Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 06th
Home arrow Sections arrow የዶላር ምንዛሪ በጥቁር ገበያ ከአስር ብር በለጠ
የዶላር ምንዛሪ በጥቁር ገበያ ከአስር ብር በለጠ Print E-mail
Wednesday, 27 February 2008
በጥቁር ገበያ የአንድ ዶላር ምንዛሪ ከአስር ብር በላይ መድረሱንና የሌሎች የውጭ ገንዘቦች ምንዛሪ ዋጋም በተመሳሳይ መልኩ እድገት እያሳየ መምጣቱ ተጠቆመ፡፡
የዶላር ምንዛሪ ዋጋ በተለይ ካለፉት ሦስት ሣምንታት ወዲህ በፍጥነት እያደገ በኢትዮጵያ የዶላር ምንዛሪ ታሪክ አንድ ዶላር ከአሥር ብር በላይ ሲወጣ የመጀመሪያ ጊዜው ነው፡፡

ከአንድ ዓመት በላይ የአንድ ዶላር ዋጋ በጥቁር ገበያ ከ9.20 እስከ 9.60 ባለው መካከል ሲመነዘር የቆየ ሲሆን በባንኮች ደግሞ አንድ ዶላር ከዘጠኝ ብር ባነሰ እየተመነዘረ የቆየ ቢሆንም ከሦስት ሳምንታት ወዲህ ግን በባንኮች ጭምር የምንዛሪ ዋጋው እያሻቀበ መጥቶ በአማካይ 9.50 ብር በጥቁር ገበያ ደግሞ 10 ብር ከ2ዐ ሳንቲም ነው፡፡

በጥቁር ገበያ እየታየ ያለው የዶላር ምንዛሪ ዋጋ እድገት ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ከአንድ ብር በላይ እንዲሆን አድርጐታል፡፡ በባንኮች በኩልም የአንድ ዶላር ምንዛሪ ዋጋ ለረጅም ጊዜያት ከ8.80 እስከ 9.05 አካባቢ ነበር፡፡ በዚህ ዓመት ግን ምንዛሪው በፍጥነት በማደግ ላይ እንደሆነ ያሳያል፡፡

ያነጋገርናቸው አንዳንድ የባንክ ባለሙያዎች የዶላር ምንዛሪ በጥቁር ገበያም ሆነ በባንኮች እድገት እያሳየ መምጣቱ ከውጭ ምንዛሪ እጥረት ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

በዳዊት ታዬ
 
< Prev   Next >