| የሃይማኖት ጉዳይ ረቂቅ መመሪያ ወደ... |
|
|
| Sunday, 02 March 2008 | |
|
የሃይማኖት ጉዳይ ረቂቅ መመሪያ ወደ ክልሎችና ዩኒቨርሲቲዎች ተላከ በትምህርት ቤቶች ውስጥ ስላለው የሃይማኖት ጉዳይ በተመለከተ የተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ውይይት እንዲደረግበት ወደ ክልሎችና ዩኒቨርሲቲዎች መላኩን የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ስንታየሁ ወልደሚካኤል ገለፁ፡፡ የትምህርት ሚኒስቴርን የስድስት ወር የስራ ሪፖርት አስመልክተው ከትናንት ወዲያ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት ሚኒስትሩ እንደገለፁት በየደረጃው ውይይት ሲደረግባቸው የቆዩት የሃይማኖት ጉዳይ ረቂቅ መመሪያዎች ወደ ክልሎችና ዩኒቨርሲቲዎች ተልከዋል፡፡ በተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ዙሪያ ከእስልምና ምክር ቤት፣ ከካቶሊክ፣ ከፕሮቴስታንትና ከኦርቶዶክስ የሃይማኖት መሪዎች ጋር ሁለት ጊዜ ውይይት መካሄዱን የገለፁት ዶ/ር ስንታየሁ ከሃይማኖት መሪዎቹ ጋር የተደረገውን ውይይት መነሻ በማድረግ ክልሎችና ዩኒቨርሲቲዎች ውይይት እንዲያደርጉበት ጉዳዩ እንደተላከላቸው ተናግረዋል፡፡ አንዳንድ ክልሎችና ዩኒቨርሲቲዎች በተላከው ረቂቅ መመሪያ ላይ መልስ የሰጡበት ሁኔታ መኖሩንም ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡ ዶ/ር ስንታየሁ እንዳሉት ከክልሎችና ከዩኒቨርሰቲዎች የሚገኘውን ገብረ መልስ መሰረት በማድረግና የሌሎች አገሮችን ተሞክሮ ግምት ውስጥ በማስገባት እንደገና ከሃይማኖት መሪዎች ጋር ሰፊ ውይይት ተካሂዶ ረቂቅ መመሪያው ይፀድቃል፡፡ የዩኒቨርሲቲ ስርዓት አላማዊ መሆን እንዳለበት በህገ መንግስቱ መጠቀሱን የጠቆሙት ሚኒስትሩ አዲስ የሚዘጋጀው የትምህርት ቤት የሃይማኖት ረቂቅ መመሪያም በህገ መንግስቱ የተዘረዘሩ ጉዳዮችን የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በኃይሌ ሙሉ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |