Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 06th
Home arrow Sections arrow ለመንግሥት የፋይናንስ ተቋማት አዲስ...
ለመንግሥት የፋይናንስ ተቋማት አዲስ... Print E-mail
Sunday, 02 March 2008
ለመንግሥት የፋይናንስ ተቋማት አዲስ ስኬልና የደሞዝ ጭማሪ ተደረገ

ለመንግሥት ባንኮችና ኢንሹራንስ ድርጅቶች ተዘጋጅቶ የቀረበው አዲስ የደሞዝ ጭማሪና የደሞዝ ስኬል መንግሥት አፀደው፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የቢዝነስና የኮንስትራክሽን ባንክ ቀደም ብለው የደሞዝ ጭማሪ እንዲደረግ ለመንግሥት የፋይናንስ ድርጅቶች ኤጀንሲ ጥያቄ አቅርበው ነበር፡፡ የገንዘብ ተቋማቱ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ኤጀንሲው ያለውን የኑሮ ውድነት በማጤን፣ የመንግሥት የፋይናንስ ድርጅቶች የመወዳደር አቅም እንዲኖራቸው ከማድረግ አንፃር ጥያቄውን ተቀብሎ ከየተቋማቱ የቦርድ አመራር አባላት ጋር በመነጋገር ረዘም ላለ ጊዜ ጉዳዩን ሲያጠናው ቆይቷል፡፡

ኤጀንሲው የደሞዝ ጭማሪና የስኬል ማሻሻያ በማድረግ አስተያየቱን ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አቅርቧል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ጉዳዩን ካጠኑና ከመረመሩ በኋላ የኤጀንሲውን ጥያቄ ተቀብለው የተጠየቀው የደሞዝ ጭማሪ እንዲደረግ መፍቀዳቸውን ከኤጀንሲው የተገኘ መረጃ አመልክቷል፡፡

በዚሁ መሰረት ሁሉንም የመንግሥት የገንዘብ ተቋማት ያስደስታል፣ የሰራተኛውን ሞራል ይጠብቃል ተብሎ የታመነበት የደሞዝ ጭማሪና የስኬል ማሻሻያ መደረጉን መረጃው ያስረዳል፡፡

ኤጀንሲው ለፋይናንስ ተቋሞቹ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት የደሞዝ ጭማሪው አራት ወር ወደ ኋላ ተመልሶ ከህዳር ወር ጀምሮ በስራ ላይ ይውላል፡፡ ይህ የደሞዝ ጭማሪ ማንኛውንም ክፍልና ሁሉንም ሠራተኛ የሚያካተት ነው፡፡

ይህ ጊዜያዊ ስኬልና ጭማሪው BPR (የሥራ ሂደት ማሻሻያ ሂደት) ፕሮግራሙ እንደፀደቀ አዲስና ቋሚ የተሻለ የደሞዘ ስኬል እስከሚወጣ ብቻ የሚቆይ ነው፡፡

የደሞዝ ጭማሪና የስኬል ማሻሻያ ለማድረግ በመንግሥት የተወሰነው ሂደት በተለይም ወደ ኋላ ተመልሶ አራት ወር እንዲሰራ ተደርጎ መወሰኑ ተከትሎ ያነጋገርናቸው ሰራተኞችና ኃላፊዎች በውሳኔው መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡ ኤጀንሲው ይህንኑ ለማስፈፀም ያደረገውን ጥረትና መንግሥት ለወሰነውን ውሳኔ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በውሳኔው መሰረት ጭማሪው ለሁሉም የተለቀቀ ሲሆን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ግን ለህትመት እስከ ገባንበት ድረስ የጭማሪው ውሳኔ ለሰራተኞች እንዳልተለቀቀ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የልማት ባንክ ምንጮች ውሳኔው ለምን እንዳልደረሳቸው ጠይቀው “ኮምፒዩተሩ በቫይረስ ስለተጠቃ ነው” የሚል መልስ እንዳገኙ ገልፀዋል፡፡

በጋዜጣው ሪፖርተር
 
< Prev   Next >