Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 28th
Home arrow Sections arrow አስተዳደሩ በድክመቱ ላይ ትኩረት ያድርግ
አስተዳደሩ በድክመቱ ላይ ትኩረት ያድርግ Print E-mail
Wednesday, 27 February 2008
በሪፖርተር ጋዜጣ የካቲት 16 ቀን 2000 እትም እኔ የምለው ገጽ ..አዲስ አበባን የገደላት ሥራ ወይስ ወሬ.. በሚል ርዕስ ከአዲስ አበባ ጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደር የማስታወቂያና ባህል ቢሮ የቀረበውን የመልስ ጽሑፍ አንብቤዋለሁ፡፡ ከቢሮው የቀረበው ይህ ጽሁፍ አትንኩኝ ባይነትን ያንጸባረቀ፣ በአስተዳደሩ ላይ በገሃድ የሚታዩትን የመልካም አስተዳደር እጦትና ሙስናን ሸፋፍኖ ያለፈ ነው፡፡
ከመሬት ጋር በተያያዘ በርካታ ሙስናዎች በመፈጸማቸው በቁጥጥር ስር የዋሉ በርካታ ኃላፊዎች መኖራቸው እንዴት ተዘነጋ? ከቀበሌ እስከ ክፍለ ከተማና እስከ አስተዳደሩ ድረስ በመልካም አስተዳደር እጦት ሳቢያ የሚጉላሉ ባለጉዳዮች ችግር ምን ዓይነት መፍትሄ ተበጀለት?

የጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደሩ ኃላፊነቱን ሲረከብ በጅምር የነበሩትን የጋራ ቤቶች ተረክቦ ዳር ማድረሱ አይካድም፡፡ ጥያቄው ግን ሁሉም ቤቶች በትክክልና በአግባቡ ለተጠቃሚዎች ተዳርሰዋል ወይ የሚለው ነው፡፡ ማግኘት የሚገባው ያጣበት፣ ማጣት የሚገባው ያገኘበት እንቅስቀሴ የለም?

ከተማዋንም ለነዋሪዎቿ ምቹ የማድረጉ ሥራ በስፋት እንደተከናወነ አድርጎ መጻፉ ..አይናችሁን ጨፍኑና ላሞኛችሁ.. ዓይነት ነው፡፡ ምክንያቱም በገሃድ የሚታየው ከተማዋ ፅዳቷ እየተጠበቀ ሳይሆን የደረቅ ቆሻሻ መከማቻና የፍሳሽ ቆሻሻ መተላለፊያ መሆኗ ነው፡፡ ..የደረቅ ቆሻሻ ማንሻ ያለህ?.. እያለች በመጮህም ላይ ነች፡፡

የከተማው አስተዳደር አንዳንድ ጠንካራ ጎኖቹን ጠቃቅሶ ከመኩራራቱ ይልቅ ደካማ ጐኑን እየዳሰሰ ዕድሜ እስከሰጠው ዕለት ድረስ ጠንክሮ ቢንቀሳቀስ መልካም ነው፡፡

(አብርሃም ኃይሌ፣ ከፒያሳ)
 
< Prev   Next >