Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow ሀኪምን ያስናቀ ኮምፒውተር
ሀኪምን ያስናቀ ኮምፒውተር Print E-mail
Wednesday, 27 February 2008
የአእምሮ ህመሞችን ለመመርመር ከሀኪሞች በተሻለ መስራት የሚችል ኮምፒውተር መኖሩ ታወቀ፡፡ ደረጃቸውን የጠበቁ ኮምፒውተሮች የመርሳት በሽታን ለመመርመር ያላቸው ውጤታማነት ተጠንቶ 96 በመቶ ውጤታማ ሆኖ መገኘቱን ኤክስፐርቶች አስታውቀዋል፡፡
በኮምፒውተር የአእምሮ ህመምን በተሻለ መልኩ መመርመር መቻሉም ለተለያዩ በሽታዎች በተሻለና ውጤታማ በሆነ መልኩ መድኃኒቶችን መጠቀም እንደሚያስችልም ተመራማሪዎች ገልፀዋል፡፡ የኮምፒውተር ምርመራው በመድኃኒቶቹ የተሻለ ውጤት እንዲኖር የሚያስችለው የአእምሮ ህመሙ ያለበትን ደረጃ በትክክል ማሳየት ስለሚችል ነው፡፡

የአንታርክቲካ ግግር በረዶ እየቀለጠ ነው

በአንታርቲካ የበረዶ ግግር ላይ የሚሰሩ የእንግሊዝ ሳይንቲስቶች እንደሚሉት በተለይ በምዕራብ አንታርክቲካ የሚገኘው የበረዶ ክምር እየቀለጠ ነው፡፡ ሂደቱ በዚህ ከቀጠለም በዓለም ደረጃ የባህር ውሃ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል፡፡

ከሳይንቲስቶቹ ጥናት ግኝት የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው የቴክሳስ ጠረፍ አካባቢዎች የሚገኘው በረዶ ቅልጠት መጠን ጨምሯል፡፡ ይህም ለወደፊቱ በአካባቢው አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል የሚያሳይ እንደሆነ ሳይንቲስቶቹ ገምተዋል፡፡

እንደ ሳተላይት መረጃዎች እ.ኤ.አ 199ዐዎቹ ጀምሮ የበረዶ ቅልጠት መጠን በየዓመቱ በአንድ በመቶ እየጨመረ ነው፡፡ በዚህ ዓመት ግን የቅልጠቱ መጠን ሰባት በመቶ ጨምሯል፡፡ በዚሁም ምክንያት በርካታ በረዶ ቀልጦ ከባህር ጋር ተቀላቅሏል፡፡ "ለዚሁም ምክንያቱ የአካባቢው ሙቀት መጨመር ብቻ አይሆንም" የሚል ግምት እንዳላቸው ሳይንቲስቶቹ ገልፀዋል፡፡

የፀጉር መነቀል ችግር በዘር ይተላለፋል


በቀን እስከ መቶ የራስ ፀጉር ዘለላዎች መነቀል በአንድ ጤነኛ ሰው ላይ የሚታይ ጤናማ ሂደት ነው፡፡ የሚያስጨንቅም አይደለም፡፡ ምክንያቱም በየቀኑ እያንዳንዱ የሚረግፍ ፀጉር በተፈጥሯዊ መንገድ ራሱን ይተካል፡፡ ከመቶ በላይ የሚነቀል ከሆነ ግን ችግር መኖሩ በግልፅ የሚታይ ይሆናል፡፡

ከቦን ዩኒቨርሲቲ የተወጣጡ ተመራማሪዎች ለስድስት ዓመታት ባደረጉት ጥናት ከተፈጥሯዊው ሂደት ባለፈ የፀጉር መነቀል ችግር የሚያስከትለውን ዘረመል/ጂን አግኝተዋል፡፡ በዘር የሚተላለፈው የፀጉር መነቀል ችግር ፣ሃይቻትሪችሲስ ልምኘሌክስ፣ ይባላል፡፡

ሳይንቲስቶቹ እንደሚሉት የፀጉር መነቀል ችግር በዘር እንዲተላለፍ የሚያደርገው ጂን መገኘቱ ለችግሩ መፍትሔ የሚሆን መድኃኒት ለማግኘት ያስችላል፡፡ የፀጉር መነቀል ችግር በሴቶችም ሆነ ወንዶች ላይ የሚከሰት ሲሆን አንዳንዴ ገና በልጅነት መላጣ እስከመሆን ሊያደርስ ይችላል፡፡ ችግሩ እድሜ በጨመረ ቁጥር በስፋት እየቀጠለ የሚሄድ ነው፡፡

ወደ ማርስ የሚላከው ፣ተሽከርካሪ፣ ሙከራ ጀመረ

ወደ ማርስ የሚላከውን ፣ተሽከርካሪ፣ ዓይነት ሞዴል ሙከራ መጀመሩን ኤክስፐርቶች አስታውቀዋል፡፡

እንደ ቢቢሲ ዘገባ ከሆነ ማርስ ላይ ህይወት ያለው ነገር ለመፈለግ ሳይንቲስቶች አዲስ ሙከራ እያደረጉ ነው፡፡ ለዚህ ስራ መሳካትም ኘላኔቷን ሊዞር የሚችል ተሽከርካሪ መላክ የግድ ሆኗል፡፡ የታሰበውን ዓይነት ተሽከርካሪ ሞዴልም ሙከራ እየተደረገበት ይገኛል፡፡ በኘላኔቷ ዙሪያ የተለያዩ ናሙናዎችን የሚሰበስብ አምስት ተሽከርካሪ እጆች ያሉት ሮቦት እና ካሜራ ግን ከዚህ ቀደም ሙከራ ተደርጐባቸዋል፡፡

ከፀሃይ ቀጥላ በአራተኛነት የምትገኘው ኘላኔት ላይ ያሉት አዳዲስ ነገሮችን ለማወቅ በሚካሄደው ኘሮጀክት 14 አገሮች ድርሻ አላቸው፡፡ በማርስ ላይ የሚካሄደው ሚሽን እንደቀጠለ ሲሆን ለጥናት እገዛ እንዲያደርግ የታሰበው ተሽከርካሪ እ.ኤ.አ በ2013 የሚመጥቅ ሲሆን በ2014 መጨረሻ አካባቢ ቀዩዋ ኘላኔት በመባል ወደምትታወቀው ማርስ እንደሚያርፉ ይጠበቃል፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ በባዮ ፊውል የአውሮኘላን በረራ ተካሄደ

አንድ የንግድ አውሮኘላን በመጀመሪያ ጊዜ በከፊል ባዮፊውል በረራ ማድረጉ ተገለፀ፡፡ በረራው ከለንደን ሔዝሮው እስከ አምስተርዳም ሲሆን የባዮፊውሉ ከብራዚሉ በባሱ ለውዝና ኮኮናት የተሠራ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የአካባቢ ጥናት ባለሙያዎች በረራው ሕዝባዊ እውቅና እንዲሰጠውና "በባዮፊውል ላይ የሚደረግ ምርት ዘለቄታዊ አይደለም" ለሚለው ምላሽ እንደሚሰጥ ተጠቁሟል፡፡

እስከዚህ ወር መጨረሻም ተመሳሳይ ሙከራ በኤር-ባስ እንደሚደረግ ተመልክቷል፡፡ የቨርጅን አትላንቲክ ጃምቦ ጄት ኃላፊ ሪቻርድ ብራንሶን እንዳሉት በረራው ወሳኝና በበረራ ኢንዱስትሪውን ለስኬት የሚያግዝ ነው፡፡ የመጀመሪያ የሆነው በረራም በካርቦን ልቀት እየተፈጠረ ያለውን ቀውስ ለመቀነስ የሚያግዘውን ነዳጅ ለማምረት እንደሚያበረታታ ተናግረዋል፡፡

በባዮ ፊውል በሚደረግ በረራ ከተወሰነ ከፍታ በኋላ ወደ በረዶነት የመቀየር ፀባይ ሊኖረው እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

ቴክኖሎጂው በሂደት ላይ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ቨርጅን አየር መንገድ እምነት አውሮኘላኖች በ1ዐ ዓመታት ውስጥ ከእፅዋት በሚገኝ ነዳጅ ሙሉ በሙሉ እንደሚበሩ ተመልክቷል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በባዮፊውል ላይ የሚሠሩ የምርምር ሥራዎች የአየር ብክለትን ከመቀነስ አንፃር ያላቸው አስተዋፅኦ አነስተኛ እንደሆነ የገለፁት የአየር ንብረት ባለሙያው ኬኔት ሪቸር የምርምሩ ቀጣይነት በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ያለውን ችግር ለመፍታት ወሳኝ መፍትሄ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
 
< Prev   Next >