Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow ክቡር ሚኒስትር
ክቡር ሚኒስትር Print E-mail
Wednesday, 27 February 2008
[የሥራ ቀን ነው፣ የሥራ ሰዓት ነው፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ ግን በአንድ ትልቅ ሆቴል ጂም ውስጥ ናቸው፡፡ ስፖርት እየሰሩ ያወራሉ]
- ክቡር ሚኒስትር ለምን ደስ እንደሚሉኝ ያውቃሉ?
- አላውቅም፡፡
- እጅግ በጣም ዘመናዊ ነዎት፡፡
- እጅግ በጣም አመሰግናለሁ፡፡
- በዚህ ሰዓት እንዴት ስፖርት ይሰራሉ ብሎ የሚያማ አይጠፋም፡፡ ሌሊቱን ሲሰሩ አድረው ነው ወደ ጂም የመጡት?
- ሌላ ጊዜ እንዳልከው ስሰራ አድራለሁ፡፡ ትናንት ግን አንድ ጓደኛዬ ጋብዞኝ እዚያ አመሸሁና ደከመኝ፡፡
- አንድ ቀን ሊሆን ይችላል፡፡ ሌላ ጊዜ ግን ሲሰሩ ያድራሉ አይደል ክቡር ሚኒስትር?
- ትክክል ነህ በተለይ ሰሞኑን እንቅልፍም አጥቻለሁ፡፡
- ምን ተገኘ?
- ይህ የወርቅ ጉዳይ ነዋ!
- ታዲያ እርስዎ ምን አገባዎት? የእርስዎ መሥሪያ ቤት ሥራ አይደለም፡፡
- ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኮሚቴ አቋቁመው ያለው ወርቅ እውተኛነት ተጣርቶ እንዲቀርብልኝ ብለዋል፡፡
- አስጠሊታ ድርጊት ነው የምታየው፡፡ ነገሩ በሙሉ ባሌስትራ ይመስልሃል፡፡ የእናቴን የወርቅ ጥርስ እንኳ መጠራጠር ጀምሬያለሁ፡፡ ነጋዴዎቹ ሲያጭበረብሩ ዓይን የላቸውም፡፡ ለመስረቅምኮ ብልጥና ብልህ መሆን ያስፈልጋል፡፡
- መስረቅማ ሁሉም ይሰርቃል፡፡ የእነዚህ ግን ዓይን ያወጣ ነው፡፡ አይደል ክቡር ሚኒስትር?
- እውነት ነው፡፡ ሰው አይሳሳትም አይባልም፡፡ ኑሮ አልሟላ ሲል ጉቦ መውሰድ፣ ስጦታ መቀበል፣ ግብር አለመክፈል የመሳሰሉ አሉ፡፡ ይህ ግን ጥሩ አይደለም፡፡
- ክቡር ሚኒስትር አጣርታችሁ ምን አገኛችሁ?
- ምን መሰለህ የባንኮች ሁኔታ አጥኑ ስለተባልን ስለ ልማት ባንኩ ሁኔታም እያጠናን ነው፡፡
- ታዲያ እሱ ምን ችግር አለው? እርስዎ እዚያ ያሉትን ሰዎች በሚገባ ያውቋቸዋል?
- አውቃቸዋለሁ፡፡ ወዳጆቼ ናቸው የሚያናድደኝም ይሄ ነው፡፡
- ለምን ይናደዳሉ ክቡር ሚኒስትር?
- አንዳንዶቹ እኔንም ጭምር ነበርክበት፣ ግንኙነት ነበረህ ሊሉኝ ይፈልጋሉ፡፡
- እርስዎ ነጋዴውን በማገዝ የታወቁ ስለሆኑ ቅናትም ሊሆን ይችላል፡፡
- ነው እንጂ፡፡ ቅናት፣ ምቀኝነት፣ ኋላ ቀርነት፡፡ እዚህ እየመጣሁ ስፖርት ስሰራ፣ ማሳጅ ሳደርግ፣ ስዋኝ ..ኃላፊነት አይሰማውም.. ይሉኛል፡፡
- እርስዎ ዋይን ይጠጣሉ፣ ሌሎቹ ከቢራ ሌላ አያውቁም፡፡ እርስዎ ስቴክ ይበላሉ፣ አሮስቶ ይበላሉ፣ አይስክሬም ይወዳሉ፡፡ ሌሎቹ ሚኒስትሮች እኮ ከቅልጥምና ዱለት ውጭ ምግብ ያለም አይመስላቸውም፡፡ ዘመናዊ አይደሉማ፡፡
- እውነትህን ነው፡፡ ዘመናዊ በመሆን የኢትዮጵያን ገፅታ መቀየር አለብን፡፡ አሁን ደግሞ ለምን እዚያ ትልቁ ሆቴል ባር ላይ ሁሌ ታመሻለህ ይሉኛል፡፡ ያን ሆቴልና ባር እወደዋለሁ ዘመናዊ ነው፡፡ ጂም ስለሌለ ነው እዚህ የመጣሁት እንጂ እዚያው እሰራ ነበር፡፡ ብዙ ነገር አለ፡፡ እዛኛው ሆቴል ባር እንደተለመደው ኋላ ላይ ተገናኝተን በደንብ እናወራለን፡፡
- እሺ ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ቻው!

[ማታ በሌላኛው ትልቅ ሆቴል ባር እየጠጡ ያወራሉ]

- ይጠጡ እንጂ ክቡር ሚኒስትር፡፡ እኔ የምጠጣው ሁሉ አሁን አልከፍልም፡፡ ፅፌ ፈርሜ ሌላ ጊዜ ነው የምከፍለው፡፡ የፈለጉትን ይጠጡ ክቡር ሚኒስትር፡፡
- በዚህ ዓይነት ሳይታወቅህ ብዙ እየጠጣህና እየጋበዝክ ዕዳ ውስጥ ትገባ ይሆናል፡፡
- አዎን አንዳንዴ ሳይታወቀኝ ብዙ ይሆናል፡፡
- ለነገሩ ሰውዬው ጥሩ ሰው ነው፡፡
 - አልገባኝም፡፡
- ብዙ ዕዳ ቢሆንም እንደ ዓለም ባንክና አይ.ኤም.ኤፍ የእዳ ቅነሳ ያደርግልህ ይሆናል፡፡
- ምን የዕዳ ቅነሳ...? የዕዳ ስረዛ እንጂ..
- እኮ፡፡
- ክቡር ሚኒስትር ያቺን ነገር እንዴት አረጉልኝ?
- ለእኔ ተወው ብየሃለሁ፡፡
- ጊዜ ወሰደ፡፡
- ብሄራዊ ባንክ ባወጣው ሪፖርት ምክንያት ልማት ባንኮች ስለተደናገጡ ትንሽ ጊዜ ትሰጠኛለህ፡፡ ሰዎቹ ፈርተዋል፡፡ ነገር ግን ፍርሃቱ ለአንድ ሳምንት ነው፡፡ ሴትየዋን ዛሬ አናግራታለሁ፡፡ እሷ በቀላሉ እሺ ትለኛለች፡፡
- ለእርስዎ ሁሉም ነገር በቀላሉ እሺ ትላለች እየተባለ ይወራል፡፡
- ቅድም እንዳልኩህ የምቀኞች ወሬ ነው፡፡
- እርስዎ ግን የእኔን ጉዳይ ጨርሰው ከዚያ በኋላ መልቀቅ አለብዎት፡፡
- ካልገፉኝ እንኳ አልለቅም፡፡
- ይልቀቁ.. ሰውየው ያኛውን እየቀጠረ ነው፡፡ እርስዎንም ይቀጥርዎታል፡፡ እንደውም የተሻለ ገንዘብ ያገኛሉ፡፡
- ለቀቅኩ ስትልማ መንግሥትም ለምን ብሎ ይጠይቃል? ይከታተላል፡፡ ኢሕአዴግ ቀላል ድርጅት መስሎሃል፡፡
- አጉል እንዳይቀሩ ብዬ እኮ ነው፡፡ ለመሆኑ እየተዘጋጁበት ነው?
- አዎን፡፡ ቤት አለኝ፣ የተወሰነ ገንዘብ አለኝ፡፡ ሰውየው አትክፈል ቢሉኝም እዚህ እየከፈልኩ ነው የምጠጣው፡፡ እግዚአብሔር ይመስገን በነጋዴው ሕብረተሰብ የተከበርኩ ነኝ፡፡ አምባሳደሮች ሲያገኙኝ ዘመናዊ ነህ ይሉኛል፡፡ ተመስገን ነው፡፡
- እንትናን ያስሩት ይሆንል እየተባለ ይወራል፡፡
- እኔ እስካለሁ ድረስ ምንም አይሆንም፡፡
- ኧረ ለሁላችንም ስትል ቆይ እንዲያውም አትልቀቅ፡፡
- እኔምኮ ለዛ ብዬ ነው ባልለቅ ይሻላል የምልህ፡፡
- ብዙ ነጋዴ ጓደኞቼ አሉኝ ሊያነጋግሩህ ይፈልጋሉ፡፡ ቤትህ ቢመጡና እራት እየበላችሁ ብታወሩ ምን ይመስልሃል?
- ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን ባለቤቴ ስለሌለች እራት የሚሰራ የለም፡፡
- የት ሄዱ?
- አሜሪካ
- በዚህ ሰዓት፡፡ እዚያ አሁን ብርድ ነው፡፡
- ልማት ባንክ ሰባት መቶ ሚሊዮን ብር ከሰረ የሚል ዜና በጋዜጣ ስታነብ ያስሩኛል ብላ በርግጋ ሄደች፡፡
- ምን ሆንኩ ብለው፡፡ ዝሆኖች ይታሰራሉ ሲባል ሰምታ ጥንቸልዋ ሸሸች እንደሚባለው ነው?
- ..እስኪጣራ ድረስ.. ብላ ይሆናል፡፡
- አንድ ነጋዴ ቤት እራት ይዘጋጅና እርስዎ እዚያ ሄደው ይገናኛሉ፡፡
- ምን ፈልገው ነው?
- ወዳጃችን ነው ሃቀኛ ነው፣ ለምን አንረዳውም ብለው ነው፡፡ ሊረዱህ ይፈልጋሉ፡፡
- ምን ልበላቸው?
- ክቡር ሚኒስትር ቤት አለኝ፣ መኪና አለኝ ይበሏቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ይቀበሉና የሚሆነውን በኋላ እንነጋገራለን፡፡
- ያው እንደምታውቀኝ እኔ መልሼ ለተቸገረ ነው የምሰጠው፡፡
- እኮ፡፡
- ከወርቅ ጋር ግንኙነት ያላቸው ባይሆኑ ጥሩ ነው፡፡
- ለምን ክቡር ሚኒስትር?
- መንግሥት እየተከታተላቸው ስለሆነ ችግር ሊከተል ይችላል፡፡
- እነዚህ ባሌስትራ ሳይሆን እውነተኛ ወርቅ ነው የሸጡት፡፡ ያውቃቸዋል በልማት ባንክ ብዙ አግዘዋቸዋል፡፡
- እስቲ ብቻ ጥንቃቄ ያስፈልጋል፡፡
- አንዳንዱ ሚኒስትር ከሥራ ቢወጣ ስልክ ውሃና መብራት እንደሚቋረጥበት ያውቃሉ፡፡ አምስት ሳንቲም አይኖረውም፡፡ እንደነሱ መሆን ይፈልጋሉ?
- እሺ አልኩ እኮ፡፡ እሄዳለሁ፣ አገኛቸዋለሁ፡፡
- ጎሽ ለእርስዎ ብለው አይሰጡዎትም፡፡ ለልጆቹ ብለው ነው የሚሰጡዎት፡፡ ለልጆችዎ ሲሉ ይቀበሉ፡፡
- የማላውቃቸው ሰዎች ይኖሩ ይሆን?
- አይ ክቡር ሚኒስትር አይኖሩም፡፡ አንዱ ግን አታውቀውም እንጂ ከዚህ በፊት በቫት ጉዳይ ታስሮ ከጉድ ያወጣኸው አንተ ነህ፡፡ እሱ በሚገባ ያውቅሃል፡፡
- እሺ በቃ ነገ ነው ያልከኝ?
- አዎን ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ቻው፡፡

[በማግስቱ ክቡር ሚኒስትር አንደኛው ቤት ሄዱ፡፡ ሌሎችም እዚያ መጥተው ያወራሉ]

- ክቡር ሚኒስትር እርስዎ አባታችን ነዎት በጣም ነው የምናመሰግንዎት፡፡
- ለምን ባንክ ካላበደረ ባንክነቱ ለምንድነው?
- እውነት ነው ነገር ግን እርስዎ ባይኖሩ ኖሮ አይሰጠንም ነበር፡፡
- እኔ ደስ ያለኝ ከባንክ ከወሰዳችሁ በኋላ አገርን ማልማታችሁ ነው፡፡ ሁላችሁም ውጤታማ ሆናችኋል፡፡ ለወደፊቱም በርቱ፡፡
- ክቡር ሚኒስትር ለወደፊቱማ አንድ ችግር እንዳይፈጠር ፈራን፡፡
- ምን?
- ይኸውልዎት ክቡር ሚኒስትር ብዙ ሰዎች በወርቅ ምክንያት እየታሰሩ ናቸው፡፡ ጓደኞቻችንም ታስረዋል፡፡
- እና?
- እንዲያውም የአንዱ እናት በልቅሶ አይናቸው ሊጠፋ ነው፡፡
- እና?
- ለእናትዮዋ ሲባል እኛ ዋስ ሆነን ብናስፈታውስ?
- ሕዝብ ዓይንና ጆሮ ውስጥ የገባ ነገር ስለሆነ አስቸጋሪ ነው፡፡
- እርስዎ መርማሪዎቹን ቢያነጋግሩልን?
- ምን ብዬ?
- እናትየዋ እንዳይሞቱ በዋስ ቢወጣና በቀጠሮ ቀን ቢቀርብ፡፡
- ወንጀሉ ከባድ ነው ተብሏል፡፡
- የጠላት ወሬ ነዋ፡፡ እነዚህ ሰዎች በግብር ከፋይነት ስለተሸለሙ  በኤክስፐርትነት ስለተሸለሙ ጠላት በዛባቸው፡፡
- እስቲ እዚያ ባንክ ውስጥ ይህን ጉዳይ የሚያውቁ ወዳጆች ስላሉ እነሱ ጋ ልደውል፡፡
- ምን ክፍል ናቸው?
- ትሬዠሪ ግምጃ ቤት፡፡
- ክቡር ሚኒስትር እሳቸውንማ ዛሬ አስረዋቸዋል እኮ፡፡
- ታሰሩ እንዴ?
- አዎን፡፡
- [በመደንገጥ] ከወርቁ ጋር በተያያዘ?
- አዎን፡፡
- እስቲ ሄጄ ላጣራ

[ክቡር ሚኒስትር ወደ መኪናቸው አመሩ፡፡ ሰዎችን አዩ]

- ጤና ይስጥልኝ፡፡ ይህ መኪና የኔ ነው፡፡ ምን ፈልጋችሁ ነው?
- እርስዎን ፈልገን ነው፡፡
- ለምን?
- በሕግ ይፈለጋሉ፡፡ ወንጀል ምርመራ ይዘንዎት ልንሄድ ነው፡፡
- ለምን? በምን ምክንያት?
- ክቡር ሚኒስትር ከወርቅ ጋር በተያያዘ ጉዳይ ሊጠየቁ ይፈለጋሉ፡፡
- በወርቅ?
- ጥርጣሬ ነው፡፡
- እና ብትጠረጥሩ፣ ብትጠረጥሩ እኔም ወርቅ ነው ብዬ ባሌስትራ እንዳላስገባ ፈራችሁ?
- ጥያቄው ባሌስትራን ወርቅ ነው ብለው አስገቡ አይደለም፡፡
- ታዲያ ምን ተብሎ ነው የምታሰረው?
- ወርቅ ሰው ነዎት ተብለው ተሹመው ባሌስትራ ሆነው በመገኘትዎ ነው፡፡
 
< Prev   Next >