡ ፋብሪካው ሥራ ሲጀምር ለ1500 ሰዎች የሥራ እድል እንደሚፈጥርና ምርቱንም በተለይ ለምሥራቅ አፍሪካ አገሮች እንደሚላክ ተጠቁሟል፡፡ ካንትሪ ትሬዲንግ ይህንን ኩባንያ ሥራ ሲያስጀምር ለራሱ ብቻ አስቦ አይደለም ያሉት አቶ ቢኒያም ፋብሪካው የሕዝብ ንብረት ሆኖ እንዲተዳደር ለማድረግ ለሕዝብ አክሲዮን የሚሸጥ መሆኑንና ይህም በቅርብ ጊዜ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ካንትሪ ትሬዲንግ ምርቶችን በማከፋፈልና በመሸጥ የላቀ ድርሻ ለነበራቸው ባለ መደብሮችና የሽያጭ ሠራተኞች ሽልማት በሰጠበትና ምርቱን ገዘተው ለነበሩ ደንበኞች ከምርቱ ጋር ሸጦላቸው በነበረ ሎተሪ አወጣጥ ሥነስርዓት ላይ የተገኙት የአኪራ ኢንተርናሽናል ሽያጭ ማናጀር ሚስ ፔ ሆም ቦም፣ በአፍሪካ የመጀመሪያው የአኪራ ቴሌቪዥን መገጣጠሚ ፋብሪካ በኢትዮጵያ መክፈት ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ገልፀዋል፡፡ እንደ ማናጀሯ ገለፃ መገጣጠሚያ ፋብሪካውን በካንትሪ ትሬዲንግ በኩል ኢትዮጵያ ውስጥ በመክፈት ሌሎች የአፍሪካ አገሮች ምርቱን ከኢትዮጵያ እንዲገዙ እንደሚያስችላቸው ከትናንት በስቲያ ምሽት በግዮን ሆቴል በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ አስረድተዋል፡፡ በዳዊት ታዬ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |