| የመንግሥት ቤቶች በህገ-ወጥ ግለሰቦች... |
|
| Sunday, 06 January 2008 | |
|
የመንግሥት ቤቶች በህገ-ወጥ ግለሰቦች እየተያዙ ነው በአስተዳደሩ በተለያየ የሥራ ደረጃ ላይ የሚገኙ የአንዳንድ ቀበሌ አስተዳደር አካላት ከቁርጠኝነት ማነስና ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት ባለመቻላቸው የመንግሥት ቤቶች በህገ ወጦች ተሰብረው እንዲያዙ፣ በፍርድ ቤት ውሳኔ ያለ አግባብ ለግለሰቦች እንዲመለሱ እየተደረገ መሆኑን የአስተዳደሩ ህግና ፍትህ ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ፡፡ በተለምዶ የቀበሌ ቤቶች እየተባሉ የሚጠሩት የመንግሥት ቤቶች በህገ-ወጦች ተሰብረው የመያዝ፣ ኮንዶሚኒየም ቤት የደረሳቸው ግለሰቦች ቤቱን ለመንግሥት ያለማስከረብና በአዋጅ የተወረሱ ቤቶች በፍርድ ቤት ውሳኔ ለግለሰቦች እንዲሰጡ የማድረግ ሥራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኙ ቢሮው ገል..ል፡፡ /አዲስ ልሳን ታህሳስ 19 ቀን 2000 ዓ.ም/ በትግራይ 100 የጤና ጣቢያዎች ሊገነቡ ነው የፌዴራል መንግሥት በትግራይ በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች የተጀመረውን የጤና አገልግሎት የማስፋፋት ሥራ ለማጠናከር በያዝነው ዓመት 100 ጤና ጣቢያዎችን እንደሚገነባ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡ የፌዴራልና የክልል መንግሥታት ከምግባረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት የሕዝቡን የጤና ችግሮች ለመፍታት በርካታ ሥራዎች ማከናወናቸውን፣ አገር በቀል ምግባረ ሰናይ ድርጅት የሆነው የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር የሥነ ተዋልዶና ኤች አይ ቪ /ኤድስን በመከላከል ዙሪያ እያከናወነ ያለው አኩሪ ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል በማለት የፌዴራል መንግሥት ከሚያስገነባቸው አንድ ሺህ ጤና ጣቢያዎች መካከል 100ዎቹን በትግራይ ይገነባል ብሏል፡፡ /ዋኢማ/ ምቹ የህግና የፖለቲካ ሁኔታ ቢኖርም በሴቶች ላይ ጥቃቶች እየተፈፀሙ ነው በኢትዮጵያ የሴቶችን መብት ለማስከበር የሚያስችል ምቹ የህግና የፖለቲካ ሁኔታ ቢኖርም በሴት ላይ አሁንም የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥቃቶችና በደሎች እንደሚፈፀሙ አንድ ጥናት አመለከተ፡፡ አገሪቱ የሴቶችን መብት ለማሟላት ለመጠበቅና ለማረጋገጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተደነገጉ የሴቶች የሰብዓዊ መብት ህጐችና ድንጋጌዎች መቀበሏን፣ በአገር አቀፍ ደረጃ የሴቶች ፖሊሲ ዶክመንት ወጥቶ ሥራ ላይ እንዲውል መደረጉን፣ የሴቶች እኩልነትና ፍትሀዊ ክፍፍልን የሚያረጋግጥ ህግ መፅደቁን፤ በሴቶች ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታትና ምላሽ ለመስጠት የሕግ ማስተካከያ ከተደረገባቸው መካከልም፣ የቤተሰብ ህግ፣ የፌዴራል የወንጀል ሕግና የመሬት አዋጅ እንደሚጠቀሱ፣ ነገር ግን በቤት ውስጥ ጥቃት ዙሪያ 81 በመቶ ሴቶችና 52 ነጥብ 5 በመቶ ወንዶች የሚስት ድብደባን እንደሚደግፉ፣ በአገር ውስጥና በውጭ በህገ ወጥ የሰው ዝውውር፣ ሴቶችንና ህፃናትን ለሥራና ወሲባዊ ድርጊቶች መጠቀም አሳሳቢ ችግር እየሆነ መምጣቱን ጥናቱ አመልክቷል፡፡ /አዲስ ዘመን ታህሳስ 22 ቀን 2000 ዓ.ም/
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ኅብረት ጋር ቀደም ሲል ያልፈረመቻቸውን ስድስት ስምምነቶች አዲስ አበባ ውስጥ ፈረመች፡፡ የፈረመቻቸው ስምምነቶች የአፍሪካ መልስ ማቋቋሚያ ኢንስቲትዩት፣ የአፍሪካ ማዳበሪያ ልማት ማዕከል ማቋቋሚያ ስምምነት፣ በአፍሪካ አገሮች መካከል የአፍሪካ ቴክኒካል ስምምነት መርሃ ግብር ማቋቋሚያ ስምምነት፣ የአፍሪካ ወጣቶች ቻርተር፣ የአፍሪካ ዴሞክራሲ፣ የምርጫና የአስተዳደር ቻርተርና የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የሽብርተኝነት መከላከልና መዋጋት ስምምነቶች መሆናቸው ተገል..ል፡፡ /ኢዜአ/
|
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |