Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow በአፋር የቱሪስቶች ጠለፋ ሙከራ ሁለት...
በአፋር የቱሪስቶች ጠለፋ ሙከራ ሁለት... Print E-mail
Sunday, 02 March 2008
በአፋር የቱሪስቶች ጠለፋ ሙከራ ሁለት ሹፌሮች የገቡበት አልታወቀም

በቅርቡ በአፋር ክልል ዳሎል አካባቢ በጉብኝት ላይ የነበሩ 28 ፈረንሳዊ ቱሪስቶችን ለማገት የተደረገው ሙከራ እንደከሸፈ እና ቱሪስቶቹ በደህና ወደ አዲስ አበባ እንደተመለሱ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን የተገለፀ ቢሆንም ቱሪስቶቹን ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ሁለት ኢትዮጵያውያን ሾፌሮች የት እንደደረሱ እስካሁን አልታወቀም፡፡
ቱሪስቶቹን ያስጐበኝ የነበረው ዴይዚ ቱር ተቀጣሪ የሆኑት ኤርሚያስ አስራት እና ጉዲና መዐዛ የጠለፋ ሙከራ ከተደረገበት ረቡዕ የካቲት 12/2000 ዓ.ም ጀምሮ የደረሱበት አልታወቀም፡፡ ከአካባቢው የተገኘ መረጃ እንደሚጠቁመው ሁለቱ ኢትዮጵያዊያን ሹፌሮች የጠለፋ ሙከራውን ባካሄዱት ታጣቂዎች ተይዘው ወደ ኤርትራ ግዛት ተወስደዋል፡፡

የኤርሚያስ አስራት ቤተሰቦች ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት ስለ ኤርሚያስ የጠለፋ ሙከራው ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ የሰሙት ነገር እንደሌለ እና ጉዳዩንም ለመንግሥት አመልክተዋል፡፡ ቱሪስቶቹ በሠላም ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸው ተገል”ል፡፡ ለጠፉት ኢትዮጵያኖች ጉዳይ ግን በቂ ትኩረት አልተሰጠም፡፡ ይሄኔ የጠፉት የውጪ ሀገር ዜጐች ቢሆኑ ኖሮ ትልቅ የመወያያ ርዕስ ይሆን ነበር ብለዋል፡፡

የዴይዚ ቱር ኃላፊዎች በስልክ ለማነጋገር ሞክረን ጉዳዩ በመንግሥት የተያዘ በመሆኑ መግለጫ አንሰጥም ብለዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ዋህድ ብርሃኔ ጉዳዩን መንግሥት በመከታተል ላይ እንደሆነ እና አዲስ ነገር ሲኖር ይፋ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡

ከጠለፋው ሙከራ በኋላ ቱሪስቶቹ ወደ አዲስ አበባ በሠላም ተመልሰው ደቡብ ኢትዮጵያን ሲጐበኙ ሰንብተዋል፡፡  

በቃለየሱስ በቀለ
 
< Prev   Next >