Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 07th
Home arrow Sections arrow የዓፄ ዮሐንስ ቅሪተ አካል እንዲመለስ...
የዓፄ ዮሐንስ ቅሪተ አካል እንዲመለስ... Print E-mail
Sunday, 02 March 2008
የዓፄ ዮሐንስ ቅሪተ አካል እንዲመለስ ጥያቄ ሊቀርብ ነው

በ1881 ዓ.ም በመተማ ከደርቡሽ ጋር ሲዋጉ የተሰውት አፄ ዮሐንስ አራተኛ ጭንቅላታቸውን ወደ እናት አገሩ ለማስመለስ እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡ እንቅስቃሴው አገራዊ ጉዳይ በመሆኑ ሁሉም እንዲተባበር ተጠይቋል፡፡
የዓፄ ዮሐንስ አራተኛ ጭንቅላት ከሱዳን እንዲመለስ እየተንቀሳቀሰ ያለው ኮሚቴ ጊዜያዊ አስተባባሪ አቶ ተኪአ ገ/መድህን ለሪፖርተር እንደገለፁት፣ ጥረቱ የተጀመረው ቀደም ብሎ ሲሆን እስከ አሁን በሺዎች የሚቆጠሩ ፊርማዎች ተሰባስበዋል፡፡ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ውስጥም ከ20 ሺህ በላይ ሰው ይፈርማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል፡፡

እንደ አቶ ተኪአ ገለፃ፣ አፄ ዮሐንስ ደርቡሽ መተማን እያቃጠለ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በመድፈሩ ወረራውን ለመቀልበስ ሲዋጉ የተሰውት ታላቅ መሪ ጭንቅላታቸው በደርቡሾች ተቆርጦ ከተወሰደ በኋላ ለሳምንታት በከተማ እያዞሩ ሲጨፍሩበት መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

“የአገሬ ህልውና ተጠብቆ ይኖራል፣ እኔ ግን እሞታለሁ” ብለው አንገታቸውን ለሰይፍ የሰጡ እኚህ ታላቅ ንጉሠ ነገሥት ጭንቅላታቸው ወደ እናት አገሩ ተመልሶ በክብር እንዲያርፍ፣ አደባባይ እንዲሰየምላቸው የመታሰቢያ ሐውልት እንዲቆምላቸው እንዲሁም በሚድያዎች በኩል ተገቢ ትኩረት እንዲሰጣቸው እንጠይቃለን” ይላል መግለጫው፡፡

“አዲሱ ትውልድ የአፄ ዮሐንስ ታሪክ ማውሳት ማለት የኢትዮጵያ ታሪክ ማውሳት መሆኑን አውቆ፣ ታሪካቸውን ጠንቅቆ እንዲያውቅና ይህ የአገር ትልቅ ቅርስ ወደ እናት አገሩን ለማስመለስ ጥረት ማድረግ ይኖርበታል” ብለዋል አቶ ተኪአ፡፡

አቶ ተኪአ በማከልም “አፄ ዮሐንስ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ሲፈታተኑ የነበሩት እንደ ጣልያን፣ ግብፅና ሱዳን የመሳሰሉ በርካታ የውጭ ወራሪዎች በመመከት የአገራችን አንድነት ጠብቀው ያለፉ ታላቅ መሪ ናቸው” በማለት አገሩን የሚወድ ማንኛውም ዜጋና መንግሥት የተጀመረውን ይህንን ጥረት ለማሳካት የቻለውን ሁሉ እንዲሰራ ጠይቀዋል፡፡

የአጼ ዮሐንስ ጭንቅላት ሱዳን ስለመኖሩ ተጠይቀው የታሪክ ምሁራን ሱዳን እንደሚገኝ እንዳረጋገጡላቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

በየማነ ናግሽ
 
< Prev   Next >