Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 28th
Home arrow Sections arrow በሐረሪ ብሔራዊ ሊግ (ሐብሊ) ውስጥ...
በሐረሪ ብሔራዊ ሊግ (ሐብሊ) ውስጥ... Print E-mail
Sunday, 02 March 2008
Image
አቶ ሙራድ አብዲልሃዲ
በሐረሪ ብሔራዊ ሊግ (ሐብሊ) ውስጥ አለመግባባት ተፈጥሯል


የሐረሪ ብሔራዊ ሊግ (ሐብሊ) በፓርቲው ውስጥ ያለውን ችግር ለመሸፋፈን የተለያዩ ስልቶችን ይጠቀማል ሲሉ አባላቱ ገለፁ፡፡ የፓርቲው ሊቀመንበር ያስተባብላሉ፡፡
በሐረሪ ብሔራዊ ሊግ (ሐብሊ) ውስጥ የአብላጫ ድምጽ ለመያዝ በሚል የጠቅላላ ጉባኤ መቀመጫ እንዲጨመር መደረጉ ለተፈጠረው ቅሬታ መነሻ ነው፡፡

የሐብሊ የአዲስ አበባ የአካባቢ ሊግ ጽህፈት ቤት አባላት ስማቸው እንዳይጠቀስ ጠይቀው እንዳመለከቱት የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የፓርቲውን መተዳደሪያ ደንብ በመጣስ የጠቅላላ ጉባኤ መቀመጫ የጨመሩት አብላጫ ድምጽ ለማግኘት ሲሉ ነው፡፡

ከድሬዳዋ 70፣ ከአዲስ አበባ 80፣ ከሐረር 150፣ ከሌሎች ከተሞች 20 ወንበሮች ያሉት የፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተጨማሪ መቀመጫ የተጨመረው አዲስ አበባና ድሬዳዋ በአንድነት ሐረሪ ካለው ድምጽ ጋር እኩል ስለሚሆኑ ይህንኑ እኩል ድምጽ ለማበላለጥ እንደሆነ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ተናግረዋል፡፡

በዚሁ ምክንያት አስቸኳይ ስብሰባ ያደረገው የሐብሊ የአዲስ አበባ አካባቢ ሊግ ጽህፈት ቤት የተፈፀመው ተግባር የፓርቲውን መተዳደሪያ ደንብ የጣሰ መሆኑን ጠቅሶ ለፓርቲው ሊቀመንበር ደብዳቤ እንደላከ ታውቋል፡፡

ከፓርቲው ደንብና መመሪያ በላይ የሚሆን ማንኛውም አካል በሕግ እንደሚጠየቅ የገለፁት የአዲስ አበባ የፓርቲው አባላት ለሐብሊ ሊቀመንበር በላኩት ደብዳቤ “እርስዎም አንድ የፓርቲው አባል ነዎት” ብሏቸዋል፡፡ ከህግ በላይ ሊሆኑ እንደማይችሉም ገልፆላቸዋል፡፡

“በሐረር ከተማ ያሉት የፓርቲው አባላት የወር ደሞዝተኛ በመሆናቸው ያመኑበትን አስተያየት ለመስጠት ይቸገራሉ” ያሉት የአዲስ አበባ የፓርቲው አባላት “የአዲስ አበባ የፓርቲው አባላት በንግድም ሆነ በኑሮ ግንኙነታቸው ከፌደራል መንግሥት ጋር በመሆኑ በፓርቲው ውስጥ ያለአንዳች ፍርሃት በነፃነት ሃሳባቸውን ስለሚያራምዱ ከደንብ ውጪ ወንበር ለመጨመር የተፈለገው የፓርቲው አመራሮች የፈለጋቸውን ውሳኔ በአብላጫ ድምጽ ለመወሰን ሲሉ ነው” ብለዋል፡፡ አያይዘውም መጨመር እንኳን ቢያስፈልግ ለጠቅላ ጉባኤ ቀርቦ መጽደቅ እንዳለበት አስታውቀዋል፡፡

የሐብሊ ሊቀመንበር አቶ ሙራድ አብዲልሃዲ አዲስ ተጨመረ ስለተባለው  መቀመጫ የቀረበውን ቅሬታ ተጨባጭነት የሌለው ብለውታል፡፡

አከራካሪ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የማዕከላዊ ኮሚቴው ህገ ደንብን የመተርጎም ስልጣኑን ተጠቅሞ የፓርቲውን የጠቅላ ጉባኤ አባላት ከፍ አድርጓል በማለት ሊቀመንበሩ ተናግረዋል፡፡

ለየጽህፈት ቤቱ አስር አስር መቀመጫ መጨመሩን ያስታወቁት አቶ ሙራድ “በጥቅሉ 130 ተጨማሪ የጠቅላላ ጉባኤ መቀመጫ ተጨምሯል፡፡ ይህ ደግሞ ህጋዊ ነው፡፡ የማዕከላዊ ኮሚቴው የመወሰን ስልጣን አለው” ብለዋል፡፡

ፓርቲው ራሱን በገመገመበት ወቅት ከፍተኛ የተባለ የመልካም አስተዳደር ችግር መኖሩን የገለፁት የፓርቲው አባላት “የፓርቲው አመራሮች እያደረጉ ያሉት ተግባር በፓርቲው ውስጥ ያለውን ችግር ለመሸፋፈን ነው” ካሉ በኋላ “በነፃነት ሃሳብ የሚሰጡ ፣ጥገኛ ባለሃብት፣ የሚል ስም ይሰጣቸዋል” በማለት በአባላቱ ዘንድ ያለውን ቅሬታ ተናግረዋል፡፡

በሌላ ዜና ሀርዳ በመባል የሚታወቀው ተቀማጭነቱ አዲስ አበባ የሆነው የሐረሪ ተወላጆች የልማት ማኅበር ፈርሶ በአዲስ እንዲዋቀር እንቅስቃሴ መጀመሩ ታውቋል፡፡

ጉዳዩን አስመልክቶ የማኅበሩ ቦርድ ለሪፖርተር እንደገለፁት “ፓርቲና ማኅበር የተለያዩ ናቸው፡፡ ፓርቲው ሳይፈጠር የተመሰረተን ማኅበር ገድሎ ሌላ ማኅበር ከማቋቋም ያለውን ማጠናከር ይሻላል”

ሀርዳ በአሁኑ ወቅት ምንም ገንዘብ የሌለው፣ ሰራተኞች መልቀቂያ ጠይቀው በመሰናበታቸው የቦርዱ አባላት እየመሩት እንደሆነ ቦርዱ አልሸሸገም፡፡

በአሰግድ ተፈራ
 
< Prev   Next >